New Amharic Standard Version

ናሆም 2:1-13

የነነዌ አወዳደቅ

1ነነዌ ሆይ፤ አጥቂ መጥቶብሻል፤

ምሽግሽን ጠብቂ፤

መንገድሽን ሰልዪ፤

ወገብሽን ታጠቂ፤

ኀይልሽን ሁሉ አሰባስቢ።

2አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣

የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም፣

እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ፣

እግዚአብሔር የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል።

3የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፤

ተዋጊዎቹ ቀይ ልብስ ለብሰዋል፤

ዝግጁ በሆኑበት ቀን፣

የሠረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል፤

የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል2፥3 የዕብራይስጡ ትርጒም ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናቱና የሱርስቱ ቅጆች ግን ፈረሰኞች ይፈጥናሉ ይላሉ።

4ሠረገሎች በአደባባይ ወዲያ ወዲህ ይከንፋሉ፤

በመንገዶችም ላይ ይርመሰመሳሉ፤

የሚንበለበል ፋና ይመስላሉ፤

እንደ መብረቅም ይወረወራሉ።

5ምርጥ ተዋጊዎቹን ይጠራል፤

ዳሩ ግን መንገድ ላይ ይሰናከላሉ፤

ወደ ከተማዪቱ ቅጥር ይሮጣሉ፤

መከላከያ ጋሻውም በቦታው አለ።

6የወንዙ በር ወለል ብሎ ተከፈተ፤

ቤተ መንግሥቱም ወደቀ።

7ከተማዪቱ መማረኳና መወሰዷ እንደማይቀር፣

አስቀድሞ ተነግሮአል2፥7 የዕብራይስጡ ቃል ትርጒም በትክክል አይታወቅም።

ሴቶች ባሪያዎቿ እንደ ርግብ ያለቅሳሉ፤

ደረታቸውንም ይደቃሉ።

8ነነዌ እንደ ኵሬ ናት፤

ውሃዋም ይደርቃል፤

“ቁም! ቁም!” ብለው ይጮኻሉ፤

ነገር ግን ወደ ኋላ የሚመለስ የለም።

9ብሩን ዝረፉ፤

ወርቁን ንጠቍ፤

በየግምጃ ቤቱ ያለው፤

የተከማቸውም ሀብት ስፍር ቍጥር የለውም።

10ተበዝብዛለች፤ ተዘርፋለች፤ ተራቍታለች።

ልብ ቀልጦአል፤ ጒልበት ተብረክርኮአል፤

ሰውነት ተንቀጥቅጦአል፤ ፊት ሁሉ ገርጥቶአል።

11አሁን ታዲያ የአንበሶቹ ዋሻ፣

ደቦሎቻቸውን ያበሉበት

ወንዱና ሴቷ አንበሳ የሄዱበት፣

ግልገሎችም ሳይፈሩ የተሰማሩበት ቦታ ወዴት ነው?

12አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃውን ያህል ገደለ፤

ለእንስቶቹም ዐንቆ ገደለላቸው፤

የገደለውን በማረፊያ ቦታው፣

የነጠቀውንም በዋሻው ሞልቶታል።

13የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“በእናንተ ላይ ተነሥቼባችኋለሁ፤

ሠረገሎቻችሁን አቃጥዬ አጨሳለሁ፤

ደቦል አንበሶቻችሁን ሰይፍ ይበላል፤

የምትበሉትን በምድር ላይ አልተውላችሁም፤

የመልእክተኞቻችሁም ድምፅ፣

ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

那鴻書 2:1-13

尼尼微的覆滅

1尼尼微啊,

攻擊者已經向你撲來。

你要進駐堡壘,

把守道路,

集中全力,

準備上陣!

2雖然擄掠者曾擄掠雅各

擄掠以色列

毀壞他們的葡萄樹枝,

但耶和華必恢復雅各的榮耀,

恢復以色列的榮耀。

3他的勇士手持紅色盾牌,

他的士兵身穿朱紅戰衣。

整裝待發之日,

戰車鐵光閃閃,

松木矛槍在空中揮舞。

4戰車在街道上狂奔,

在廣場上橫衝直撞,

亮如火炬,疾似閃電。

5亞述王召集將領,

他們一路跌跌撞撞,

奔上城牆,架起防禦盾牌。

6河閘大開,王宮坍塌。

7王后赤身被擄;

宮女捶胸悲泣,

像鴿子一樣哀鳴。

8尼尼微城自古以來就像聚水的池子,

如今居民卻像洩漏的池水四散奔逃。

雖有人喊:「站住!站住!」

卻無人回頭。

9搶銀子吧!搶金子吧!

城裡有無盡的財富和數不清的寶物。

10尼尼微被洗劫一空!

被洗劫一空!

一片荒涼!

人們膽戰心驚,雙膝哆嗦,

渾身發抖,面色蒼白。

11如今那獅子的洞穴,

那餵養壯獅的地方在哪裡呢?

從前,雄獅、母獅和幼獅曾在那裡出入,

無人驚擾。

12雄獅為幼獅撕碎充足的食物,

為母獅掐死獵物,

洞穴裡堆滿獵物,

堆滿撕碎的肉。

13萬軍之耶和華說:

「我要與你為敵,

燒毀你的戰車,

使刀劍吞噬你的壯獅;

我要使你無法再擄掠他國,

你使者的聲音將從此消逝。」