1ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ። 2በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው። 3ለእነርሱም፣ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሓይ ሞቅ እስክትል ድረስ አይከፈቱም፤ በር ጠባቂዎቹ ዘብ በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ፣ በሮቹን ይዝጓቸው፤ መወርወሪያም ያደርጉባቸው፣ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹን በየጥበቃ ቦታቸው፣ አንዳንዶቹን ደግሞ በየቤታቸው አጠገብ እንዲቆሙ መድቡ” አልኋቸው።
ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር
4ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር። 5ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው።
6የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደየራሳቸው ከተሞች ተመለሱ፤
7የተመለሱትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከሚስጴሬት፣ ከበጉዋይ፣ ከነሑምና ከበዓና ጋር ነው።
የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር፤
39ካህናቱ፦
43ሌዋውያኑ፦
44መዘምራኑ፦
45በር ጠባቂዎቹ፦
46የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦
57የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦
61ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የተመለሱ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ዘሮቻቸው ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፤
63ከካህናቱ መካከል፦
የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቶአል፤
64እነዚህ የየቤተ ሰብ ትውልድ ሐረጋቸውን ከመዝገብ ለማግኘት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ። 65ስለዚህም አገረ ገዡ በኡሪምና በቱሚም አገልግሎት የሚሰጥ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።
66የማኅበሩ ቍጥር በሙሉ 42,360 ነበር፤ 67ይህ 7,337 የወንድና የሴት አገልጋዮቻቸውን አይጨምርም፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው። 68736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች7፥68 አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆች (እንዲሁም ዕዝ 2፥66) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ይህንን ጥቅስ አይጨምሩም።፣ 69435 ግመሎችና 6,720 አህዮችም ነበሯቸው።
70አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዡም 1,000 የወርቅ ዳሪክ7፥70 8.5 ኪሎ ግራም ያህል ነው።፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ። 71ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ7፥71 170 ኪሎ ግራም ያህል ነው። 2,200 የብር ምናን ለግምጃ ቤቱ ሰጡ። 72የቀረው ሕዝብ ባጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ7፥72 1.1 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። 2,000 የብር ምናንና 67 አልባሰ ተክህኖ ነበር።
73ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።
ዕዝራ ሕጉን አነበበ
ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣