New Amharic Standard Version

ሰቆቃወ 5:1-22

1እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኛ ላይ የደረሰውን አስብ፤

ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም።

2ርስታችን ለመጻተኞች፣

ቤቶቻችን ለባዕዳን ዐልፈው ተሰጡ።

3ወላጅ አልባና አባት የሌላቸው ሆንን፤

እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ።

4ለምንጠጣው ውሃ መክፈል ነበረብን፤

ዕንጨታችንንም የምናገኘው በግዢ ነበር።

5የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤

ተጨንቀናል ዕረፍትም አጥተናል።

6እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣

ለአሦርና ለግብፅ እጃችንን ሰጠን።

7አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው አለፉ፤

እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።

8ባሮች ሠልጥነውብናል፤

ከእጃቸው ነጻ የሚያወጣን ማንም የለም።

9በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሣ፣

በሕይወታችን ተወራርደን እንጀራ አገኘን።

10ቈዳችን እንደ ምድጃ ጠቍሮአል፤

በራብም ተቃጥሎአል።

11ሴቶች በጽዮን፣

ደናግል በይሁዳ ከተሞች ተደፈሩ።

12መሳፍንት በእነርሱ እጅ ተሰቀሉ፤

ሽማግሌዎችም አልተከበሩም።

13ጐልማሶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤

ወንዶች ልጆች በዕንጨት ሸክም ተንገዳገዱ።

14ሽማግሌዎች ከከተማዪቱ በር ሄደዋል፤

ጐልማሶች ዝማሬያቸውን አቁመዋል።

15ደስታ ከልባችን ጠፍቶአል፤

ጭፈራችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል።

16አክሊላችን ከራሳችን ላይ ወድቆአል፤

ወዮልን፤ ኀጢአት ሠርተናልና!

17ከዚህ የተነሣ ልባችን ደከመ፤

ከእነዚህ የተነሣም ዐይናችን ፈዘዘ፤

18ባዶዋን የቀረችው የጽዮን ተራራ፣

የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና።

19አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ለዘላለም ትገዛለህ፤

ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

20ስለ ምን ፈጽመህ ትረሳናለህ?

ስለምንስ ለረዥም ጊዜ ትተወናለህ?

21እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን፤

ዘመናችንን እንደ ቀድሞው አድስ፤

22ፈጽመህ ካልጣልኸን፣

ከመጠን በላይ ካልተቈጣኸን።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

耶利米哀歌 5:1-22

求耶和華憐憫

1耶和華啊,求你顧念我們的遭遇,

看看我們所受的恥辱!

2我們的土地被陌生人侵佔,

我們的房屋落入外族人手中。

3我們成了喪父的孤兒,

我們的母親成了寡婦。

4我們喝水要付錢,

燒的柴要用錢買。

5敵人緊追不捨,

我們疲憊不堪,不得安歇。

6為了得到食物,

我們向埃及亞述卑躬屈膝。

7我們的祖先犯了罪,

已經逝去,

我們卻要承擔他們的罪責。

8奴僕做了我們的主人,

無人從他們手中解救我們。

9曠野中殺機四伏,

我們冒著生命危險才得到糧食。

10我們因饑餓而發熱,

皮膚熱如烤爐。

11婦女在錫安遭強暴,

少女在猶大被姦污。

12首領雙手被吊起來,

老人得不到尊敬。

13青年被迫推磨,

孩童肩背柴捆,步履蹣跚。

14老人不再坐在城門口,

青年不再彈琴奏樂。

15我們心中的快樂消失,

我們的舞蹈變成了哀哭。

16榮耀的冠冕從我們頭上落下。

我們犯了罪,我們有禍了!

17此情此景使我們黯然神傷,

淚眼模糊。

18錫安山一片荒涼,

豺狼四處遊蕩。

19耶和華啊,你永遠掌權,

你的寶座世代長存。

20你為何永遠忘記我們?

為何如此長久地棄絕我們?

21耶和華啊,求你使我們回到你身邊,

讓我們歸向你,

恢復我們昔日的繁榮!

22難道你完全棄絕了我們,

仍然向我們大發烈怒嗎?