New Amharic Standard Version

ምሳሌ 3:1-35

ከጥበብ የሚገኝ ተጨማሪ በረከት

1ልጄ ሆይ፤ ትምህርቴን አትርሳ፤

ትእዛዛቴን በልብህ ጠብቅ፤

2ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤

ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል።

3ፍቅርና ታማኝነት ከቶ አይለዩህ፤

በዐንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤

በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው።

4በዚያን ጊዜ ሞገስንና መልካም ስምን፣

በእግዚአብሔርና በሰው ዘንድ ታገኛለህ።

5በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤

በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤

6በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤

እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።3፥6 ወይም ጐዳናህን ያቀናልሃል

7በራስህ አስተያየት ጠቢብ ነኝ አትበል፤

እግዚአብሔርን ፍራ፤ ከክፉም ራቅ።

8ይህም ለሰውነትህ ጤንነትን፣

ለዐጥንትህም ልምላሜን ያመጣልሃል።

9እግዚአብሔርን በሀብትህ፣

ከምርትህ ሁሉ በኵራት አክብረው፤

10ይህን ብታደርግ፣ ጎተራህ ሞልቶ ይትረፈረፋል፤

መጥመቂያህም በአዲስ የወይን ጠጅ ቲፍ ብሎ ይሞላል።

11ልጄ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤

በዘለፋውም አትመረር፤

12አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ3፥12 ወይም እንደሚገሥጽ ሁሉ፣

እግዚአብሔርም የሚወደውን ይገሥጻልና።

13ጥበብን የሚያገኛት፣

ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርጋት ሰው ቡሩክ ነው፤

14እርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣

ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና።

15ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤

አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።

16በቀኝ እጇ ረጅም ዕድሜ አለ፤

በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች።

17መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤

ጐዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።

18ለሚያቅፏት የሕይወት ዛፍ ናት፤

የሚይዟትም ይባረካሉ።

19እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤

በማስተዋል ሰማያትን በየስፍራቸው አጸና፤

20በዕውቀቱ ቀላያት ተከፈሉ፤

ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ።

21ልጄ ሆይ፤ ትክክለኛ ፍርድንና አስተውሎ መለየትን ጠብቅ፤

እነዚህ ከእይታህ አይራቁ፤

22ለነፍስህ ሕይወት፣

ለዐንገትህም ጌጥ ይሆናሉ።

23ከዚያም መንገድህን በሰላም ትሄዳለህ፤

እግርህም አይሰናከልም፤

24ስትተኛ አትፈራም፤

ትተኛለህ እንቅልፍህም ጣፋጭ ይሆናል።

25ድንገተኛን መከራ፣

በክፉዎች ላይ የሚደርሰውንም ጥፋት አትፍራ፤

26እግዚአብሔር መታመኛህ ይሆናልና፤

እግርህንም በወጥመድ ከመያዝ ይጠብቃል።

27ማድረግ እየቻልህ

ለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ አትቈጠብ።

28አሁን በእጅህ እያለ፣

ጎረቤትህን፣ “ቈይተህ ተመለስ፤ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው።

29አንተን ተማምኖ በአጠገብህ በተቀመጠ፣

በጎረቤትህ ላይ ክፉ አትምከርበት።

30ምንም ጒዳት ሳያደርስብህ፣

ያለ ምክንያት ሰውን አትክሰስ።

31በክፉ ሰው አትቅና፤

የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ፤

32እግዚአብሔር ጠማማን ሁሉ ይጸየፋልና፤

ለቅን ሰው ግን ምስጢሩን ይገልጥለታል።

33የእግዚአብሔር ርግማን በክፉዎች ቤት ላይ ነው፤

የጻድቃንን ቤት ግን ይባርካል።

34እርሱ በዕቡያን ፌዘኞች ላይ ያፌዛል፤

ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል።

35ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፤

ሞኞችን ግን ለውርደት ያጋልጣቸዋል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

箴言 3:1-35

信靠耶和華

1孩子啊,不要忘記我的訓言,

要把我的誡命存在心裡,

2因為這必使你延年益壽,

幸福平安。

3不要讓慈愛和信實離開你,

要把他們繫在你的頸項上,

刻在你的心坎上。

4這樣,你必蒙上帝和世人的喜悅,

享有美譽。

5你要全心信靠耶和華,

不可倚靠自己的悟性。

6凡事都要尋求祂,

祂必指引你走正路。

7不要自以為有智慧,

要敬畏耶和華,遠離惡事。

8這樣可醫治你的身體,

滋潤你的筋骨。

9你要用自己的財富和一切初熟的物產來尊崇耶和華,

10祂必使你五穀滿倉,

榨酒池溢出新釀。

11孩子啊,不可輕視耶和華的管教,

也不可厭煩祂的責備。

12因為耶和華責備祂所愛的人,

就像父親責備他所疼愛的孩子。

13找到智慧、得到悟性的人有福了,

14因為智慧比銀子更有價值,

比金子更有益處,

15比珠寶更珍貴;

你所喜愛的一切都難以相比。

16智慧的右手有長壽,

左手有富貴和尊榮。

17她的路上有福樂,

她的道上有平安。

18對持守智慧的人來說,

智慧是生命樹,

緊握智慧的人必蒙祝福。

19耶和華以智慧奠立大地,

以悟性鋪設諸天;

20祂的知識使深淵裂開,

使天上降下甘霖。

21孩子啊,你要守護智慧和明辨力,

別讓她們離開你的視線。

22她們必給你帶來生命,

作你頸項上華美的裝飾。

23如此,你必步履穩健,不致失足;

24你必安然躺臥,睡得香甜。

25不要怕突來的災禍,

不要怕惡人遭毀滅,

26因為耶和華是你的靠山,

祂使你的腳不陷入網羅。

27倘若有力量行善,

就當幫助有需要的人,不要推託。

28倘若可以幫忙,

就不可對有求於你的鄰人說:

「回去吧,明天再來,我必給你!」

29鄰舍在你附近安分居住,

不可謀害他。

30別人若沒有害你,

不要無故與他相爭。

31不要羡慕殘暴之徒,

也不可步其後塵,

32因為耶和華憎惡邪僻之徒,

喜愛正直的人。

33耶和華咒詛惡人的家,

賜福義人的家。

34耶和華譏笑好譏誚的人,

恩待謙卑的人。

35智者得尊榮,

愚人受羞辱。