New Amharic Standard Version

ምሳሌ 29:1-27

1ከብዙ ተግሣጽ በኋላ ዐንገቱን የሚያደነድን ሰው፣

በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።

2ጻድቃን ሥልጣን ሲይዙ ሕዝብ ሐሤት ያደርጋል፤

ክፉዎች ሲገዙ ግን ሕዝብ ያቃስታል።

3ጥበብን የሚወድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤

የአመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል።

4ፍትሕን በማስፈን ንጉሥ አገርን ያረጋጋል፤

ጒቦ ለማግኘት የሚጐመጅ ግን ያፈራርሳታል።

5ባልንጀራውን የሚሸነግል፣

ለገዛ እግሩ መረብ ይዘረጋል።

6ክፉ ሰው በራሱ ኀጢአት ይጠመዳል፤

ጻድቅ ግን ይዘምራል፤ ደስም ይለዋል።

7ጻድቅ ለድኾች ፍትሕ ይጨነቃል፤

ክፉ ሰው ግን ደንታ የለውም።

8ተሳዳቢዎች ከተማን ያውካሉ፤

ጠቢባን ግን ቊጣን ያበርዳሉ።

9ጠቢብ ሰው ከተላላ ጋር ወደ ሸንጎ ቢሄድ፣

ተላላ ይቈጣል፤ ያፌዛል፤ ሰላምም አይኖርም።

10ደም የተጠሙ ሰዎች ሐቀኛን ሰው ይጠላሉ፤

ቅን የሆነውንም ለመግደል ይሻሉ።

11ተላላ ሰው ቊጣውን ያለ ገደብ ይለቀዋል፤

ጠቢብ ሰው ግን ራሱን ይቈጣጠራል።

12ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣

ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።

13ድኻውና ጨቋኙ የጋራ ነገር አላቸው፤

እግዚአብሔር ለሁለቱም የዐይን ብርሃንን ሰጥቶአቸዋል።

14ንጉሥ ለድኻ ትክክለኛ ፍርድ ቢሰጥ፣

ዙፋኑ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

15የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤

መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።

16ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ኀጢአት ይበዛል፤

ጻድቃን ግን የእነርሱን ውድቀት ያያሉ።

17ልጅህን ቅጣው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤

ነፍስህንም ደስ ያሰኛታል።

18ራእይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፤

ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው።

19አገልጋይ በቃል ብቻ ሊታረም አይችልም፤

ቢያስተውለውም እንኳ በጀ አይልም።

20በችኰላ የሚናገርን ሰው ታያለህን?

ከእርሱ ይልቅ ተላላ ተስፋ አለው።

21ሰው አገልጋዩን ከልጅነቱ ጀምሮ ቢያቀማጥል፣

የኋላ ኋላ ሐዘን29፥21 በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጓሜ በእርግጠኝነት አይታወቅም ያገኘዋል።

22ቊጡ ሰው ጠብን ይጭራል፤

ግልፍተኛም ብዙ ኀጢአት ይሠራል።

23ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብርን

ይጐናጸፋል።

24የሌባ ግብረ አበር የገዛ ራሱ ጠላት ነው፤

የመሐላውን ርግማን እየሰማ ጭጭ ይላል።

25ሰውን መፍራት ወጥመድ ነው፤

በእግዚአብሔር የሚታመን ግን በሰላም ይኖራል።

26ብዙዎች በገዥ ፊት ተደማጭነት ማግኘት ይሻሉ፤

ሰው ፍትሕ የሚያገኘው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

27ጻድቃን አታላዮችን ይጸየፋሉ፤

ክፉዎችም ቅኖችን ይጠላሉ።

Japanese Contemporary Bible

箴言 知恵の泉 29:1-27

29

1何度しかられても言うことを聞かない者は、

突然倒れて二度と立ち直れません。

2正しい人が治めると国民は喜び、

悪者が権力を握ると嘆きます。

3知恵のある子は父親を幸せにしますが、

悪い女とつき合う者は財産を使い果たして、

親に恥をかかせます。

4正しいことをする王は国をしっかり治め、

わいろを要求する王は国を滅ぼします。

5-6調子のいいお世辞は罠です。

悪人はそれに足をとられて転びますが、

正しい人は近寄ろうともしないので安全です。

7正しい人は貧しい人の権利も認めますが、

神を信じない者は気にもかけません。

8愚か者はけんかの種をまき散らし、

知恵のある人は事を丸く収めます。

9愚か者と言い争っても無駄です。

相手はかっとなり、感情をむき出しにして、

こちらをさげすむだけです。

10神を恐れる人は、

いのちをつけねらう者のためにも祈ります。

11神に逆らう者は頭にくるとすぐにどなり、

知恵のある人はじっと我慢します。

12悪い指導者の回りには、悪い部下が集まるものです。

13金持ちも貧しい人も、

主の前では全く同じように太陽の恵みを受けます。

14貧しい人を差別せずに正しく裁く王は、

長く国を治めます。

15子どもは、しかられ懲らしめられることで、

何が悪いことなのかを知ります。

わがままいっぱいに育てると、

あとで母親が恥をかきます。

16支配者が悪いと国民も悪くなりますが、

正しい人は必ず彼らの滅びを見届けます。

17子どもをきびしくしつければ、

老後は幸せに過ごせます。

18神を知らない民は好き勝手に振る舞い、

手がつけられませんが、

国中の人が神の教えを守ろうとする国は幸いです。

19右から左に聞き流す者は、しかるだけでなく、

懲らしめなければ言うことを聞きません。

20短気な者に比べたら、愚か者のほうがまだましです。

21使用人を子どものころから甘やかすと、

息子のように大きな顔をするようになります。

22短気な者は争いの種をまき散らし、

いつもめんどうに巻き込まれます。

23自分を鼻にかけすぎるとたたかれ、

謙遜にしているとほめられます。

24悪いとわかっていながら、どろぼうに手を貸す者は、

いつかは自分にいや気がさします。

25人を恐れることは危険な罠ですが、

主に頼れば安心です。

26正しい裁判をしてほしかったら、

裁判官に取り入ろうとせず、主に任せなさい。

27正しい人は悪者のすることが、

悪者は正しい人のすることが大きらいです。