New Amharic Standard Version

ምሳሌ 26:1-28

1በረዶ በበጋ፣ ዝናብ በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉ፣

ክብርም ለተላላ አይገባውም።

2ክንፎቿን እንደምታርገበግብ ድንቢጥ ወይም ቱር እንደምትል ጨረባ፣

ከንቱ ርግማንም በማንም ላይ አይደርስም።

3ለፈረስ አለንጋ፣ ለአህያ መሸበቢያ፣

ለተላላ ጀርባም በትር ይገባዋል።

4ቂልን እንደ ቂልነቱ አትመልስለት፤

አለዚያ አንተም ራስህ እንደ እርሱ ትሆናለህ።

5ቂልን እንደ ቂልነቱ መልስለት፤

አለዚያ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል።

6በተላላ እጅ መልእክትን መላክ፣

የገዛ እግርን እንደ መቊረጥ ወይም ዐመፃን እንደ መጋት ነው።

7በቂል አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣

ሰላላ የሽባ ሰው እግር ነው።

8ለተላላ ክብር መስጠት፣

በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።

9በአላዋቂ አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣

በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው።

10ቂልን ወይም የትኛውንም ዐላፊ አግዳሚ የሚቀጥር፣

ፍላጻውን በነሲብ እየወረወረ ወገኖቹን እንደሚያቈስል ቀስተኛ ነው።

11ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ሁሉ፣

ተላላም ቂልነቱን ይደጋግማል።

12ራሱን እንደ ጠቢብ የሚቈጥረውን ሰው አይተሃልን?

ከእርሱ ይልቅ ለተላላ ተስፋ አለው።

13ሰነፍ፣ “በመንገድ ላይ አንበሳ አለ፤

አስፈሪ አንበሳ በአውራ ጐዳና ላይ ይጐማለላል” ይላል።

14መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣

ሰነፍም በዐልጋው ላይ ይገላበጣል።

15ሰነፍ እጁን ወጭት ውስጥ ያጠልቃል፤

ወደ አፉ ለመመለስ ግን እጅግ ይታክታል።

16በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ከሰባት ሰዎች ይልቅ፣

ሰነፍ ራሱን ጠቢብ አድርጎ ይቈጥራል።

17በሌሎች ጠብ ጥልቅ የሚል መንገደኛ፣

የውሻ ጆሮ እንደሚይዝ ሰው ነው።

18ትንታግ ወይም የሚገድል ፍላጻ እንደሚወረውር ዕብድ፣

19“ቀልዴን እኮ ነው” እያለ

ባልንጀራውን የሚያታልል ሰውም እንደዚሁ ነው።

20ዕንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤

አሾክሻኪ ከሌለም ጠብ ይበርዳል።

21ከሰል ፍምን፣ ዕንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣

አዋኪ ሰውም ጠብን ያባብሳል።

22የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጒርሻ ነው፤

ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል።

23ክፋትን በልብ ቋጥሮ ለስላሳ ቃል የሚናገር ከንፈር፣

በብር ፈሳሽ26፥23 ወይም በሚያብለጨልጭ ነገር እንደ ተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው።

24ተንኰለኛ በከንፈሩ ይሸነግላል፤

በልቡ ግን ክፋትን ይቋጥራል።

25ንግግሩ ማራኪ ቢሆንም አትመነው፤

ሰባት ርኵሰት ልቡን ሞልቶታልና።

26ተንኰሉ በሽንገላው ይሸፈን ይሆናል፤

ነገር ግን ክፋቱ በጉባኤ ይገለጣል።

27ጒድጓድ የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤

ድንጋይ የሚያንከባልልም ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል።

28ሐሰተኛ ምላስ የጐዳቻቸውን ትጠላለች፤

ሸንጋይ አንደበትም ጥፋትን ታመጣለች።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

箴言 26:1-28

1愚人得尊榮本不合宜,

如夏天降雪、收割時下雨。

2麻雀翻飛,燕子翱翔,

咒詛不會無端降臨。

3鞭子打馬,韁繩勒驢,

棍棒責打愚人的背。

4別照愚人的愚昧回答他,

免得你像他一樣。

5要照愚人的愚昧回答他,

免得他自以為有智慧。

6靠愚人傳信,

如同砍斷自己的腳,

自討苦吃。

7愚人口中說箴言,

如同跛子空有腿。

8把尊榮給愚人,

就像把石子綁在甩石器上。

9愚人口中說箴言,

如同醉漢握荊棘。

10雇用愚人或路人,

如同弓箭手亂箭傷人。

11愚人一再重複愚昧事,

就像狗回頭吃所吐的。

12自以為有智慧的人,

還不如愚人有希望。

13懶惰人說:「路上有獅子,

街上有猛獅。」

14懶惰人賴在床上滾來滾去,

就像門在門軸上轉來轉去。

15懶惰人手放在餐盤,

卻懶得送食物進嘴。

16懶惰人自以為比七個善於應對的人更有智慧。

17插手他人的糾紛,

猶如揪狗的耳朵。

18-19欺騙鄰舍還說是開玩笑,

如同瘋子亂拋火把、亂射箭。

20沒有木柴,火自然熄滅;

沒有閒話,爭端便平息。

21好鬥之人煽動爭端,

如同餘火加炭、火上加柴。

22閒言閒語如可口的美食,

輕易進入人的五臟六腑。

23火熱的嘴,邪惡的心,

猶如瓦器鍍了層銀。

24怨恨人的用美言掩飾自己,

心中卻藏著詭詐。

25縱然他甜言蜜語,你也不可信他,

因為他心中充滿各種可憎之事。

26雖然他用詭計掩飾怨恨,

他的邪惡必被會眾揭穿。

27挖陷阱的,必自陷其中;

滾石頭的,必自傷己身。

28撒謊的舌恨它所害的人,

諂媚的嘴帶來毀滅。