New Amharic Standard Version

ምሳሌ 25:1-28

የሰሎሞን ተጨማሪ ምሳሌዎች

1እነዚህ የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ሰዎች የቀዷቸው ሌሎች የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፦

2ነገርን መሰወር ለእግዚአብሔር ክብሩ ነው፤

ነገርን ፈልፍሎ ማውጣት ግን ለነገሥታት ክብራቸው ነው።

3ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉ፣

የነገሥታትም ልብ እንደዚሁ አይመረመርም።

4ከብር ዝገትን አስወግድ፤

አንጥረኛውም ንጹሕ ነገር25፥4 ወይም ጽዋ ያገኛል፤

5ክፉን ከንጉሥ ፊት አርቅ፤

ዙፋኑም በጽድቅ ትጸናለች።

6በንጉሥ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤

በታላላቆች መካከል መገኘትም አይመርህ፤

7በትልቅ ሰው ፊት ከሚያዋርድህ፣

ራሱ፣ “ወደዚህ ከፍ በል” ቢልህ ይሻላልና።

በዐይንህ ያየኸውን ሁሉ፣

8ወደ ፍርድ አደባባይ በችኰላ አታውጣው፤25፥7-8 ወይም ዐይንህን የጣልህበት ሰው፣ 8 … አትውጣ

ባልንጀራህ ካሳፈረህ፣

ኋላ ምን ይውጥሃል?

9ስለ ራስህ ጒዳይ ከባልንጀራህ ጋር በምትከራከርበት ጊዜ፣

የሌላውን ሰው ምስጢር አታውጣ፤

10ያለዚያ ይህን የሚሰማ ያሳፍርሃል፤

አንዴ የጠፋውን ስምህንም ፈጽሞ መመለስ አትችልም።

11ባግባቡ የተነገረ ቃል፣

በብር መደብ ላይ እንደ ተቀረጸ የወርቅ እንኮይ ነው።

12የጠቢብ ሰው ዘለፋ ለሚሰማ ጆሮ፣

እንደ ወርቅ ጒትቻ ወይም እንደ ጥሩ የወርቅ ጌጥ ነው።

13በመከር ጊዜ የበረዶ ቅዝቃዜ ለሰስ እንደሚያደርግ ሁሉ፣

ታማኝ መልእክተኛም ለላኩት እንደዚሁ ነው፤

የጌቶቹን መንፈስ ያሳርፋልና።

14የማይለግሰውን ስጦታ እቸራለሁ ብሎ ጒራ የሚነዛ ሰው፣

ዝናብ እንደሌለው ደመናና ነፋስ ነው።

15በትዕግሥት ገዥን ማግባባት ይቻላል፤

ለስላሳ አንደበትም ዐጥንት ይሰብራል።

16ማር ስታገኝ በልክ ብላ፤

ከበዛ ያስመልስሃል።

17ወደ ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ፤

ታሰለቸውና ይጠላሃል።

18በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር፣

እንደ ቈመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ተሳለ ፍላጻ ነው።

19በመከራ ጊዜ በወስላታ ሰው መተማመን፣

በተበላሸ ጥርስና በሰለለ እግር እንደ መታመን ነው።

20ላዘነ ልብ የሚዘምር፣

በብርድ ቀን ልብሱን እንደሚያወልቅ፣

ወይም በሶዳ ላይ እንደ ተጨመረ ሆምጣጤ ነው።

21ጠላትህ ቢራብ አብላው፤

ቢጠማም ውሃ አጠጣው።

22ይህን በማድረግህም፣ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህ፤

እግዚአብሔርም ዋጋህን ይከፍልሃል።

23የሰሜን ነፋስ ዝናብ እንደሚያመጣ ሁሉ፣

ሐሜተኛ ምላስም ቊጡ ፊት ታስከትላለች።

24ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር፣

በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።

25ከሩቅ የሚመጣ መልካም ዜና፣

የተጠማችን ነፍስ እንደሚያረካ ቀዝቃዛ ውሃ ነው።

26ለክፉ ሰው የሚንበረከክ ጻድቅ፣

እንደ ደፈረሰ ምንጭ ወይም እንደ ተበከለ የጒድጓድ ውሃ ነው።

27ከመጠን በላይ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤

የራስንም ክብር መሻት አያስከብርም።

28ራሱን የማይቈጣጠር ሰው፣

ቅጥሯ እንደ ፈረሰ ከተማ ነው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

箴言 25:1-28

所羅門的箴言(續)

1以下也是所羅門的箴言,由猶大希西迦的人抄錄。

2將事隱藏是上帝的榮耀,

把事查明是君王的光榮。

3天之高,地之厚,

君王的心測不透。

4除掉銀子裡的渣滓,

銀匠就能鑄造器皿。

5清除君王身邊的惡人,

王位必因公義而鞏固。

6不可在王面前妄自尊大,

不要佔據大人物的位子。

7與其在權貴面前受羞辱,

不如等人邀請你坐上座。

8不可魯莽地打官司,

以免敗訴、羞愧難當。

9遇到跟鄰舍爭訟,

不可洩露其秘密,

10免得聽見的人辱罵你,

你的惡名將永難洗刷。

11一句話說得合宜,

就像金蘋果放在銀器裡。

12對受教者而言,

智者的責備猶如金耳環和金飾物。

13忠信的使者叫主人心裡舒暢,

就像夏收之時有冰雪的涼氣。

14誇口送禮物卻食言的人,

就像沒有雨水的風和雲。

15堅忍說服君王,

柔舌折斷骨頭。

16找到蜂蜜要酌量而食,

免得吃多了嘔吐。

17不要頻頻去鄰舍家,

免得惹人煩、遭人厭。

18作偽證陷害鄰舍的人,

無異於大錘、刀和利箭。

19危難時投靠奸詐之人,

形同倚靠壞牙和跛腳。

20對憂傷的人唱歌,

如同天寒脫衣、傷口撒鹽。

21你的仇敵若餓了,

就給他吃的;

若渴了,就給他水喝;

22因為你這是把炭火堆在他頭上,

耶和華必獎賞你。

23北風帶來雨水,

讒言激起憤怒。

24寧願住在屋頂的一角,

不跟爭鬧的妻子同屋。

25有好消息從遠方傳來,

如涼水滋潤乾渴的人。

26義人向惡人低頭,

就像清泉被攪渾,

水井受污染。

27蜂蜜吃得太多有害無益,

追求自己的榮耀也不光彩。

28無法自制的人就像被攻破的無牆之城。