ምሳሌ 10 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ምሳሌ 10:1-32

የሰሎሞን ምሳሌዎች

1የሰሎሞን ምሳሌዎች፤

ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤

ተላላ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።

2ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤

ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።

3እግዚአብሔር ጻድቁ እንዲራብ አያደርግም፤

የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል።

4ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤

ትጉህ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ።

5ሰብሉን በበጋ የሚሰበስብ ጠቢብ ልጅ ነው፤

በመከር ጊዜ የሚተኛ ግን ውርደት ይከተለዋል።

6በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው፤

መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል።10፥6 ወይም የክፉዎች አፍ ግን መዓትን ይሰውራል፤ እንዲሁም 11 ይመ።

7የጻድቃን መታሰቢያቸው በረከት ነው፤

የክፉዎች ስም ግን እንደ ጠፋ ይቀራል።

8በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝ ይቀበላል፤

ለፍላፊ ተላላ ግን ወደ ጥፋት ያመራል።

9ሐቀኛ ሰው ያለ ሥጋት ይራመዳል፤

በጠማማ ጐዳና የሚሄድ ግን ይጋለጣል።

10በተንኰለኛ ዐይን የሚጠቅስ ሐዘን ያስከትላል፤

ለፍላፊ ተላላም ወደ ጥፋት ያመራል።

11የጻድቅ አንደበት የሕይወት ምንጭ ናት፤

መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል።

12ጥላቻ ጠብን ያነሣሣል፤

ፍቅር ግን ስሕተትን ሁሉ ይሸፍናል።

13ጥበብ በአስተዋይ ሰው ከንፈር ትገኛለች፤

በትር ግን ማመዛዘን ለጐደለው ሰው ጀርባ ነው።

14ጠቢባን ዕውቀት ያከማቻሉ፤

የተላላ አንደበት ግን ጥፋትን ይጋብዛል።

15የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤

ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት።

16የጻድቃን ደመወዝ ሕይወት ታስገኝላቸዋለች፤

የክፉዎች ትርፍ ግን ቅጣትን ታመጣባቸዋለች።

17ተግሣጽን ነቅቶ የሚጠብቅ የሕይወትን መንገድ ያሳያል፤

ዕርምትን የማይቀበል ግን ሌሎችን ወደ ስሕተት ይመራል።

18ጥላቻውን የሚሸሽግ ሐሰተኛ አንደበት ያለው ነው፤

ሐሜትን የሚዘራ ሁሉ ተላላ ነው።

19ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤

አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው።

20የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤

የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም።

21የጻድቃን ከንፈሮች ብዙዎችን ያንጻሉ፤

ተላሎች ግን ከማመዛዘን ጕድለት ይሞታሉ።

22የእግዚአብሔር በረከት ብልጽግናን ታመጣለች፤

መከራንም አያክልባትም።

23ተላላ ሰው በክፉ ተግባር ይደሰታል፤

አስተዋይ ሰው ግን በጥበብ ደስ ይለዋል።

24ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤

ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል።

25ዐውሎ ነፋስ ሲነሣ ክፉዎች ተጠራርገው ይወሰዳሉ፤

ጻድቃን ግን ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ።

26ሆምጣጤ ጥርስን፣ ጢስ ዐይንን እንደሚጐዳ፣

ሰነፍም ለሚልኩት እንዲሁ ነው።

27እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤

የክፉዎች ዕድሜ ግን በዐጭር ይቀጫል።

28የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤

የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል።

29የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን መጠጊያ፣

ክፉ ለሚያደርጉ ግን መጥፊያቸው ነው።

30ጻድቃን ፈጽሞ አይነቀሉም፤

ክፉዎች ግን በምድር አይኖሩም።

31የጻድቃን አንደበት ጥበብን ያፈልቃል፤

ጠማማ ምላስ ግን ትቈረጣለች።

32የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢውን ነገር ያውቃሉ፤

የክፉዎች አንደበት ግን የሚያውቀው ጠማማውን ብቻ ነው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

箴言 10:1-32

所罗门的箴言

1以下是所罗门的箴言:

智慧儿使父亲快乐,

愚昧儿叫母亲担忧。

2不义之财毫无益处,

公义救人脱离死亡。

3耶和华不让义人挨饿,

祂使恶人的奢望成空。

4游手好闲招致贫穷,

勤奋努力带来富足。

5精明儿夏季时贮藏,

不肖子收成时酣睡。

6祝福临到义人的头,

残暴充满恶人的口。

7义人流芳于世,

恶人名声朽烂。

8心存智慧的接受诫命;

说话愚昧的自招灭亡。

9行正道者活得安稳,

走歪路者终必败露。

10挤眉弄眼,带来忧伤;

胡言乱语,导致灭亡。

11义人的口是生命之泉,

恶人的口却充满残暴。

12恨能挑起各样纷争,

爱能遮掩一切过犯。

13明哲人口中有智慧,

无知者背上受鞭打。

14智者储藏知识,

愚人口惹祸端。

15钱财是富人的坚垒,

贫乏带给穷人毁灭。

16义人的报酬是生命,

恶人的果子是惩罚。

17听从教诲的,走生命之路;

拒绝责备的,必步入歧途。

18暗藏仇恨的满口虚谎,

散布流言的愚不可及。

19言多必失,智者慎言。

20义人之舌似纯银,

恶人之心无价值。

21义人的口滋养众人,

愚人因无知而死亡。

22耶和华的祝福使人富足,

祝福中不加任何忧愁10:22 祝福中不加任何忧愁”或译“劳苦无法使其加增”。

23愚人以恶为乐,

哲士喜爱智慧。

24恶人所怕的必临到他,

义人的心愿必得实现。

25暴风扫过,

恶人消逝无踪,

义人永不动摇。

26雇用懒惰人,

如醋倒牙,如烟熏目。

27敬畏耶和华的享长寿,

恶人的寿数必被缩短。

28义人的憧憬带来欢乐,

恶人的希望终必破灭。

29耶和华的道保护正直人,

毁灭作恶之人。

30义人永不动摇,

恶人无处容身。

31义人的口发出智慧,

诡诈的舌必被割掉。

32义人说话得体合宜,

恶人的口胡言乱语。