New Amharic Standard Version

ምሳሌ 1:1-33

መግቢያ፤ የምሳሌዎቹ ዐላማና ጭብጥ

1የእስራኤል ንጉሥ፣ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤

2ጥበብንና ተግሣጽን ለመቀበል፤

ጥልቅ ሐሳብ የሚገልጡ ቃላትን ለማስተዋል፤

3ጽድቅን፣ ፍትሕንና ሚዛናዊ ብያኔን በማድረግ፣

የተገራ ጠቢብ ልቦናን ለማግኘት፤

4ብስለት ለሌላቸው አስተዋይነትን፣

በዕድሜ ለጋ ለሆኑት ዕውቀትንና ልባምነትን ለመስጠት፤

5ጥበበኞች ያድምጡ፤ ትምህርታቸውንም ያዳብሩ፤

አስተዋዮችም መመሪያ ያግኙበት፤

6ይህም የጠቢባንን ምሳሌዎችንና ተምሳሌቶችን፣

አባባሎችንና ዕንቆቅልሾችን ይረዱ ዘንድ ነው።

7እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፤

ተላሎች1፥7 በመጽሐፈ ምሳሌና በብሉይ ኪዳን ሌሎች መጻሕፍት ውስጥ ተላላ የሚለው በተደጋጋሚ ተጽፏል፤ ይህም የሞራል ጒድለትን ያመለክታል። ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።

ጥበብን ገንዘብ ለማድረግ የተሰጠ ምክር

8ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤

የእናትህንም ትምህርት አትተው።

9ለራስህ ሞገስን የሚያጐናጽፍ አክሊል፣

ዐንገትህን የሚያስውብ ድሪ ይሆንልሃል።

10ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣

እሺ አትበላቸው፤

11“ከእኛ ጋር ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤

በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤

12እንደ መቃብር፣ ወደ ጒድጓድ1፥12 በዕብራይስጡ ሲኦል ይላል። እንደሚወርዱ፣

ከነሕይወታቸው እንዳሉ እንዋጣቸው፤

13ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በያይነቱ እናገኛለን፤

ቤቶቻችንንም በዝርፊያ እንሞላለን፤

14ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል፤

የጋራ ቦርሳ ይኖረናልቃ ቢሉህ፣

15ልጄ ሆይ፤ አብረሃቸው አትሂድ፤

በሚሄዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ፤ 16እግራቸው ወደ ኀጢአት ይቸኵላል፤

ደም ለማፍሰስም ፈጣኖች ናቸው።

17ወፎች ፊት እያዩ ወጥመድ መዘርጋት፣

ምንኛ ከንቱ ነው!

18እነዚህ ሰዎች የሚያደቡት በገዛ ደማቸው ላይ ነው፤

የሚሸምቁትም በራሳቸው ላይ ብቻ ነው።

19ያላግባብ ለጥቅም የሚሯሯጡ ሁሉ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤

የሕይወታቸው መጥፊያም ይኸው ነው።

ጥበብን ለሚያናንቁ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

20ጥበብ በጐዳና ላይ ጮኻ ትጣራለች፤

በየአደባባዩ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፤

21ዉካታ በበዛባቸው ጐዳናዎች ላይ1፥21 በዕብራይስጡና በሰብዓ ሊቃናት ትርጒሞች በቅጥሮች ጫፍ ላይ ይላሉ። ትጮኻለች፤

በከተማዪቱም መግቢያ በር ላይ እንዲህ ትላለች፤

22“እናንት ብስለት የሌላችሁ1፥22 በዕብራይስጡ ብስለት የሌለው የሚለው ቃል በዚህ መጽሐፍ በአጠቃላይ መልካም ምግባር የሌለውንና ክፋትን ለማድረግ ልቡ ያዘነበለ ሰውን ያመለክታል። ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወዱታላችሁ?

ፌዘኞች በፌዝ ደስ የሚሰኙት፣

ሞኞችስ ዕውቀትን የሚጠሉት እስከ መቼ ነው?

23ዘለፋዬን ብትሰሙኝ ኖሮ፣

ልቤን ባፈሰስሁላችሁ፣

ሐሳቤንም ባሳወቅኋችሁ ነበር።

24ነገር ግን በተጣራሁ ጊዜ እምቢ ስላላችሁኝ፣

እጄንም ስዘረጋ ማንም ግድ ስላልነበረው፣

25ምክሬን ሁሉ ስለናቃችሁ፣

ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፣

26እኔ ደግሞ በመከራችሁ እሥቅባችኋለሁ፤

መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ፤

27መዓት እንደ ማዕበል ሲያናውጣችሁ፣

መከራም እንደ ዐውሎ ነፋስ ሲጠራርጋችሁ፣

ሥቃይና ችግር ሲያጥለቀልቃችሁ አፌዝባችኋለሁ።

28“በዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤

አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ነገር ግን አያገኙኝም።

29ዕውቀትን ስለ ጠሉ፣

እግዚአብሔርንም መፍራት ስላልመረጡ፣

30ምክሬን ለመቀበል ስላልፈለጉ፣

ዘለፋዬን ስለናቁ፣

31የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤

የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ።

32ብስለት የሌላቸውን ስድነታቸው ይገድላቸዋል፤

ተላሎችንም ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል፤

33የሚያዳምጠኝ ሁሉ ግን በሰላም ይኖራል፤

ክፉን ሳይፈራ ያለ ሥጋት ይቀመጣል።”

Japanese Contemporary Bible

箴言 知恵の泉 1:1-33

1

箴言の目的と主題

1ダビデ王の子、イスラエルの王ソロモンの教え。

2-3ソロモン王がこの教訓を書いたのは、

人々がどんな時にも物事を正しく判断し、

公正であってほしいと考えたからです。

4「未熟な人たちが賢くなってほしい。」

「若い人が正しい生活を送るように注意したい。」

5-6「賢い人には、

これらの知恵のことばの深い真理をもっと探究し、

より賢くなり、

人々を指導できるようになってほしい。」

それが彼の願いでした。

序文――知恵を求め、悪者には警戒しなさい

7-9では、どうしたら賢く

なれるのでしょう。

まず主を信じ、主を大切にすることです。

愚かな人は主の教えをさげすみます。

両親の忠告に従いなさい。

そうすれば、あとになって

人々にほめられるようになります。

10もし悪い仲間が、「われわれの仲間に入れ」

と言っても、きっぱり断りなさい。

11「待ち伏せして人を襲い、

身ぐるみ巻き上げ、殺そう、

12正しい者も悪い者も見境なく。

13盗んだ物はわれわれのものだ。

あらゆる物が!

14さあ、仲間に入れ。山分けしよう」と誘われても、

15決してその誘いにのってはいけません。

そんな者たちには近寄らないようにしなさい。

16彼らは悪いことをするだけが生きがいで、

人殺しは彼らの専売特許なのです。

17鳥は罠が仕掛けられているところを見れば、

近寄りません。

18ところが、彼らは自分で自分を罠にかけているのです。

愚かなことに、罠をかけて

自分のいのちをつけねらっているのです。

19暴力をふるったり人殺しをしたりする者たちは、

みなこうなるのです。

彼らには悲惨な死が待っています。

知恵の勧め

20知恵は町の中で叫んでいます。

21大通りの群衆や法廷の裁判官、

そして国中の人に呼びかけます。

22「愚か者よ、いつまで聞き分けがないのか。

いつまで知恵をさげすみ、素直に真実を認めないのか。

23さあ、わたしの言うことを聞きなさい。

あなたに知恵の霊を注ぎ、賢くしよう。

24わたしは何度も呼んだのに、

あなたがたはそばに来ようともしなかった。

嘆願までしたのに、知らん顔をしていた。

25わたしの忠告にも叱責にも、耳を貸そうとしない。

26あなたがたには、いつか災いが起こる。

そのとき、わたしはあなたがたを笑う。

27災いが嵐のように襲いかかり、

恐れや苦しみに打ちのめされそうになるとき、

28そのときになって助けてくれと言っても、

わたしはあなたがたを助けない。

わたしを懸命に捜しても、もう遅い。

29それはあなたがたが真実から目をそむけ、

主を信頼せず、

30わたしの忠告を聞かずに、

やりたいことをやっていたからだ。

31あなたがたは、その報いを受けなければならない。

自分で選んだ道なのだから、十分苦しみ、

恐ろしい思いをするがいい。

32わたしをきらうとは、全く愚かな人たちだ。

一歩一歩死に近づいているのも知らずに、

いい気になっている。

33しかし、わたしに聞き従う人は、

何の心配もなく、毎日を平和に暮らす。」