New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 7:1-29

በሌሎች ላይ አለመፍረድ

7፥3-5 ተጓ ምብ – ሉቃ 6፥41፡42

1“እንዳይፈረድባችሁ በማንም ሰው ላይ አትፍረዱ፤ 2በምትፈርዱበትም ዐይነት ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል።

3“በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ ሳትመለከት፣ በወንድምህ ዐይን ያለውን ጕድፍ ለምን ታያለህ? 4በዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ ወንድምህን፣ ‘ዐይንህ ውስጥ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ’ ማለት እንዴት ትችላለህ? 5አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።

6“በእግራቸው እንዳይረግጡት፣ ተመልሰውም ነክሰው እንዳይቦጫጭቋችሁ፣ የተቀደሰ ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቈቻችሁንም በእሪያ ፊት አትጣሉ።

ለምኑ፤ ፈልጉ፤ አንኳኩ

7፥7-11 ተጓ ምብ – ሉቃ 11፥9-13

7“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል። 8የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም በሩ ይከፈትለታል።

9“ከእናንት መካከል ልጁ ዳቦ ቢለምነው፣ ድንጋይ የሚሰጥ አባት አለ? 10ወይንም ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጥ ይኖራልን? 11ታዲያ እናንት ክፉዎች ሳላችሁ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፣ የሰማዩ አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካም ስጦታን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም? 12ሌሎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና።

ጠባቡና ሰፊው በር

13“በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። 14ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው።

ሐሰተኛ ነቢያት

15“በውስጣቸው ነጣቂ ተኵላዎች ሆነው ሳሉ የበግ ለምድ ለብሰው መካከላችሁ በመግባት ከሚያሸምቁ ሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ። 16ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ ቍጥቋጦ ወይን፣ ከኵርንችትስ በለስ ይለቀማልን? 17እንዲሁም ጥሩ ዛፍ ሁሉ ጥሩ ፍሬ፣ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል። 18ጥሩ ዛፍ መጥፎ ፍሬ፣ መጥፎም ዛፍ ጥሩ ፍሬ ማፍራት አይችልም። 19ጥሩ ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። 20ስለዚህ በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ።

21“በሰማይ ያለውን ያባቴን ፈቃድ ሳይፈጽም ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም። 22በዚያ ቀን ብዙዎች፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህ አጋንንት አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ታምራት አላደረግንምን?’ ይሉኛል። 23በዚያ ጊዜ፣ ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንት ክፉዎች፤ ከእኔ ራቁ’ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ።

ብልኁና ሞኙ ቤት ሠሪ

7፥24-27 ተጓ ምብ – ሉቃ 6፥47-49

24“እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል። 25ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንን ቤት መታው፤ በዐለት መሠረትም ላይ ስለ ተመሠረተ አልወደቀም። 26ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የማያውለው ግን ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራን ሞኝ ሰው ይመስላል። 27ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንን ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም የከፋ ነበር።”

28ኢየሱስ ማስተማሩን በፈጸመ ጊዜ፣ ሕዝቡ በትምህርቱ ተደነቁ። 29ምክንያቱም እንደ አይሁድ ሃይማኖት መምህራናቸው ሳይሆን እንደ ባለ ሥልጣን አስተምሮአቸው ስለ ነበር ነው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

馬太福音 7:1-29

責人先責己

1「不要論斷別人,免得你們被論斷。 2因為你們怎樣論斷別人,也必照樣被論斷;你們用什麼尺度衡量別人,也要用什麼尺度衡量你們。 3為什麼你只看見你弟兄眼中的小刺,卻看不見自己眼中的大樑呢? 4既然你自己眼中有大樑,又怎麼能對弟兄說『讓我除去你眼中的小刺』呢? 5你這偽君子啊!要先除掉自己眼中的大樑,才能看得清楚,好清除弟兄眼中的小刺。

6「不要把聖物給狗,免得狗轉過頭來咬你們,也不要把珍珠丟在豬前,免得豬踐踏了珍珠。

祈求、尋找、叩門

7「祈求,就會給你們;尋找,就會尋見;叩門,就會給你們開門。 8因為凡祈求的,就得到;尋找的,就尋見;叩門的,就給他開門。

9「你們做父親的,誰會在兒子要餅時給他石頭, 10要魚時給他毒蛇呢? 11你們雖然邪惡,尚且知道把好東西給兒女,你們的天父豈不更要把好東西賜給求祂的人嗎?

12「所以,你們希望人怎樣待你們,就要怎樣待人,這是律法和先知的教導。

辨別與抉擇

13「你們要進窄門,因為通向滅亡的門大,路寬,進去的人也多; 14但通向永生的門小,路窄,找到的人也少。

15「你們要提防假先知,他們披著羊皮到你們當中,骨子裡卻是凶殘的狼。 16你們可以憑他們結的果子認出他們。荊棘怎能結出葡萄呢?蒺藜怎能長出無花果呢? 17同樣,好樹結好果子,壞樹結壞果子; 18好樹結不出壞果子,壞樹也結不出好果子。 19凡不結好果子的樹,都要被砍下來丟在火裡。 20因此,你們可以憑他們結的果子認出他們。 21並不是所有稱呼我『主啊,主啊』的人都能進天國,只有遵行我天父旨意的人才能進去。 22在審判那天,很多人會對我說,『主啊,主啊,我們不是奉你的名傳道,奉你的名趕鬼,奉你的名行了許多神蹟嗎?』 23我會清楚地告訴他們,『我從來不認識你們,你們這些作惡的人走開!』

兩種蓋房子的人

24「所以,凡聽了我的這些話就去行的人,就像聰明人把房子建在磐石上。 25任由風吹雨打、洪水沖擊,房子仍屹立不倒,因為它建基在磐石上。 26凡聽了我這些話不去行的,就像愚昧人把房子建在沙土上。 27遇到風吹雨打、洪水沖擊,房子就倒塌了,而且倒塌得很厲害。」

28大家聽完耶穌這番教導,都很驚奇, 29因為祂教導他們時像位有權柄的人,不像他們的律法教師。