New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 19:1-30

ስለ መፋታት የቀረበ ጥያቄ

19፥1-9 ተጓ ምብ – ማር 10፥1-12

1ኢየሱስ ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ፣ ገሊላን ትቶ ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደ። 2ብዙ ሕዝብም ተከተለው፤ በዚያም ፈወሳቸው።

3ፈሪሳውያንም ሊፈትኑት ቀርበው፣ “ለመሆኑ አንድ ሰው በማንኛውም ምክንያት ሚስቱን መፍታት ተፈቅዶአልን?” ሲሉ ጠየቁት።

4እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸው አላነበባችሁምን? 5እንዲህም አለ፤ ‘ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣመራል፣ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’ የተባለው በዚህ ምክንያት አይደለምን? 6ከእንግዲህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው።”

7እነርሱም፣ “ታዲያ፣ ሙሴ አንድ ወንድ የፍቺውን የምስክር ወረቀት ሰጥቶ ሚስቱን እንዲያሰናብት ለምን አዘዘ?” አሉት።

8ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሴ የልባችሁን ጥንካሬ አይቶ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ፈቀደላችሁ እንጂ ከመጀመሪያው እንዲህ አልነበረም፤ 9እላችኋለሁ፤ በትዳሯ ላይ ዝሙት ፈጽማ እስካልተገኘች ድረስ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ ሴት የሚያገባ ሁሉ አመንዝራ ይሆናል፤ እርሷንም አመንዝራ ያደርጋታል፣ የተፈታችውንም ሴት የሚያገባ ያመነዝራል።”

10ደቀ መዛሙርቱም፣ “የባልና የሚስት ጒዳይ እንዲህ ከሆነ አለማግባት ይሻላል” አሉት።

11ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ከተሰጣቸው በስተቀር ይህንን ትምህርት ማንም ሊቀበል አይችልም፤ 12ምክንያቱም አንዳንዶች ጃንደረባ ሆነው ይወለዳሉ፤ ሌሎች በሰው እጅ ተሰልበው ጃንደረባ ይሆናሉ፤ ደግሞም ለመንግሥተ ሰማይ ሲሉ ራሳቸውን ጃንደረባ የሚያደርጉ አሉ። ይህን መቀበል የሚችል ይቀበል።”

ኢየሱስ ሕፃናትን ባረካቸው

19፥13-15 ተጓ ምብ – ማር 10፥13-16፤ ሉቃ 18፥15-17

13ከዚያም እጆቹን በላያቸው ላይ ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሕፃናትን ወደ እርሱ አቀረቧቸው። ደቀ መዛሙርቱ ግን ሕፃናቱን ያመጡትን ሰዎች ገሠጿቸው።

14ኢየሱስም፣ “ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማይ እንደ እነርሱ ላሉት ናትና” አላቸው። 15እጁንም ከጫነባቸው በኋላ ከዚያ ስፍራ ተነሥቶ ሄደ።

የሀብታሙ ጥያቄ

19፥16-29 ተጓ ምብ – ማር 10፥17-30፤ ሉቃ 18፥18-30

16ከዚያም አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ፤ የዘላለምን ሕይወት አገኝ ዘንድ ምን መልካም ነገር ልሥራ” ሲል ጠየቀው።

17ኢየሱስም፣ “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንዱ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ከፈለግህ ግን ትእዛዛቱን ጠብቅ” አለው።

18ሰውየውም፣ “የትኞቹን ትእዛዛት?” ሲል ጠየቀ።

ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አትግደል፣ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ 19አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ።”

20ጐልማሳውም ሰውየ፣ “እነዚህንማ ጠብቄአለሁ፤ ከዚህ ሌላ የሚጐድለኝ ምን አለ?” አለው።

21ኢየሱስም፣ “ፍጹም ለመሆን ከፈለግህ፣ ሄደህ ንብረትህን ሁሉ ሸጠህ፣ ገንዘቡን ለድኾች ስጥ፤ በሰማይም ሀብት ታገኛለህ። ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው።

22ጐልማሳው ሰውየም ይህን ሲሰማ ብዙ ሀብት ስለ ነበረው እያዘነ ሄደ።

23ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አለ፤ “እውነት እላችኋለሁ፣ ለሀብታም ወደ መንግሥተ ሰማይ መግባት እጅግ አስቸጋሪ ነው። 24ደግሜ እላችኋለሁ፤ ሀብታም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል።”

25ይህን ሲሰሙ፣ ደቀ መዛሙርቱ እጅግ በመገረም፣ “እንግዲያስ ማን ሊድን ይችላል?” ሲሉ ጠየቁ።

26ኢየሱስም እየተመለከታቸው፣ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉም ነገር ይቻላል” አላቸው።

27ጴጥሮስም መልሶ፣ “እኛ ሁሉን ትተን ተከትለንሃል፤ ታዲያ ምን እናገኝ ይሆን?” አለው።

28ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ በሚመጣው አዲስ ዓለም የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም የተከተላችሁኝ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ ትፈርዳላችሁ። 29ስለ ስሜ ብሎ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን19፥29 አንዳንድ ቅጆች እናትን ወይም ሚስትን ይላሉ ፣ ልጆችን ወይም ዕርሻን የሚተው ሁሉ መቶ ዕጥፍ ይቀበላል፤ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። 30ነገር ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች፣ ብዙ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።”

Thai New Contemporary Bible

มัทธิว 19:1-30

การหย่าร้าง

(มก.10:1-12)

1เมื่อพระเยซูตรัสถ้อยคำเหล่านี้จบก็เสด็จจากแคว้นกาลิลีเข้าไปในเขตยูเดียอีกฟากหนึ่งของแม่น้ำจอร์แดน 2ฝูงชนกลุ่มใหญ่ติดตามพระองค์มาและพระองค์ทรงรักษาพวกเขาที่นั่น

3พวกฟาริสีบางคนมาทดสอบพระองค์ พวกเขาทูลถามว่า “ผิดบัญญัติหรือไม่ที่ผู้ชายจะขอหย่าภรรยาเพราะเหตุหนึ่งเหตุใดก็ตาม?”

4พระองค์ทรงตอบว่า “ท่านไม่ได้อ่านหรือที่ว่าในปฐมกาลพระผู้สร้าง ‘ทรงสร้างพวกเขาเป็นผู้ชายและผู้หญิง’19:4 ปฐก.1:27 5และกล่าวว่า ‘เพราะเหตุนี้ผู้ชายจะละจากบิดามารดาของตนไปผูกพันเป็นหนึ่งเดียวกับภรรยาและทั้งสองจะเป็นเนื้อเดียวกัน’?19:5 ปฐก.2:24 6ดังนั้นเขาจึงไม่ได้เป็นสองอีกต่อไปแต่เป็นหนึ่งเดียว ฉะนั้นที่พระเจ้าทรงผูกพันเข้าด้วยกันแล้วอย่าให้มนุษย์มาพรากจากกันเลย”

7พวกเขาทูลว่า “ก็แล้วทำไมโมเสสสั่งให้ผู้ชายทำหนังสือหย่าและให้ภรรยาไปได้?”

8พระเยซูตรัสว่า “โมเสสอนุญาตให้ท่านหย่าภรรยาของท่านเพราะใจของท่านทั้งหลายแข็งกระด้าง แต่ไม่ได้เป็นเช่นนี้ตั้งแต่ต้น 9เราบอกท่านว่าผู้ใดหย่าภรรยาของตนด้วยเหตุอื่นๆ ยกเว้นการผิดศีลธรรมทางเพศ แล้วไปแต่งงานกับหญิงอื่น ชายผู้นั้นก็ล่วงประเวณี”

10เหล่าสาวกทูลว่า “ถ้าสภาพระหว่างสามีและภรรยาเป็นอย่างนี้ก็อย่าแต่งงานเลยดีกว่า”

11พระเยซูทรงตอบว่า “ไม่ใช่ทุกคนที่รับข้อนี้ได้เว้นแต่บรรดาผู้ที่ประทานให้ 12เพราะบางคนก็เกิดมาเป็นขันที บางคนก็ถูกมนุษย์ทำให้เป็นเช่นนั้น และที่ครองตัวเป็นโสด19:12 หรือได้ทำตัวเป็นขันทีเพื่ออาณาจักรสวรรค์ก็มี ใครยอมรับเช่นนี้ได้ก็จงรับเถิด”

พระเยซูกับเด็กเล็กๆ

(มก.10:13-16; ลก.18:15-17)

13แล้วมีผู้พาเด็กเล็กๆ มาหาพระเยซูเพื่อให้วางพระหัตถ์และอธิษฐานเผื่อ แต่เหล่าสาวกตำหนิผู้ที่พาเด็กๆ มา

14พระเยซูตรัสว่า “จงให้เด็กเล็กๆ มาหาเรา อย่าขัดขวางเขาเลย เพราะอาณาจักรสวรรค์เป็นของคนที่เป็นเหมือนเด็กเหล่านี้” 15เมื่อพระองค์ทรงวางพระหัตถ์บนพวกเขาแล้วก็เสด็จไปจากที่นั่น

เศรษฐีหนุ่ม

(มก.10:17-30; ลก.18:18-30)

16ชายคนหนึ่งมาทูลถามพระเยซูว่า “ท่านอาจารย์ ข้าพเจ้าจะต้องทำดีอะไรบ้างจึงจะได้ชีวิตนิรันดร์?”

17พระเยซูทรงตอบว่า “เหตุใดท่านจึงมาถามเราว่าอะไรดี? มีอยู่เพียงผู้เดียวที่ดี หากท่านปรารถนาจะเข้าสู่ชีวิต จงเชื่อฟังบทบัญญัติ”

18เขาทูลว่า “ข้อไหนบ้าง?”

พระเยซูตรัสว่า “ ‘อย่าฆ่าคน อย่าล่วงประเวณีอย่าลักขโมย อย่าเป็นพยานเท็จ 19จงให้เกียรติบิดามารดาของเจ้า’19:19 อพย.20:12-16ฉธบ.5:16-20 และ ‘จงรักเพื่อนบ้านเหมือนรักตนเอง’19:19 ลนต.19:18

20ชายหนุ่มคนนั้นทูลว่า “ทุกข้อเหล่านี้ข้าพเจ้าถือรักษามาตลอด ยังขาดอะไรอีกบ้าง?”

21พระเยซูตรัสตอบว่า “หากท่านปรารถนาจะเป็นคนดีพร้อม จงไปขายทุกสิ่งที่มีและแจกจ่ายให้คนยากจนแล้วท่านจะมีทรัพย์สมบัติในสวรรค์ จากนั้นจงตามเรามา”

22เมื่อชายหนุ่มได้ยินเช่นนั้นก็จากไปด้วยความเศร้าเพราะเขาร่ำรวยมาก

23แล้วพระเยซูตรัสกับเหล่าสาวกของพระองค์ว่า “เราบอกความจริงแก่ท่านว่าเป็นการยากที่คนรวยจะเข้าอาณาจักรสวรรค์ 24เราบอกอีกว่าให้อูฐลอดรูเข็มก็ยังง่ายกว่าที่คนรวยจะเข้าในอาณาจักรของพระเจ้า”

25เมื่อเหล่าสาวกได้ยินเช่นนั้นก็ประหลาดใจนักจึงทูลถามว่า “ถ้าเช่นนั้นใครจะรอดได้?”

26พระเยซูทรงมองดูพวกเขาและตรัสว่า “สำหรับมนุษย์ก็เป็นไปไม่ได้ แต่สำหรับพระเจ้าทุกสิ่งเป็นไปได้”

27เปโตรทูลตอบพระองค์ว่า “ข้าพระองค์ทั้งหลายได้ละทิ้งทุกสิ่งมาติดตามพระองค์! แล้วข้าพระองค์ทั้งหลายจะได้อะไรบ้าง?”

28พระเยซูตรัสแก่พวกเขาว่า “เราบอกความจริงแก่ท่านว่าขณะที่ทุกสิ่งถูกสร้างขึ้นใหม่เมื่อบุตรมนุษย์ประทับบนบัลลังก์อันรุ่งเรืองของพระองค์ พวกท่านที่ตามเรามาก็จะนั่งบนบัลลังก์ทั้งสิบสองพิพากษาชนอิสราเอลสิบสองเผ่าด้วย 29และทุกคนที่ละทิ้งบ้าน พี่น้องชายหญิง หรือบิดามารดา19:29 สำเนาต้นฉบับบางสำเนาว่ามารดาหรือภรรยา หรือลูก หรือไร่นาเพราะเห็นแก่เราจะได้รับการตอบแทนร้อยเท่าและจะได้ชีวิตนิรันดร์ 30แต่หลายคนที่เป็นคนต้นจะเป็นคนสุดท้ายและหลายคนที่เป็นคนสุดท้ายจะเป็นคนต้น