New Amharic Standard Version

ማሕልየ መሓልይ 8:1-14

1ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ፣

እንደ ወንድሜ በሆንህ!

ከዚያም ውጭ ባገኝህ፣

እስምህ ነበር፤

ታዲያ ማንም ባልናቀኝ!

2እኔም ወደ አስተማረችኝ፣

ወደ እናቴም ቤት፣

እጅህን ይዤ በወሰድሁህ ነበር፤

የምትጠጣውን ጣፋጭ የወይን ጠጅ፣

የሮማኔን ጭማቂም በሰጠሁህ።

3ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤

ቀኝ እጁም ዐቅፎኛል።

4እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤

ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣

ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት እማጠናችኋለሁ።

ባልንጀሮቿ

5ውዷን ተደግፋ፣

ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት?

ሙሽራዪቱ

ከእንኰይ ዛፍ ሥር አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ ፀነሰችህ፤

በዚያም ታምጥ የነበረችው አንተን

ወለደችህ።

6በልብህ እንዳለ፣

በክንድህም እንደምትይዘው ማኅተም አስቀምጠኝ፤

ፍቅር እንደ ሞት የበረታች፣

ቅናቷም8፥6 ወይም ጥልቅ ስሜት እንደ መቃብር8፥6 ዕብራይስጡ ሲኦል ይለዋል ጨካኝ ናትና፤

እንደሚንቦገቦግ እሳት፣

እንደ ኀይለኛም ነበልባል ትነዳለች።8፥6 ወይም እንደ እግዚአብሔም ነበልባል

7የውሃ ብዛት ፍቅርን ሊያጠፋ አይችልም፣

ፈሳሾችም አያሰጥሟትም፤

ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ

ስለ ፍቅር ቢሰጥ

ፈጽሞ ይናቃል።

ባልንጀሮቿ

8ትንሽ እኅት አለችን፤

ጡትም ገና አላወጣችም፤

ስለ እርሷ በምንጠየቅበት ቀን

ምን ማድረግ እንችል ይሆን?

9እርሷ ቅጥር ብትሆን፣

በላይዋ የብር መጠበቂያ ማማ እንሠራባታለን፤

በር ብትሆን፣

በዝግባ ዕንጨት እንከልላታለን።

ሙሽራዪቱ

10እነሆ እኔ ቅጥር ነኝ፤

ጡቶቼም እንደ ማማ ግንቦች ናቸው፤

እኔም በዐይኖቹ ፊት፣

ሰላምን እንደሚያመጣ ሰው ሆንሁ።

11ሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤

የወይኑን ተክል ቦታም ለአትክልተኞች አከራየው፤

እያንዳንዳቸውም የፍሬውን ዋጋ፣

አንድ አንድ ሺህ ሰቅል ብር ያመጡለት ነበር።

12የወይኔ ተክል ቦታ የራሴ፣ የግሌ ነው፤

ሰሎሞን ሆይ፤ አንድ ሺሁ ሰቅል ለአንተ፤

ፍሬውን ለሚጠብቁ ደግም ሁለት መቶ ይሁን።

ሙሽራው

13አንቺ በአትክልቱ ቦታ የምትኖሪ ሆይ፤

ባልንጀሮቼ ድምፅሽን ይሰማሉ፤

እስቲ እኔም ልስማው።

ሙሽራዪቱ

14ውዴ ሆይ፤ ቶሎ ናልኝ፤

ሚዳቋን፣

ወይም በቅመም ተራራ ላይ የሚዘል፣

የዋልያን ግልገል ምሰል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

雅歌 8:1-14

1如果你是我的同胞兄弟就好了。

這樣,在外頭遇見你,

我也可以親吻你,

沒有人會取笑我。

2我可以把你帶進我母親的家——她教養了我。

我要給你喝石榴汁釀的醇酒。

3你的左手扶著我的頭,

右手緊抱著我。

4耶路撒冷的少女啊,

我懇求你們,

不要叫醒或驚動愛情,

等它自發吧。

耶路撒冷的少女:

5那從曠野上來、靠在良人身旁的是誰呢?

女子:

我在蘋果樹下喚醒你,

你母親在那裡懷你養你,

為你受生產之苦。

6請把我印在你的心上,

刻在你的手臂上,

因為愛情如死亡一般堅固,

嫉妒像陰間一樣殘酷,

它燃起的火焰是燒滅一切的烈火。

7愛情,大水不能熄滅,

江河不能淹沒。

若有人想傾其家財買愛情,

必遭唾棄。

女子的兄長:

8我們有一個小妹,

她的胸脯還沒有發育。

若有人來提親,

我們該怎麼辦?

9她若是牆,

我們要在上面建造銀塔;

她若是門,

我們要用香柏木板圍護她。

女子:

10我是一面牆,

雙乳像城樓,

我在他眼中像找到平安的人。

11所羅門巴力·哈們有一個葡萄園,

他把葡萄園租給農夫,

租金是每人一千塊銀子。

12我的葡萄園,我自己作主。

所羅門啊,你的一千塊銀子自己留著,

二百塊銀子給管果園的人。

男子:

13你這住在園中的人啊,

同伴們都在聆聽你的聲音,

求你讓我也聽見吧!

女子:

14我的良人啊,

願你像香草山上的羚羊和小鹿,

快快來到我身邊!