New Amharic Standard Version

ሚክያስ 1:1-16

1በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፤

2እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ሁላችሁም ስሙ፤

ምድር ሆይ፤ በውስጧም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፤

ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣

ልዑል እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይመሰክርባችኋል።

በሰማርያና በኢየሩሳሌም ላይ የተላለፈ ፍርድ

3እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያ ስፍራው ይመጣል፤

ወርዶም በምድር ከፍታዎች ላይ ይራመዳል።

4ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ፤

ሸለቆዎችም ይሰነጠቃሉ፤

በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፣

በገደል ላይ እንደሚወርድ ፈሳሽ ይሆናሉ።

5ይህ ሁሉ የሚሆነው ስለ ያዕቆብ በደል፣

ስለ እስራኤልም ቤት ኀጢአት ነው።

የያዕቆብ በደል ምንድን ነው?

ሰማርያ አይደለችምን?

የይሁዳስ የኰረብታ መስገጃ ምንድን ነው?

ኢየሩሳሌም አይደለችምን?

6“ስለዚህ ሰማርያን የፍርስራሽ ክምር፣

ወይን የሚተከልባትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤

ድንጋዮቿን ወደ ሸለቆ አወርዳለሁ፤

መሠረቷንም ባዶ አደርጋለሁ።

7ጣዖቶችዋ ሁሉ ይሰባበራሉ፤

ለቤተ መቅደሷ የቀረበው ገጸ በረከት በእሳት ይቃጠላል፤

ምስሎችዋን ሁሉ እደመስሳለሁ፤

ገጸ በረከቷን በዝሙት አዳሪነት እንደ ሰበሰበች ሁሉ፣

አሁንም ገጸ በረከትዋ የዝሙት አዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል።

ልቅሶና ሐዘን

8በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤

ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤

እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤

እንደ ጒጒትም አቃስታለሁ።

9ቊስሏ የማይሽር ነውና፤

ለይሁዳ ተርፎአል፤

እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣

እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሶአል።

10በጌት1፥10 ‘ጌት’ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ‘አውራ’ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው። አታውሩት፤

ከቶም አታልቅሱ1፥10 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ሲስማማ፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጒም ግን ‘በአኮ ላይ አታልቅሱ’ ይላል። ‘በአኮ’ የሚለው የዕብራይስጡ ቃል ‘አለቀሰ’ ከሚለው የዕብራይስጡ ቃል ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው።

በቤትዓፍራ1፥10 ‘ቤት ዓፍራ’ ትርጒሙ ‘የትቢያ ቤት’ ማለት ነው።

በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።

11እናንት በሻፊር1፥11 ‘ሻር’ ትርጒሙ አስደሳች ማለት ነው። የምትኖሩ፣

ዕርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ዕለፉ፤

በጸዓናን1፥11 ‘ጸዓናን’ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ‘ውጣ’ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው። የሚኖሩ

ከዚያ አይወጡም፤

ቤትዔጼል በሐዘን ላይ ናት፤

ለእናንተም መጠጊያ ልትሆን አትችልም።

12ከመከራው መገላገልን በመሻት፣

በማሮት1፥12 ‘ማሮት’ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ‘መራራ’ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው። የሚኖሩ በሥቃይ

ይወራጫሉ፤

እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር፣

ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአልና።

13እናንት በለኪሶ1፥13 ‘ለኪሶ’ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ቡድን ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው። የምትኖሩ፣

ፈረሶችን ከሠረገላው ጋር አያይዙ፤

ለጽዮን ሴት ልጅ፣

የኀጢአት መጀመሪያ እናንት ነበራችሁ፤

የእስራኤል በደል

በእናንተ ዘንድ ተገኝቶአልና።

14ስለዚህ እናንተ ለሞሬሼትጌት፣

ማጫ ትሰጣላችሁ፤

የአክዚብ1፥14 ‘አክዚብ’ ትርጒሙ አታላይ/ማታለል ማለት ነው። ከተማ፣

ለእስራኤል ነገሥታት መታለያ ትሆናለች።

15እናንት በመሪሳ1፥15 ‘መሪሳ’ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ‘ድል አድራጊ’ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ አነባበብ አለው። የምትኖሩ

ድል አድራጊ አመጣባችኋለሁ፤

ያ የእስራኤል ክብር የሆነው

ወደ ዓዶላም ይመጣል።

16ደስ ለምትሰኙባቸው ልጆቻችሁ፣

በሐዘን ራሳችሁን ተላጩ፤

ራሳችሁን እንደ አሞራ ራስ ተመለጡት፤

ከእናንተ በምርኮ ይወሰዳሉና።

Japanese Contemporary Bible

ミカ書 1:1-16

1

1次に述べるのは、ヨタム王、アハズ王、ヒゼキヤ王がユダ王国を治めていた時代に、モレシェテの町に住むミカに伝えられた主からのことばです。それはサマリヤとユダの両国へのことばで、幻によってミカに示されたものです。

2よく聞け。

世界のすべての国々の民よ、耳をすませよ。

主が聖なる神殿の中から、

あなたがたを告発したのだ。

サマリヤとエルサレムに対するさばき

3見よ、主が来ようとしている。

天の王座を離れ、山々の頂の上を歩きながら、

地上に来る。

4山々は、火の中の蝋のように主の足の下で溶け、

丘を流れ落ちる水のように谷へ流れ込む。

5どうしてこんなことが起こっているのか。

イスラエルとユダの罪のせいだ。

どんな罪か。

首都サマリヤとエルサレムを中心に行われている

偶像崇拝と虐待である。

6それゆえ、サマリヤの町は瓦礫の山となり、

開けた野となって、

その通りはぶどうを植えるために掘り返される。

主はその城壁と要塞を壊し、土台をあばき、

その石を下の谷へ流し入れる。

7刻んだ像は一つ残らず粉々に砕かれ、

礼拝者たちの寄進で建てた

きらびやかな偶像の神殿は焼き払われる。

嘆きと悲しみ

8わたしは声をあげて嘆こう。山犬のようにほえ、

夜、泣きながら砂漠を横切る

だちょうのように悲しげに。

はだし、裸で歩こう。

9わたしの民の傷が治せないほど深いからだ。

主はエルサレムを罰しようと、

すでにその門に立っている。

10ガテの町は災いだ。

嘆き悲しむな。

ベテ・レアフラでは、悩み、

恥じてちりの中を転げ回れ。

11シャフィルの民は身ぐるみはがされて、

裸になって恥じたまま、奴隷として引かれて行く。

ツァアナンの民は城壁の外に姿を現そうとしない。

ベテ・エツェルは町の土台ごと一掃される。

12マロテの民は、

これから良い時代になるだろうと望みをかけている。

だが、待ちかまえているのは苦痛だけだ。

主が、今にもエルサレムを打とうとしているからだ。

13急げ、ラキシュの民よ、

一番速い戦車で逃げるのだ。

ユダの町で最初にイスラエルの偶像礼拝の罪に

ならったのは、あなたなのだから。

そして南のすべての町が、

あなたの例にならうようになった。

14ガテのモレシェテに書き送れ。

もう救われる望みはない。

アクジブの町は、できもしない援助を約束して、

イスラエルの王を欺いた。

15マレシャの民よ、あなたは敵の賞品になる。

敵は、「イスラエルの誉れ」である

アドラムにまで侵入する。

16泣け。

子どもたちのために泣き悲しめ。

子どもたちは奪い去られ、二度と会えなくなる。

奴隷として遠くの地へ連れて行かれてしまった。

頭をそって嘆き悲しむがいい。