መዝሙር 9 NASV – 시편 9 KLB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 9:1-20

መዝሙር 99፥0 ምዕ9 መዝ 9 እና 10 በመጀመሪያው የጥንት ቅጅ ላይ አንጓዎቹ ተከታታይ ፊደላት ባሉት የዕብራይስጥ ሆህያት የሚጀምሩ እንዲሁም ጅማሬው ወይም መጨረሻው ትርጒም አዘል የሆነ አንድ ወጥ ግጥም ነበር፤ በሰብዓ ሊቃናት ውስጥ ሁለቱም አንድ መዝሙር ናቸው።

በክፉ ላይ ፍርድ

ለመዘምራን አለቃ፤ በሙትላቤን ቅኝት፤ የዳዊት መዝሙር

1እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤

ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ።

2በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤

ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ።

3ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፣

ተሰነካክለው ከፊትህ ይጠፋሉ፤

4ፍርዴም ጒዳዬም በአንተ እጅ ናቸውና፤

ቅን ፍርድ እየሰጠህ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል።

5ሕዝቦችን ገሠጽህ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤

ስማቸውንም እስከ ወዲያኛው ደመሰስህ።

6ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤

ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤

መታሰቢያቸውም ተደምስሶአል።

7እግዚአብሔር ግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤

መንበሩንም ለፍርድ አጽንቶአል።

8ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤

ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።

9እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤

በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።

10ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።

11በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤

ሥራውንም በሕዝቦች መካከል በግልጽ አውሩ፤

12ደም ተበቃዩ ዐስቦአቸዋልና፤

የጭቍኖችንም ጩኸት አልዘነጋም።

13እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት፤

አይተህም ራራልኝ፤ ከሞት ደጅም አንሥተህ መልሰኝ፤

14ይህን ስታደርግልኝ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ደጅ፣

ምስጋናህን ዐውጃለሁ፤

በማዳንህም ሐሤት አደርጋለሁ።

15አሕዛብ በቈፈሩት ጒድጓድ ገቡ፤

እግራቸውም ራሳቸው በስውር ባስቀመጡት ወጥመድ ተያዘ።

16እግዚአብሔር በትክክለኛ ፍርዱ የታወቀ ነው፤

ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ። ሒጋዮን9፥16 ወይም በተመሥጦ ማሰብ ሴላ

17ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል9፥17 ወይም መቃብር ይወርዳሉ፤

እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ።

18ችግረኞች ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤

የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም።

19እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ ሰውም አያይል፤

አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።

20እግዚአብሔር ሆይ፤ ድንጋጤ አምጣባቸው፤

ሕዝቦች ሰው ከመሆን እንደማያልፉ ይወቁ። ሴላ

Korean Living Bible

시편 9:1-20

하나님의 구원에 대한 찬양

(성가대 지휘자를 따라 ‘아들의 죽음’ 이란 곡조에 맞춰 부른 다윗의 노래)

1여호와여, 내가 마음을 다하여

주를 찬양합니다.

주께서 행하신 놀라운 일을

내가 다 말하겠습니다.

2내가 주 안에서

기뻐하고 즐거워하며

가장 높으신

주의 이름을 찬양하겠습니다.

3주께서 나타나시면

내 원수들이 뒤돌아서다가

넘어져 죽을 것입니다.

4주께서 나를 변호하시며

내가 한 일을 보증하시고

주의 보좌에 앉으셔서

나를 의롭게 심판하셨습니다.

5주께서 이방 나라들을 책망하시며

악인들을 망하게 하시고

그들의 이름을

영원히 지워 버리셨습니다.

6원수들이 멸망하여 영원히 사라지고

그 도시들은 잿더미가 되었으므로

다시는 기억조차

할 수 없게 되었습니다.

7영원히 다스리시는 여호와께서

심판을 위해

자기 보좌를 베푸셨으니

8그가 의롭게 세상을 다스리시고

모든 민족을

공정하게 심판하시리라.

9여호와는 압박당하는 자의

피난처이시며

환난 때에 피할 요새이시다.

10여호와여, 주를 아는 자들은

다 주를 신뢰할 것입니다.

이것은 주를 찾는 자들을

주께서 버리지 않으셨기 때문입니다.

11시온에 계신 여호와를 찬양하라.

그가 행한 일을

온 세상에 선포하라.

12살인자에게 복수하시는 하나님은

고통당하는 자들을 기억하시며

그들의 부르짖음을

외면하시지 않으리라.

13여호와여, 나를 불쌍히 여기소서.

내 원수들이

나에게 주는 고통을 보시고

죽게 된 나를 구하소서.

14그러면 내가

예루살렘 주민 앞에서

주를 찬양할 것이요

주께서 나를 구하신 일을

기뻐할 것입니다.

15이방 나라들은

자기들이 판 함정에

스스로 빠지고

자기들이 쳐 놓은 그물에

자기들의 발이 걸렸구나.

16여호와는 의로운 심판으로

자기를 나타내시고

악인들은

그들이 행한 일로 함정에 빠진다.

17악인들은

9:17 히 ‘스올’지옥으로 가게 되어 있는 법,

이것이 하나님을 잊어버린

모든 민족들의 운명이다.

18가난한 자라고 해서

언제나 무시당하는 것이 아니며

가난한 자의 희망이

영원히 좌절되는 것도 아니다.

19여호와여, 일어나소서!

사람들이 주를

이기지 못하게 하시고

이방 나라들을

주 앞에서 심판하소서.

20여호와여, 그들을 두렵게 하시며

그들은 죽을 수밖에 없는

존재임을 알게 하소서.