መዝሙር 60 NASV – Забур 60 CARS

New Amharic Standard Version

መዝሙር 60:1-12

መዝሙር 60

ከሽንፈት በኋላ የቀረበ ብሔራዊ ጸሎት

60፥5-12 ተጓ ምብ – መዝ 108፥6-13

ለመዘምራን አለቃ፤ “የኪዳን ጽጌረዳ”። በሚለው ቅኝት የሚዘመር፤60፥0 ርእሱ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። በሰሜናዊ ምዕራብ መስጴጦምያና60፥0 ርእሱ የአራማውያን ወይም የሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ነው። በማእከላዊ ሶርያ የሚኖሩትን አራማውያን60፥0 ርእሱ በመካከለኛው ሶርያ የሚገኙት አራማውያንን የሚያመለክት ነው። በወጋቸው ጊዜ፣ ኢዮአብም ተመልሶ በጨው ሸለቆ አሥራ ሁለት ሺህ ኤዶማውያንን በፈጀ ጊዜ፣ ለትምህርት፤ የዳዊት ቅኔ

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ጣልኸን፤ አንኰታኰትኸን፤

ተቈጣኸንም፤ አሁን ግን መልሰህ አብጀን።

2ምድሪቱን አናወጥሃት፤ ፍርክስክስ አደረግሃት፤

ትንገዳገዳለችና ስብራቷን ጠግን።

3ለሕዝብህ አበሳውን አሳየኸው፤

ናላ የሚያዞር የወይን ጠጅ እንድንጠጣም ሰጠኸን።

4ነገር ግን ከቀስት እንዲያመልጡ፣

ለሚፈሩህ ምልክት አቆምህላቸው። ሴላ

5ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣

በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስም ስጠን።

6እግዚአብሔር ከመቅደሱ እንዲህ ሲል ተናገረ፤

“ደስ እያለኝ የሴኬምን ምድር እሸነሽናለሁ፤

የሱኮትን ሸለቆ አከፋፍላለሁ።

7ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤

ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤

ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።

8ሞዓብ የመታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤

በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤

በፍልስጥኤም ላይ በድል እልል እላለሁ።”

9ወደ ተመሸገው ከተማ ማን ያመጣኛል?

ማንስ ወደ ኤዶምያስ ይመራኛል?

10አምላክ ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?

እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰራዊታችን ጋር እኮ አልወጣ አልህ!

11በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤

የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና።

12በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤

ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።

Священное Писание

Забур 60:1-9

Песнь 60

1Дирижёру хора. На струнных инструментах. Песнь Давуда.

2Всевышний, услышь мой крик,

внемли молитве моей!

3С края земли я к Тебе взываю;

сердце моё в унынии.

Возведи меня на скалу, которая мне недоступна,

4ведь Ты – прибежище моё,

крепкая башня от врага.

5Да живу я вечно в храме Твоём

и под кровом крыльев Твоих покоюсь. Пауза

6Всевышний, Ты услышал мои обеты;

Ты дал мне наследие тех, кто боится Твоего имени.

7Умножь дни жизни царя,

продли его годы из поколения в поколение.

8Да восседает он вечно перед Всевышним;

сохрани его Своей милостью и истиной.

9И буду я Твоё имя воспевать всегда,

день за днём исполняя мои обеты.