መዝሙር 51 NASV – Забур 51 CARS

New Amharic Standard Version

መዝሙር 51:1-19

መዝሙር 51

የኀጢአት ኑዛዜ

ለመዘምራን አለቃ፤ ዳዊት ወደ ቤርሳቤህ ከገባ በኋላ፣ ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ፤ የዳዊት መዝሙር።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ መጠን፣

ምሕረት አድርግልኝ፤

እንደ ርኅራኄህም ብዛት፣

መተላለፌን ደምስስ።

2በደሌን ፈጽሞ እጠብልኝ፤

ከኀጢአቴም አንጻኝ።

3እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፤

ኀጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው።

4በውሳኔህ ትክክል፣

በምትሰጠው ፍርድም ንጹሕ ትሆን ዘንድ፣

አንተን፣ በእርግጥ አንተን ብቻ በደልሁ፤

በፊትህም ክፉ ነገር አደረግሁ።

5ስወለድ ጀምሮ በደለኛ፣

ገና እናቴም ስትፀንሰኝ ኀጢአተኛ ነኝ።

6እነሆ፤ እውነትን ከሰው ልብ ትሻለህ፤51፥6 በዕብራይስጡ የዚህ ሐረግ ትርጒም በትክክል አይታወቅም።

ስለዚህ ጥልቅ ጥበብን በውስጤ አስተምረኝ።51፥6 አስተምረህኛል ወይም ትፈልጋለህ ተብሎ መተርጐም ይቻላል።

7በሂሶጵ እርጨኝ፤ እኔም እነጻለሁ፤

እጠበኝ፤ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።

8ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፤

ያደቀቅሃቸው ዐጥንቶቼም ደስ ይበላቸው።

9ፊትህን ከኀጢአቴ መልስ፤

በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።

10አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤

ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።

11ከፊትህ አትጣለኝ፤

ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድ።

12የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፤

በእሽታ መንፈስም ደግፈህ ያዘኝ።

13እኔም ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ፤

ኀጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።

14የድነቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤

ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤

አንደበቴም ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል።

15ጌታ ሆይ ከንፈሮቼን ክፈት፤

አፌም ምስጋናህን ያውጃል።

16መሥዋዕትን ብትወድ ኖሮ ባቀረብሁልህ ነበር፤

የሚቃጠል መሥዋዕትም ደስ አያሰኝህም።

17እግዚአብሔር የሚቀበለው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤51፥17 ወይም አምላክ ሆይ፤ የእኔ መሥዋዕት የተሰበረ

እግዚአብሔር ሆይ፤

አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም።

18በበጎ ፈቃድህ ጽዮንን አበልጽጋት፤

የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች ሥራ።

19የጽድቅ መሥዋዕት፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና፣

ሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ያን ጊዜ ደስ ያሰኙሃል፤

ኮርማዎች በመሠዊያህ ላይ የሚሠዉትም ያን ጊዜ ነው።

Священное Писание

Забур 51:1-11

Песнь 51

1Дирижёру хора. Наставление Давуда, 2когда эдомитянин Доэг пришёл к Шаулу и сообщил ему: «Давуд в доме Ахи-Малика»51:2 См. 1 Цар. 21–22..

3Что хвалишься злодейством, сильный?

Весь день со мной милость Всевышнего!

4Твой язык замышляет гибель;

он подобен отточенной бритве, о коварный.

5Ты любишь зло больше добра

и ложь – сильнее, чем слова правды. Пауза

6Ты любишь гибельные слова

и язык вероломный.

7Но Всевышний погубит тебя навек;

Он схватит тебя и выкинет прочь из шатра,

исторгнет твой корень из земли живых. Пауза

8Увидят праведники и устрашатся,

посмеются над тобой, говоря:

9«Вот человек,

который не сделал Всевышнего своей крепостью,

а верил в свои сокровища

и укреплялся, уничтожая других».

10А я подобен маслине,

зеленеющей в доме Всевышнего;

я верю в милость Всевышнего

вовеки.

11Буду славить Тебя вовек за сделанное Тобой

и уповать на Тебя,

потому что Ты благ к верным Тебе.