መዝሙር 47 – New Amharic Standard Version (NASV)

New Amharic Standard Version

መዝሙር 47:1-9

መዝሙር 47

እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ንጉሥ የዓለም ጌታ

ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር።

1ሕዝቦች ሁላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤

ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ።

2በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ የሆነው ንጉሥ፣

ልዑል እግዚአብሔር የሚያስፈራ ነውና።

3ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፤

መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን።

4ለሚወደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን፣

ርስታችንን እርሱ መረጠልን። ሴላ

5አምላክ በእልልታ፣

እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።

6አምላካችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤

ንጉሣችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤

7እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤

ምርጥ ዝማሬ47፥7 ዕብራይስጡ ማስኪል ይላል፤ ይኸውም የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የሙዚቃውን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። አቅርቡለት።

8እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሦአል፤

እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል።

9ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር፣

የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ፤

የምድር ነገሥታት47፥9 ወይም ጋሾች የእግዚአብሔር ናቸውና፤

እርሱም እጅግ ከፍ ከፍ ያለ ነው።