New Amharic Standard Version

ሐጌ 1:1-15

የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት የተደረገ ጥሪ

1ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዥ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ1፥1 የየሹዋ ተለዋጭ ስም ሲሆን በሐጌ መጽሐፍ ውስጥ በብዛት ይገኛል። እንዲህ ሲል መጣ፤

2እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ፣ ‘የእግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ጊዜ ገና ነው’ ይላል።”

3የእግዚአብሔርም ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፤ 4“ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ፣ እናንተ ራሳችሁ በተዋቡ ቤቶቻችሁ ውስጥ ለመኖር ጊዜው ነውን?”

5ስለዚህ እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “እስቲ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤ 6ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው፤ በላችሁ ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ ግን አልረካችሁም፤ ለበሳችሁ ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።”

7እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “እስቲ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤ 8ወደ ተራራ ውጡ፤ ዕንጨት አምጡ፤ ቤቱን ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፤ እከበርበታለሁም” ይላል እግዚአብሔር9ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ተስፋ አደረጋችሁ፤ ያገኛችሁት ግን ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ያስገባችሁትንም እኔ እፍ አልሁበት፤ ይህ የሆነው ለምን ይመስላችኋል?” የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ ሁላችሁም የራሳችሁን ቤት ለመሥራት ስለሮጣችሁ ነው፤ 10ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች። 11እኔም በዕርሻዎችና በተራሮች፣ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፣ በዘይቱና ምድር በምታፈራው ሁሉ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በእጆቻችሁም ሥራ ላይ ድርቅ አመጣሁ።”

12ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፣ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ የተረፉትም ሕዝብ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ፣ የነቢዩንም የሐጌን መልእክት ሰሙ፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ልኮታልና። ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ።

13ቀጥሎም የእግዚአብሔር መልእክተኛ ሐጌ፣ ይህን የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ” ይላል እግዚአብሔር14ስለዚህ እግዚአብሔር የይሁዳን ገዥ፣ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ፣ የኢያሱን መንፈስና፣ ከምርኮ የተረፈውን ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አነሣሣ፤ እነርሱም መጥተው የአምላካቸውን የእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት መሥራት ጀመሩ። 15ይህ የሆነውም ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በሃያ አራተኛው ቀን ነበር።

Persian Contemporary Bible

حجی 1:1-15

دعوت به بازسازی خانهٔ خدا

1در سال دوم سلطنت داريوش، در روز اول ماه ششم، خداوند پيامی توسط حجی نبی برای زروبابل (پسر شئلتیئيل) حاكم يهودا، و برای يهوشع (پسر يهوصادق) كاهن اعظم، فرستاد.

2خداوند قادر متعال به حجی نبی فرمود: «اين قوم می‌گويند كه اكنون وقت بازسازی خانهٔ خدا نيست.» 3سپس، خداوند اين پيام را توسط حجی نبی برای قوم فرستاد: 4«آيا اين درست است كه شما در خانه‌های نوساخته زندگی كنيد ولی خانهٔ من خراب بماند؟ 5به نتيجهٔ كارهايتان نگاه كنيد: 6بذر زياد می‌كاريد، ولی محصول كم برداشت می‌كنيد؛ می‌خوريد ولی سير نمی‌شويد؛ می‌نوشيد ولی تشنگی‌تان رفع نمی‌گردد؛ لباس می‌پوشيد اما گرم نمی‌شويد؛ مزد می‌گيريد ولی گويی آن را در جيبهای سوراخدار می‌گذاريد.

7«خوب فكر كنيد و ببينيد چه كرده‌ايد و نتيجه‌اش چه بوده است! 8حال به كوه رفته، چوب بياوريد و خانهٔ مرا دوباره بسازيد تا من از آن راضی شوم و در آنجا مردم احترام مرا بجا آورند.

9«انتظار محصول فراوانی داشتيد، اما خيلی كم به دست آورديد؛ و وقتی همان مقدار كم را هم به منزل آورديد، آن را از بين بردم. می‌دانيد چرا؟ چون خانهٔ من خراب مانده و شما فقط به فكر خانه‌های خود هستيد. 10به همين علت است كه آسمان نمی‌بارد و زمين محصول خود را نمی‌دهد. 11من در سرزمين شما خشكسالی پديد آورده‌ام و اين خشكسالی تمام كوهها، مزرعه‌ها، تاكستانها، باغهای زيتون و ساير محصولات و حتی انسان و حيوان و تمام حاصل دسترنج شما را فرا خواهد گرفت.»

12آنگاه زروبابل و يهوشع و تمام كسانی كه از اسارت برگشته بودند از خداوند ترسيدند و پيام حجی نبی را كه خداوند، خدايشان به او داده بود اطاعت كردند.

13سپس خداوند بار ديگر توسط نبی خود حجی به قوم فرمود: «من با شما هستم.» 14‏-15خداوند در زروبابل و يهوشع و تمام قوم علاقه و اشتياق ايجاد كرد تا خانهٔ او را بسازند. پس، در سال دوم سلطنت داريوش در روز بيست و چهارم ماه ششم همه جمع شده، به بازسازی خانهٔ خداوند قادر متعال، خدای خود پرداختند.