ሐጌ 1 – NASV & BPH

New Amharic Standard Version

ሐጌ 1:1-15

የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት የተደረገ ጥሪ

1ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዥ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ1፥1 የየሹዋ ተለዋጭ ስም ሲሆን፣ በሐጌ መጽሐፍ ውስጥ በብዛት ይገኛል። እንዲህ ሲል መጣ፤

2እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ፣ ‘የእግዚአብሔር ቤት የሚሠራበት ጊዜ ገና ነው’ ይላል።”

3የእግዚአብሔርም ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፤ 4“ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ፣ እናንተ ራሳችሁ በተዋቡ ቤቶቻችሁ ውስጥ ለመኖር ጊዜው ነውን?”

5ስለዚህ እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “እስቲ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤ 6ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው። በላችሁ፤ ግን አልጠገባችሁም። ጠጣችሁ፤ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ፤ ግን አልሞቃችሁም። ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።”

7እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “እስቲ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤ 8ወደ ተራራ ውጡ፤ ዕንጨት አምጡ፤ ቤቱን ሥሩ፤ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፤ እከበርበታለሁም” ይላል እግዚአብሔር9ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ተስፋ አደረጋችሁ፤ ያገኛችሁት ግን ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ያስገባችሁትንም እኔ እፍ አልሁበት፤ ይህ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ ሁላችሁም የራሳችሁን ቤት ለመሥራት ስለ ሮጣችሁ ነው፤ 10ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች። 11እኔም በዕርሻዎችና በተራሮች፣ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፣ በዘይቱና ምድር በምታፈራው ሁሉ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በእጆቻችሁም ሥራ ላይ ድርቅ አመጣሁ።”

12ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፣ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ የተረፉትም ሕዝብ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ፣ የነቢዩንም የሐጌን መልእክት ሰሙ፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ልኮታልና። ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ።

13ቀጥሎም የእግዚአብሔር መልእክተኛ ሐጌ፣ ይህን የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ” ይላል እግዚአብሔር14ስለዚህ እግዚአብሔር የይሁዳን ገዥ፣ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስና ከምርኮ የተረፈውን ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አነሣሣ፤ እነርሱም መጥተው የአምላካቸውን የእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት መሥራት ጀመሩ። 15ይህ የሆነውም ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በሃያ አራተኛው ቀን ነበር።

Bibelen på hverdagsdansk

Haggajs Bog 1:1-15

Gud befaler folket at genopbygge templet

1Profeten Haggaj modtog følgende budskab fra Herren den første dag i den sjette måned af kong Dareios’ andet regeringsår. Haggaj fik besked på at give det videre til Judas guvernør, Zerubbabel, søn af Shealtiel, og ypperstepræsten Josva, søn af Jotzadak.

2„Hør hvad Gud, den Almægtige, siger: Hvorfor siger folk, at tiden endnu ikke er inde til at genopbygge mit tempel? 3-4Mener I virkelig, at det er rigtigt af jer at bo i fornemme huse, når mit hus stadig ligger i ruiner? 5Tænk over, hvordan det går med jer: 6I planter og sår, men får en dårlig høst. I mangler både mad og drikke og tøj, og jeres arbejdsløn forsvinder som i en hullet pung. 7Se jer omkring og tænk over situationen.

8Gå nu op i bjergene og hent tømmer, så mit tempel kan blive færdigbygget, og jeg kan glæde mig over det og vise jer min herlighed.

9I håber på en god høst, men det bliver kun til lidt, og den smule I henter hjem, forsvinder som dug for solen. Hvorfor? Fordi mit hus ligger i ruiner, mens I har travlt med at bygge huse til jer selv. 10Derfor holder jeg regnen tilbage, så I får en dårlig høst. 11Jeg lader tørken ramme både lavland og højland, korn og druer, oliven og de øvrige afgrøder. Både mennesker og kvæg lider under det. Alt jeres møjsommelige arbejde er spildt.”

12Da adlød de alle sammen Herrens ord, som kom til dem gennem profeten Haggaj. Både guvernøren Zerubbabel, ypperstepræsten Josva og den rest af befolkningen, som var kommet tilbage til landet, adlød, for de var klar over, at budskabet var fra Gud, og de tog det alvorligt.

13Profeten Haggaj gav da folket følgende ord fra Herren: „Jeg vil være med jer og velsigne jer!” 14-15Og Gud gjorde Zerubbabel, Josva og hele folket så opsat på at genopbygge Herrens, den Almægtiges, tempel, at de allerede den 24. i samme måned tog fat på arbejdet.