New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 6:1-15

የሰባቱ ዲያቆናት መመረጥ

1የደቀ መዛሙርት ቍጥር እየጨመረ በሄደበት በዚህ ወቅት፣ ከግሪክ አገር የመጡ አይሁድ በይሁዳ ይኖሩ በነበሩት አይሁድ ላይ አጒረመረሙ፤ ምክንያቱም በየዕለቱ በሚከናወነው ምግብ የማደል አሠራር ላይ ከእነርሱ ወገን የሆኑት መበለቶች ችላ ተብለው ነበር። 2ስለዚህ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ሌሎችን ደቀ መዛሙርት በአንድነት ሰብስበው እንዲህ አሉ፤ “እኛ የማእዱን አገልግሎት ለማስተናገድ ስንል የእግዚአብሔርን ቃል አገልግሎት መተው አይገባንም። 3ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ መካከል በመንፈስ ቅዱስና በጥበብ የተሞሉ ለመሆናቸው የተመሰከረላቸውን ሰባት ሰዎች ምረጡ፤ ይህን ኀላፊነት ለእነርሱ እንሰጣለን፤ 4እኛ ግን በጸሎትና በቃሉ አገልግሎት እንተጋለን።”

5አባባሉ ሁላቸውን ደስ አሰኘ፤ በእምነትና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን፣ እንዲሁም ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞናን፣ ጰርሜናንና ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ። 6እነዚህንም አምጥተው ሐዋርያት ፊት አቀረቡአቸው፤ እነርሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።

7የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ የደቀ መዛሙርቱም ቍጥር በኢየሩሳሌም እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙዎቹ ለእምነት የታዘዙ ሆኑ።

የእስጢፋኖስ መያዝ

8በዚህ ጊዜ እስጢፋኖስ ጸጋንና ኀይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅ ነገሮችንና ታምራዊ ምልክቶችን ያደርግ ነበር። 9“የነጻ ወጪዎች ምኵራብ” ተብሎ የሚጠራው ምኵራብ አባላት የሆኑ ከቀሬናና ከእስክንድርያ፣ እንዲሁም ከኪልቅያና ከእስያ አውራጃዎች የመጡ ሰዎችም ተቃውሞ አስነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ጀመር፤ 10ይሁን እንጂ ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም።

11ስለዚህ፣ “እስጢፋኖስ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲሰነዝር ሰምተናል” የሚሉ ሰዎችን በስውር አዘጋጁ።

12በዚህ ሁኔታ ሕዝቡን፣ የአገር ሽማግሌዎቹንና የሕግ መምህራኑን በማነሣሣት፣ እስጢፋኖስን አስይዘው በአይሁድ ሸንጎ ፊት አቀረቡት፤ 13እንዲህ ብለው የሚመሰክሩ የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት፤ “ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራና በሕጉ ላይ የስድብ ቃል መናገሩን በፍጹም አልተወም፤ 14ምክንያቱም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያጠፋና ከሙሴ የተቀበልነውን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተነዋል።”

15በሸንጎው ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ እስጢፋኖስን ትኵር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ የመልአክ ፊት መስሎ ታያቸው።

Thai New Contemporary Bible

กิจการของอัครทูต 6:1-15

การเลือกคนทั้งเจ็ด

1ครั้งนั้นเมื่อสาวกเพิ่มจำนวนขึ้นชาวยิวผู้ถือธรรมเนียมกรีกบ่นไม่พอใจชาวยิวผู้ถือธรรมเนียมยิวเพราะแม่ม่ายในหมู่พวกตนถูกละเลยในการแจกจ่ายอาหารประจำวัน 2ดังนั้นอัครทูตทั้งสิบสองคนจึงเรียกสาวกทั้งปวงมาประชุมพร้อมหน้ากันและกล่าวว่า “เป็นการไม่ถูกต้องที่เราจะละเลยพันธกิจแห่งพระวจนะของพระเจ้าเพื่อไปรับใช้ที่โต๊ะอาหาร 3พี่น้องทั้งหลาย จงเลือกคนเจ็ดคนในพวกท่านซึ่งเป็นที่ทราบกันว่าเต็มด้วยพระวิญญาณและสติปัญญา เราจะได้มอบความรับผิดชอบนี้แก่พวกเขา 4ส่วนเราจะได้เอาใจใส่ในการอธิษฐานและพันธกิจแห่งพระวจนะ”

5ที่ประชุมทั้งหมดเห็นชอบกับข้อเสนอนี้จึงเลือกสเทเฟน ชายผู้เปี่ยมด้วยความเชื่อและพระวิญญาณบริสุทธิ์ พร้อมทั้งฟีลิป โปรโครัส นิคาโนร์ ทิโมน ปารเมนัส และนิโคลัสจากเมืองอันทิโอกซึ่งมาเข้าจารีตยิว 6พวกเขานำทั้งเจ็ดคนนี้มาหาอัครทูต อัครทูตก็อธิษฐานและวางมือให้

7ดังนั้นพระวจนะของพระเจ้าจึงแพร่ออกไปจำนวนสาวกในกรุงเยรูซาเล็มเพิ่มขึ้นอย่างรวดเร็วและมีปุโรหิตจำนวนมากมารับเชื่อ

สเทเฟนถูกจับ

8ฝ่ายสเทเฟนผู้เปี่ยมด้วยพระคุณและฤทธิ์เดชของพระเจ้าได้ทำหมายสำคัญและปาฏิหาริย์ที่ยิ่งใหญ่หลายอย่างในหมู่ประชาชน 9แต่ถูกต่อต้านโดยสมาชิกของธรรมศาลาแห่งทาสที่ได้รับอิสรภาพ (ตามที่เขาเรียกกัน) คือพวกยิวจากเมืองไซรีน เมืองอเล็กซานเดรีย ทั้งจากแคว้นซิลีเซียและเอเชีย คนเหล่านี้โต้เถียงกับสเทเฟน 10แต่ไม่สามารถเอาชนะสติปัญญาของเขาหรือพระวิญญาณผู้ตรัสผ่านเขา

11พวกเขาจึงลอบยุบางคนให้พูดว่า “เราได้ยินสเทเฟนกล่าวลบหลู่โมเสสและพระเจ้า”

12ดังนั้นพวกเขาได้ปลุกปั่นประชาชนตลอดจนเหล่าผู้อาวุโสและพวกธรรมาจารย์ให้ลุกฮือขึ้น พวกเขาจับสเทเฟนและนำตัวมาต่อหน้าสภาแซนเฮดริน 13พวกเขาสร้างพยานเท็จมาให้การว่า “ชายคนนี้พูดลบหลู่สถานบริสุทธิ์และบทบัญญัติไม่หยุดเลย 14เพราะเราได้ยินเขาพูดว่าพระเยซูแห่งนาซาเร็ธนั้นจะทำลายสถานที่นี้และเปลี่ยนธรรมเนียมซึ่งโมเสสได้ให้สืบทอดมาจนถึงเรา”

15คนทั้งปวงที่นั่งอยู่ในสภาแซนเฮดรินก็จ้องมองสเทเฟนเห็นใบหน้าของเขาเหมือนใบหน้าของทูตสวรรค์