New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 28:1-31

ጳውሎስ በመላጥያ ደሴት

1በደኅና ወደ ምድር ከደረስን በኋላ፣ ደሴቲቱ መላጥያ ተብላ እንደምትጠራ ተረዳን። 2የደሴቲቱ ነዋሪዎችም የሚያስገርም ደግነት አሳዩን፤ ዝናብና ብርድ ነበርና እሳት አንድደው ሁላችንን ተቀበሉን። 3ጳውሎስም ጭራሮ ሰብስቦ ወደ እሳቱ ሲጨምር፣ ከሙቀቱ የተነሣ እፉኝት ወጥታ እጁ ላይ ተጣበቀች። 4የደሴቲቱ ነዋሪዎች እባብ በእጁ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በርግጥ ነፍስ ገዳይ ነው፤ ከባሕር ቢያመልጥ እንኳ የፍርድ አምላክ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ተባባሉ። 5ጳውሎስ ግን እባቢቱን ወደ እሳቱ አራገፋት፤ አንዳችም ጒዳት አልደረሰበትም። 6ሰዎቹ ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል ወይም ድንገት ሞቶ ይወድቃል ብለው ይጠባበቁ ነበር፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ጠብቀው ምንም የተለየ ነገር እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ፣ ሐሳባቸውን ለውጠው፣ “ይህስ አምላክ ነው” አሉ።

7በዚያም ስፍራ አጠገብ የደሴቲቱ አለቃ የፑፕልዮስ ርስት የሆነ መሬት ነበረ፤ እርሱም በቤቱ ተቀብሎን ሦስት ቀን በቸርነት አስተናገደን። 8የፑፕልዮስም አባት በትኵሳትና በተቅማጥ ሕመም ተይዞ ተኝቶ ነበር፤ ጳውሎስም ሊጠይቀው ገብቶ ከጸለየለት በኋላ፣ እጁን ጭኖ ፈወሰው። 9ይህም በሆነ ጊዜ፣ በደሴቲቱ የነበሩ ሌሎች ሕመምተኞችም እየመጡ ተፈወሱ። 10እኛንም በብዙ መንገድ አከበሩን፤ በመርከብም ለመሄድ በተዘጋጀን ጊዜ፣ የሚያስፈልገንን ሁሉ ጫኑልን።

ጳውሎስ ሮም ደረሰ

11ከሦስት ወር በኋላም፣ በደሴቲቱ ክረምቱን ቆሞ በሰነበተ በአንድ መርከብ ተነሥተን ጒዞ ጀመርን። ይህም መርከብ የእስክንድርያ ሲሆን፣ በላዩ ላይ የመንታ አማልክቱ የዲዮስቆሮስ አርማ ነበረበት። 12ወደ ሰራኩስ ከተማ ገብተን ሦስት ቀን በዚያ ተቀመጥን። 13ከዚያም በመርከብ ተጒዘን ሬጊዩም ደረስን፤ በማግስቱም የደቡብ ነፋስ ስለ ተነሣ ፑቲዮሉስ የደረስነው በሚቀጥለው ቀን ነበር። 14በዚያም ወንድሞችን አገኘን፤ እነርሱም ሰባት ቀን አብረናቸው እንድንቀመጥ ለመኑን፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሮም ሄድን። 15በዚያ የነበሩ ወንድሞችም መምጣታችንን ስለ ሰሙ፣ እስከ አፍዩስ ፋሩስ፣ እንዲሁም ‘ሦስት ማደሪያ’ እስከሚባለው ቦታ ድረስ ሊቀበሉን ወጡ፤ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ተጽናናም። 16ሮም በደረስን ጊዜም፣ ጳውሎስ ይጠብቀው ከነበረው ወታደር ጋር፣ ለብቻው በዚያ እንዲቈይ ተፈቀደለት።

ጳውሎስ በጥበቃ ሥር ሆኖ ሰበከ

17ከሦስት ቀንም በኋላ፣ ጳውሎስ የአይሁድን መሪዎች በአንድነት ጠራ፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞች ሆይ፤ እኔ፣ ሕዝባችንን ወይም የአባቶቻችንን ሥርዐት የሚቃረን ምንም ሳላደርግ፣ በኢየሩሳሌም አስረው ለሮማውያን አሳልፈው ሰጥተውኛል። 18እነርሱም መርምረው ለሞት የሚያበቃ በደል ስላላገኙብኝ፣ ሊፈቱኝ ፈልገው ነበር፤ 19አይሁድ በተቃወሙ ጊዜ ግን፣ ለቄሳር ይግባኝ ማለት ግድ ሆነብኝ እንጂ ሕዝቤን የምከስበት ምክንያት ኖሮኝ አይደለም። 20እናንተንም ለማየትና ለማነጋገር የጠራኋችሁ በዚሁ ምክንያት ነው፤ በዚህ ሰንሰለት የታሰርሁትም ለእስራኤል በተሰጠው ተስፋ ምክንያት ነው።”

21እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ስለ አንተ ከይሁዳ ምድር የተጻፈ አንድም ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ከዚያ የመጡ ወንድሞችም ስለ አንተ ያቀረቡት ወይም የተናገሩት አንዳች መጥፎ ነገር የለም። 22ይሁን እንጂ፣ ሰዎች ስለዚህ የእምነት ክፍል በየቦታው ክፉ እንደሚያወሩበት እናውቃለን፤ የአንተ አስተያየት ደግሞ ምን እንደሆነ መስማት እንፈልጋለን።”

23ቀን ከቀጠሩለትም በኋላ፣ ብዙ ሆነው ወደ ማረፊያ ስፍራው መጡ፤ እርሱም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየመሰከረ ያብራራላቸው ነበር፤ ከሙሴ ሕግና ከነቢያትም በመጥቀስ ስለ ኢየሱስ ሊያሳምናቸው ሞከረ። 24አንዳንዶቹ እርሱ የሚለውን አምነው ተቀበሉ፤ ሌሎቹ ግን አላመኑበትም፤ 25እርስ በርሳቸውም አልተስማሙም፤ ጳውሎስም እንዲህ የሚል የመጨረሻ ቃል ከተናገራቸው በኋላ ሄዱ፤ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ በትክክል እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፤

26“ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ እንዲህም በላቸው፤

“መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤

ማየትን ታያላችሁ፤ ነገር ግን አትመለከቱም።”

27የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና፤

ጆሮአቸውም ተደፍኖአል፤

ዐይናቸውንም ጨፍነዋል።

አለዚያማ፣ በዐይናቸው አይተው፣

በጆሮአቸው ሰምተው፣

በልባቸው አስተውለው፣

ይመለሱና እፈውሳቸዋለሁ።’

28“ስለዚህ የእግዚአብሔር ማዳን ለአሕዛብ እንደ ተላከ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤ እነርሱም ይሰሙታል።” 29ይህንንም ከተናገረ በኋላ፣ አይሁድ እርስ በርሳቸው እጅግ እየተከራከሩ ሄዱ።28፥29 አንዳንድ የጥንት ትርጒሞች ይህ ቍጥር የላቸውም።

30ጳውሎስም ራሱ በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፤ ወደ እርሱ የሚመጡትንም ሁሉ በደስታ ይቀበል ነበር፤ 31ማንም ሳይከለክለው የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከ፣ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ግልጽነት ያስተምር ነበር።

Thai New Contemporary Bible

กิจการของอัครทูต 28:1-31

บนเกาะมอลตา

1เมื่อขึ้นฝั่งโดยปลอดภัยแล้วเราจึงรู้ว่าเกาะนั้นชื่อเกาะมอลตา 2ชาวเกาะกรุณาเราเป็นพิเศษพวกเขาก่อไฟต้อนรับเราทุกคนเพราะฝนตกและหนาว 3เปาโลเก็บกิ่งไม้มาหอบหนึ่งขณะเขากำลังเอาไม้หอบนั้นใส่ไฟมีงูพิษตัวหนึ่งถูกความร้อนจึงพุ่งออกมากัดติดที่มือของเขา 4เมื่อชาวเกาะเห็นงูห้อยอยู่ที่มือของเปาโลก็พูดกันว่า “คนนี้ต้องเป็นฆาตกรแน่ๆ เพราะถึงแม้ว่าเขารอดตายจากทะเลเจ้าแห่งความยุติธรรมก็ยังไม่ปล่อยให้มีชีวิต” 5แต่เปาโลสะบัดงูทิ้งลงในไฟและไม่เป็นอันตรายแต่อย่างใด 6พวกเขาคาดว่าเปาโลจะบวมขึ้นหรือล้มตายทันทีแต่หลังจากคอยดูอยู่นานและไม่เห็นเขาเป็นอะไรจึงเปลี่ยนความคิดและพูดว่าเปาโลเป็นเทพเจ้า

7มีที่ดินแปลงหนึ่งอยู่ใกล้ๆ ที่นั่นเป็นของปูบลิอัสหัวหน้าชาวเกาะ เขาต้อนรับขับสู้เราอย่างดีตลอดสามวัน 8บิดาของปูบลิอัสป่วยมีไข้และเป็นบิดนอนซมอยู่ เปาโลเข้าไปเยี่ยม หลังจากอธิษฐานแล้วก็วางมือบนเขา รักษาเขาให้หาย 9เมื่อสิ่งนี้เกิดขึ้นคนป่วยอื่นๆ ที่เกาะนั้นก็มาและรับการรักษาให้หาย 10พวกเขาให้เกียรติเราหลายๆ ด้านและเมื่อเราพร้อมที่จะออกเรือเขาก็นำสิ่งของที่จำเป็นมาให้เรา

ถึงกรุงโรม

11สามเดือนต่อมาเราลงเรือซึ่งมาพักหนาวอยู่ที่เกาะนี้ เรือนั้นมาจากเมืองอเล็กซานเดรีย มีรูปแกะสลักเทพเจ้าแฝด คือคาสเตอร์และพอลลักซ์ที่หัวเรือ 12เราจอดแวะที่เมืองไซราคิวส์สามวัน 13จากที่นั่นเราแล่นเรือมาถึงเมืองเรยีอูม วันรุ่งขึ้นลมใต้พัดมาและในวันต่อมาก็ถึงเมืองโปทิโอลี 14เราพบพี่น้องบางคนที่นั่น เขาเชิญให้เราพักอยู่ด้วยหนึ่งสัปดาห์แล้วเราก็มากรุงโรม 15พวกพี่น้องที่กรุงโรมได้ข่าวว่าเราจะมาจึงออกมารับเราไกลถึงย่านอัปปีอัสและบ้านสามโรงแรม เมื่อได้เห็นคนเหล่านี้เปาโลก็ขอบพระคุณพระเจ้าและมีกำลังใจขึ้น 16เมื่อเรามาถึงกรุงโรมเปาโลได้รับอนุญาตให้อยู่ตามลำพังโดยมีทหารคนหนึ่งคอยคุมเขาไว้

เปาโลเทศนาในกรุงโรม

17สามวันต่อมาเปาโลเชิญบรรดาผู้นำชาวยิวมาประชุม เมื่อพวกเขามาพร้อมหน้ากันเปาโลก็กล่าวว่า “พี่น้องทั้งหลาย แม้ว่าข้าพเจ้าไม่ได้ทำผิดอะไรต่อพี่น้องร่วมชาติของเราหรือผิดธรรมเนียมของเหล่าบรรพบุรุษ ข้าพเจ้าก็ถูกจับกุมในกรุงเยรูซาเล็มและส่งตัวให้พวกโรมัน 18พวกเขาไต่สวนข้าพเจ้าแล้วก็ต้องการจะปล่อยตัวไปเพราะข้าพเจ้าไม่ได้ทำสิ่งใดผิดสมควรแก่โทษประหาร 19แต่เมื่อพวกยิวคัดค้านข้าพเจ้าจึงจำต้องถวายฎีกาถึงซีซาร์ไม่ใช่ว่ามีข้อหาอะไรจะฟ้องร้องพี่น้องร่วมชาติของข้าพเจ้า 20ด้วยเหตุนี้ข้าพเจ้าจึงเชิญท่านทั้งหลายมาพูดคุยกันเพราะที่ข้าพเจ้าถูกล่ามโซ่อยู่นี้ก็เนื่องด้วยความหวังของชนชาติอิสราเอล”

21พวกเขาตอบว่า “เราไม่ได้รับจดหมายใดๆ จากแคว้นยูเดียพาดพิงถึงท่านและก็ไม่มีพี่น้องคนใดที่มาจากที่นั่นได้รายงานหรือพูดอะไรไม่ดีเกี่ยวกับท่าน 22แต่เราอยากฟังความคิดเห็นของท่านเพราะเรารู้อยู่ว่าผู้คนทุกแห่งหนพูดติเตียนนิกายนี้”

23พวกเขานัดหมายวันที่จะพบกับเปาโลและคนเป็นอันมากพากันมายังที่พักของเขา ตั้งแต่เช้าจดเย็นเปาโลอธิบายและประกาศเรื่องอาณาจักรของพระเจ้าแก่พวกเขาและพยายามยกเหตุผลจากหนังสือบทบัญญัติของโมเสสและหนังสือผู้เผยพระวจนะมาทำให้พวกเขาเชื่อพระเยซู 24สิ่งที่เขากล่าวทำให้บางคนเชื่อแต่บางคนก็ไม่เชื่อ 25พวกเขาไม่เห็นพ้องกันและเริ่มจากไปหลังจากที่เปาโลกล่าวทิ้งท้ายว่า “เป็นจริงตามที่พระวิญญาณบริสุทธิ์ตรัสกับบรรพบุรุษของพวกท่านผ่านทางผู้เผยพระวจนะอิสยาห์ว่า

26“ ‘จงไปหาชนชาตินี้และบอกพวกเขาว่า

“เจ้าจะฟังแล้วฟังเล่าแต่จะไม่มีวันเข้าใจ

เจ้าจะดูแล้วดูเล่าแต่จะไม่มีวันประจักษ์”

27เพราะจิตใจของชนชาตินี้ดื้อด้านไป

พวกเขาแทบจะไม่เอียงหูฟัง

และพวกเขาได้ปิดตาตนเองเสีย

มิฉะนั้นแล้วพวกเขาจะได้เห็นกับตา

ได้ยินกับหู

เข้าใจด้วยจิตใจ

และหันกลับมา แล้วเราจะรักษาพวกเขา

ให้หาย’28:26,27 อสย.6:9,10

28“ฉะนั้นข้าพเจ้าอยากให้ท่านรู้ว่าความรอดของพระเจ้าได้แผ่ไปถึงชาวต่างชาติแล้วและพวกเขาจะฟัง!”28:28 สำเนาบางต้นบางสำเนาว่าฟัง!29หลังจากเปาโลกล่าวเช่นนี้แล้ว พวกยิวก็จากไปและโต้เถียงกันเองเป็นการใหญ่

30ตลอดสองปีเต็มเปาโลพักอยู่ในบ้านซึ่งเขาเช่าไว้และต้อนรับคนทั้งปวงที่มาหาเขา 31เขาประกาศเรื่องอาณาจักรของพระเจ้าและสอนเรื่ององค์พระเยซูคริสต์เจ้าอย่างกล้าหาญโดยไม่ถูกขัดขวาง