New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 25:1-27

ጳውሎስ በፊስጦስ ፊት ቀረበ

1ፊስጦስም ወደ አውራጃው ከገባ ከሦስት ቀን በኋላ፣ ከቂሳርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። 2የካህናት አለቆችና የአይሁድ መሪዎች ፊቱ ቀርበው ጳውሎስን ከሰሱት። 3ጳውሎስን መንገድ ላይ አድፍጠው ሊገድሉት ስለ ፈለጉ፣ ፊስጦስ ለእነርሱ እንዲያዳላላቸውና ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስመጣው አጥብቀው ለመኑት። 4ፊስጦስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ጳውሎስ ታስሮ በቂሳርያ እስር ቤት ይገኛል፤ እኔም በቅርቡ ወደዚያው እሄዳለሁ፤ 5ስለዚህ ከባለሥልጣኖቻችሁ መካከል አንዳንዶች ከእኔ ጋር ይምጡና ሰውየው ጥፋት ካለበት ክሱን በዚያው ያቅርቡ።”

6ከእነርሱም ጋር ስምንት ወይም ዐሥር ቀን ያህል ከሰነበተ በኋላ፣ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በማግስቱም ፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ። 7ጳውሎስ በቀረበ ጊዜ፣ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁድ ከበቡት፤ በማስረጃ ያልተደገፉ ብዙ ከባድ ክሶችም አቀረቡበት።

8ጳውሎስም፣ “እኔ በአይሁድም ሕግ ሆነ በቤተ መቅደሱ ወይም በቄሣር ላይ የፈጸምሁት በደል የለም” ሲል የመከላከያ መልሱን ሰጠ።

9ፊስጦስም ለአይሁድ በጎ ለመዋል ፈልጎ፣ ጳውሎስን “ስለዚህ ጒዳይ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ በእኔ ፊት ለመፋረድ ፈቃደኛ ነህን?” አለው።

10ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “አሁንም ቢሆን ፍትሕ ማግኘት በምችልበት፣ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ምንም በደል አልፈጸምሁም፤ 11ይሁን እንጂ ለሞት የሚያበቃ በደል ከተገኘብኝ፣ አልሙት አልልም፤ እነዚህ አይሁድ የሚያቀርቡብኝ ክስ እውነት ካልሆነ ግን፣ እኔን ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጥ የሚችል የለም፤ ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ።”

12ፊስጦስ ከመማክርቱ ጋር ከተመካከረ በኋላ፣ “ወደ ቄሳር ይግባኝ ስላልህ፣ ወደ ቄሳር ትሄዳለህ” አለው።

ፊስጦስ ከንጉሥ አግሪጳ ምክር ጠየቀ

13ከጥቂት ቀንም በኋላ፣ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ፊስጦስን እጅ ሊነሡ ወደ ቂሳርያ ወረዱ፤ 14በዚያም ብዙ ቀን ተቀመጡ፤ ፊስጦስም የጳውሎስን ጒዳይ አንሥቶ ለንጉሡ እንዲህ አለው፤ “ፊልክስ በእስር ቤት የተወው አንድ ሰው እዚህ አለ፤ 15ወደ ኢየሩሳሌም በሄድሁ ጊዜ፣ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች እንድፈርድበት ከሰውት ነበር።

16“እኔም፣ ተከሳሽ በከሳሾቹ ፊት ቆሞ ለተከሰሰበት ነገር መልስ ለመስጠት ዕድል ሳያገኝ፣ አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ልማድ እንዳልሆነ ነገርኋቸው። 17ስለዚህ ከሳሾቹ ከእኔ ጋር ወደዚህ በመጡ ጊዜ፣ ጒዳዩን ሳላጓትት በማግስቱ ችሎት ተቀምጬ ያን ሰው እንዲያቀርቡት አዘዝሁ። 18ከሳሾቹም ተነሥተው በመቆም ሲናገሩ፣ እኔ ያሰብሁትን ያህል ከባድ ክስ አላቀረ ቡበትም፤ 19ይልቁን ስለ ገዛ ሃይማኖታቸውና ሞቶ ስለ ነበረው፣ ጳውሎስ ግን ሕያው ነው ስለሚለው ሰው፣ ስለ ኢየሱስ ይከራከሩት ነበር። 20እኔም ይህን ነገር እንዴት እንደምፈታው ግራ ስለገባኝ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ስለ ዚሁ ጒዳይ እንዲፋረድ ፈቃደኝነቱን ጠየቅሁት። 21ነገር ግን ጳውሎስ ጒዳዩ በንጉሠ ነገሥቱ እንዲታይለት ይግባኝ ባለ ጊዜ፣ እኔም ወደ ቄሳር እስከምልከው ድረስ እስር ቤት እንዲይ አዘዝሁ።”

22አግሪጳም ፊስጦስን፣ “እኔም እኮ ይህ ሰው ሲናገር መስማት እፈልግ ነበር” አለው።

እርሱም፣ “እንግዲያውስ ነገ ትሰማዋለህ” አለው።

ጳውሎስ በንጉሥ አግሪጳ ፊት

23በማግስቱም አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ክብር መጥተው፣ ከከፍተኛ መኰንኖችና ከከተማዪቱ ታላላቅ ሰዎች ጋር ወደ መሰብሰቢያው አዳራሽ ገቡ፤ በፊስጦስም ትእዛዝ ጳውሎስ እንዲቀርብ ተደረገ። 24በዚህ ጊዜ ፊስጦስ እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፤ እንዲሁም እዚህ አብራችሁን ያላችሁ ሁሉ፤ ይህን ሰው ታዩታላችሁ? በኢየሩሳሌምና እዚህ በቂሳርያም የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ፣ ይህ ሰው ከእንግዲህ በሕይወት መኖር አይገባውም በማለት እየጮኹ ለመኑ። 25እኔም ለሞት የሚያበቃ አንዳች ነገር አለ ማድረጉን ተረዳሁ፤ ሆኖም ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ወደ ሮም ልልከው ወሰንሁ። 26ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የምጽፈው የተረጋገጠ ነገር አላገኘሁም፤ ስለዚህም ከተመረመረ በኋላ የምጽፈውን ነገር ለማግኘት ሁላችሁም ፊት በተለይ ደግሞ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፤ በአንተ ፊት አቀረብሁት፤ 27ይኸውም አንድ እስረኛ ወደ በላይ ሲላክ የተከሰሰበትን ምክንያት አለመግለጽ ትክክል ስላልመሰለኝ ነው።”

Het Boek

Handelingen 25:1-27

Paulus verschijnt voor Festus

1Drie dagen nadat Festus in zijn gebied was aangekomen, ging hij van Caesarea naar Jeruzalem. 2Daar kwamen de leidende priesters en leidende Joden bij hem met hun verhalen over Paulus. 3Zij vroegen hem dringend Paulus naar Jeruzalem te laten overbrengen. Zij waren namelijk van plan hem onderweg vanuit een hinderlaag te vermoorden. 4Festus antwoordde dat Paulus in Caesarea bleef en dat hij zelf binnenkort daar weer heen wilde gaan. 5‘Laten enkelen van uw leiders met mij meereizen. Als die man iets verkeerds heeft gedaan, kunnen zij hem beschuldigen,’ zei hij.

6Na een dag of negen ging Festus terug naar Caesarea. De volgende dag ging hij op zijn stoel in het gerechtshof zitten en liet Paulus voorleiden. 7Meteen gingen de Joden uit Jeruzalem om Paulus heen staan en brachten vele zware beschuldigingen tegen hem in. Maar zij konden niets bewijzen. 8Paulus verdedigde zich en zei: ‘Ik heb de Joodse wet niet overtreden, de tempel niet ontwijd en mij ook niet tegen het Romeinse bewind verzet.’ 9‘Hebt u er iets op tegen naar Jeruzalem te gaan,’ vroeg Festus, die de Joden een plezier wilde doen, ‘en daar voor mij terecht te staan?’ 10‘Ik sta voor de Romeinse rechtbank,’ antwoordde Paulus. ‘Dan moet mijn zaak daar ook worden behandeld! Zoals u wel weet, heb ik de Joden niets gedaan. 11Als ik iets heb gedaan waarop de doodstraf staat, wil ik mij niet tegen mijn terechtstelling verzetten. Maar als hun beschuldigingen stuk voor stuk gelogen zijn, heeft niemand het recht mij aan hen uit te leveren. Ik ga in hoger beroep bij de keizer!’ 12Na met zijn raadsheren te hebben gesproken, antwoordde Festus: ‘Nu u een beroep op de keizer hebt gedaan, zult u ook naar de keizer gaan.’

13Kort daarop kwam koning Agrippa met zijn zuster Bernice in Caesarea aan voor een bezoek aan Festus. 14Tijdens hun verblijf van enkele dagen sprak Festus met de koning over de zaak van Paulus. ‘Felix heeft hier een man in gevangenschap achtergelaten tegen wie de Joden een aanklacht hebben ingediend. 15Toen ik in Jeruzalem was, hebben hun leidende priesters en leiders mij gevraagd hem terecht te stellen. 16Ik wees hen erop dat het bij ons, Romeinen, niet de gewoonte is iemand te veroordelen omdat anderen dat vragen. Hij moet eerst de kans krijgen zich tegenover zijn aanklagers te verdedigen. 17Die Joden kwamen met mij mee hier naartoe en ik heb de zaak de volgende dag meteen in behandeling genomen. Maar toen ik Paulus liet voorleiden, beschuldigden zij hem van iets heel anders dan ik had verwacht. 18Er was geen sprake van een overtreding of een misdaad. 19Het ging om kwesties van hun godsdienst en over een zekere Jezus, die al dood is, maar die volgens Paulus leeft! 20Omdat ik niet wist wat ik ermee aan moest, stelde ik Paulus voor naar Jeruzalem te gaan en daar de rechtszaak voort te zetten. 21Maar hij ging in hoger beroep. Hij wilde in voorarrest blijven tot de keizer in deze zaak uitspraak zou doen. Daarom heb ik bevel gegeven hem vast te houden, tot ik hem naar de keizer kan sturen.’ 22Agrippa zei: ‘Ik zou die man ook wel eens willen horen.’ ‘Dat kan,’ antwoordde Festus. ‘Dat regelen we morgen.’

23De volgende morgen stapten Agrippa en Bernice in vol ornaat de aula binnen. In hun gevolg waren hoge militairen en leden van het stadsbestuur. 24Festus liet Paulus binnen en zei: ‘Koning Agrippa, geachte aanwezigen! Een groot aantal Joden, zowel hier in de stad als in Jeruzalem, heeft een zware aanklacht tegen deze man ingediend. 25Zij hebben geroepen dat hij niet mag blijven leven. Mij is gebleken dat hij niets heeft gedaan waarop de doodstraf staat. Maar omdat hij zich op de keizer beroepen heeft, moet ik hem wel naar Rome sturen. 26Ik weet nu niet wat ik de keizer moet schrijven. Daarom heb ik de man hier laten voorleiden, in het bijzonder om door u, koning Agrippa, te worden gehoord. Misschien komt daar iets uit wat ik kan schrijven. 27Want het lijkt mij onzinnig om een gevangene naar Rome te sturen zonder erbij te vermelden wat de aanklacht tegen hem is.’