New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 22:1-30

1“ወንድሞችና አባቶች ሆይ፤ አሁን የማቀርብላችሁን የመከላከያ መልሴን ስሙኝ።”

2እነርሱም በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገር በሰሙ ጊዜ ከፊት ይልቅ ጸጥ አሉ።

ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ 3“እኔ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ የተወለድሁ አይሁዳዊ ስሆን፣ ያደግሁት ግን በዚህ ከተማ ነው። የአባቶቻችንን ሕግ በገማልያል እግር ሥር ተቀምጬ በሚገባ ተምሬአለሁ፤ ዛሬ እናንተ እንዲህ የምትቀኑለትን ያህል እኔም ለእግዚአብሔር እቀና ነበር። 4ይህን መንገድ የሚከተሉትንም እስከ ሞት ድረስ እያሳደድሁ፣ ወንዶችንም ሴቶችንም አስሬ ወደ ወህኒ እጥላቸው ነበር። 5ይህን ተግባሬን ሊቀ ካህናቱም ሆነ ሸንጎው ሁሉ ሊመሰክሩ ይችላሉ። ከእነርሱ ደብዳቤ ተቀብዬ ደማስቆ ወዳሉት ወንድሞቻቸው በመሄድ፣ እነዚህን ሰዎች አሳስሬ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥቼ ለማስቀጣት ወደዚያ እሄድ ነበር።

6“ስንጓዝም እኩለ ቀን ገደማ ወደ ደማስቆ እንደ ተቃረብሁ፣ ድንገት ታላቅ ብርሃን ከሰማይ በዙሪያዬ በራ፤ 7እኔም ምድር ላይ ወደቅሁ፤ ከዚያም፣ ‘ሳውል፤ ሳውል፤ ለምን ታሳድደኛለህ?’ የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ።

8“እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ አንተ ማን ነህ?’ አልሁት።

“እርሱም፣ ‘አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ’ አለኝ። 9ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አዩ፤ ነገር ግን የሚናገረኝን የእርሱን ድምፅ በትክክል አልሰሙም።

10“እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ምን ላድርግ?’ አልሁት።

“ጌታም፣ ‘ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ በዚያም ልታደርገው የሚገባህን ሁሉ ይነግሩሃል’ አለኝ። 11ከብርሃኑም ጸዳል የተነሣ ዐይኔ ስለ ታወረ፣ ከእኔ ጋር የነበሩት እጄን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አደረሱኝ።

12“ከዚያም ሐናንያ የተባለ ሰው ሊያየኝ ወደ እኔ መጣ፤ እርሱም ሕግን በጥንቃቄ የሚጠብቅና በዚያ በሚኖሩት አይሁድ ሁሉ ዘንድ እጅግ የተከበረ ሰው ነበረ። 13በአጠገቤም ቆሞ፣ ‘ወንድም ሳውል ሆይ፤ ዐይኖችህ ይብሩልህ!’ አለኝ፤ እኔም በዚያችው ቅጽበት አየሁት።

14“እርሱም ቀጥሎ እንዲህ አለ፤ ‘የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን እንድታውቅ፣ ጻድቁን እንድታይና ቃሉን ከአንደበቱ እንድትሰማ መርጦሃል፤ 15ስላየኸውና ስለ ሰማኸው ነገር በሰው ሁሉ ፊት ምስክር ትሆነዋለህና። 16ታዲያ፣ አሁን ምን ትጠብቃለህ? ተነሥተህ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ፤ ከኀጢአትህም ታጠብ።’

17“ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሼ በቤተ መቅደስ ስጸልይም ተመሰጥሁ፤ 18ጌታም ሲናገረኝ አየሁ፤ እርሱም አሁኑኑ፣ ‘ፈጥነህ ከኢየሩሳሌም ውጣ! ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና’ አለኝ።

19“እኔም እንዲህ አልሁት፤ ‘ጌታ ሆይ፤ በአንተ የሚያምኑትን ሰዎች ለማሰርና ለመደብደብ፣ በየምኵራቡ ስዞር እንደ ነበር እነዚህ ሰዎች ያውቃሉ፤ 20ደግሞም የአንተን ሰማዕት22፥20 ወይም ምስክር የእስጢፋኖስን ደም በሚያፈሱበት ጊዜ፣ በድርጊታቸው ተስማምቼ በቦታው ቆሜ የገዳዮቹን ልብስ እጠብቅ ነበር።’

21“ጌታም፣ ‘ሂድ፤ በሩቅ ወዳሉት አሕዛብ እልክሃለሁና’ አለኝ።”

ጳውሎስ የሮም ዜጋ መሆኑ ታወቀ

22ሕዝቡም ይህን ቃል እስኪናገር ድረስ ሰሙት፤ ከዚህ በኋላ ግን ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ፣ “ይህስ ከምድር ገጽ ይወገድ! በሕይወት መኖር አይገባውም! ብለው ጮኹበት።

23እነርሱም እየጮኹና ልብሳቸውን እየወረወሩ፣ ትቢያም ወደ ላይ እየበተኑ ሳሉ፣ 24የጦር አዛዡ ጳውሎስን ወደ ጦር ሰፈር እንዲያስገቡትና ሕዝቡ ለምን እንዲህ እንደሚጮኹበት እየተገረፈ እንዲመረመር ትእዛዝ ሰጠ። 25ጳውሎስም በጠፍር ወጥረው ሊገርፉት ሲሉ፣ አጠገቡ የቆመውን የመቶ አለቃ፣ “አንድን የሮም ዜጋ ያለ ፍርድ ለመግረፍ ሕግ ይፈቅድላችኋልን?” አለው።

26የመቶ አለቃውም ይህን ሲሰማ፣ ወደ ጦር አዛዡ ቀርቦ፣ “ምን እያደረግህ እንደሆነ ዐውቀሃል? ሰውየው እኮ ሮማዊ ነው” አለው።

27አዛዡም ወደ ጳውሎስ ቀርቦ፣ “አንተ ሰው እስቲ ንገረኝ፤ ሮማዊ ነህን?” አለው።

እርሱም፣ “አዎን፤ ነኝ” አለው።

28አዛዡም መልሶ፣ “እኔ ይህን ዜግነት ያገኘሁት ብዙ ገንዘብ አውጥቼ ነው” አለ።

ጳውሎስም፣ “እኔ ግን ከተወለድሁ ጀምሮ ሮማዊ ነኝ” አለው።

29ስለዚህ እነዚያ ሊመረምሩት ያሰቡት ሰዎች ወዲያው ከእርሱ ሸሹ፤ የጦር አዛዡም የሮም ዜጋ መሆኑን ባወቀ ጊዜ፣ በሰንሰለት አስሮት ስለ ነበር ፈራ።

ጳውሎስ በአይሁድ ሸንጎ ፊት ቀረበ

30በማግስቱም የጦር አዛዡ፣ አይሁድ ጳውሎስን የከሰሱበት ትክክለኛው ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ስለ ፈለገ ፈታው፤ ከዚያም የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሸንጎ አባላት በሙሉ እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ ጳውሎስንም ከደረጃው አውርዶ በፊታቸው አቆመው።

Thai New Contemporary Bible

กิจการของอัครทูต 22:1-30

1“พ่อแม่พี่น้อง บัดนี้โปรดฟังคำชี้แจงของข้าพเจ้า” 2เมื่อพวกนั้นได้ยินเขากล่าวเป็นภาษาอารเมคก็เงียบงัน

แล้วเปาโลจึงกล่าวว่า 3“ข้าพเจ้าเป็นยิว เกิดที่เมืองทาร์ซัสในแคว้นซิลีเซียแต่เติบโตขึ้นในเมืองนี้ ข้าพเจ้าเป็นศิษย์ของท่านอาจารย์กามาลิเอลได้รับการอบรมสั่งสอนในด้านบทบัญญัติของบรรพบุรุษของเราเป็นอย่างดีและมีใจร้อนรนเพื่อพระเจ้าเช่นเดียวกับที่ท่านทั้งหลายเป็นอยู่ทุกวันนี้ 4ข้าพเจ้าได้ข่มเหงบรรดาผู้ติดตาม ‘ทางนี้’ ถึงตาย ได้จับกุมทั้งชายหญิงและโยนพวกเขาเข้าคุก 5มหาปุโรหิตกับสมาชิกสภาทั้งปวงก็เป็นพยานได้ ข้าพเจ้าถึงกับขอจดหมายจากพวกเขาเหล่านี้ไปถึงพวกพี่น้องของพวกเขาในเมืองดามัสกัส แล้วเดินทางไปที่นั่นเพื่อจับคนพวกนี้เป็นนักโทษและพามาที่กรุงเยรูซาเล็มเพื่อลงโทษ

6“ประมาณเที่ยงขณะที่ข้าพเจ้ามาเกือบจะถึงเมืองดามัสกัสแล้ว ทันใดนั้นมีแสงสว่างจ้าจากฟ้าสวรรค์ส่องแวบวาบรอบตัวข้าพเจ้า 7ข้าพเจ้าล้มลงกับพื้นและได้ยินพระสุรเสียงตรัสกับข้าพเจ้าว่า ‘เซาโล! เซาโลเอ๋ย! เจ้าข่มเหงเราทำไม?’

8“ข้าพเจ้าถามว่า ‘พระองค์เจ้าข้า พระองค์ทรงเป็นผู้ใด?’

“พระองค์ตรัสตอบว่า ‘เราคือเยซูแห่งนาซาเร็ธผู้ที่เจ้ากำลังข่มเหง’ 9คนที่ไปกับข้าพเจ้าเห็นแสงสว่างนั้นแต่ไม่เข้าใจพระสุรเสียงที่ตรัสกับข้าพเจ้า

10“ข้าพเจ้าทูลถามว่า ‘พระองค์เจ้าข้า ข้าพระองค์ควรทำเช่นไร?’

“องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า ‘จงลุกขึ้น เข้าไปในเมืองดามัสกัส ที่นั่นจะมีผู้บอกให้รู้ทุกสิ่งที่เจ้าได้รับมอบหมายให้ทำ’ 11คนที่ไปด้วยจูงมือข้าพเจ้าพาเข้าเมืองดามัสกัสเพราะแสงจ้านั้นทำให้ข้าพเจ้าตาบอด

12“มีคนหนึ่งชื่ออานาเนียมาหาข้าพเจ้า เขาเคร่งครัดในบทบัญญัติและเป็นที่นับถืออย่างยิ่งของชาวยิวทั้งปวงที่นั่น 13เขายืนข้างๆ ข้าพเจ้าและกล่าวว่า ‘พี่เซาโลเอ๋ย จงมองเห็นเถิด!’ วินาทีนั้นเอง ข้าพเจ้าก็สามารถมองเห็นเขา

14“แล้วเขากล่าวว่า ‘พระเจ้าของบรรพบุรุษของเราได้ทรงเลือกสรรท่านให้ทราบพระประสงค์ของพระองค์และให้ได้เห็นองค์ผู้ชอบธรรมและให้ได้ยินพระดำรัสจากพระโอษฐ์ของพระองค์ 15ท่านจะเป็นพยานฝ่ายพระองค์แก่คนทั้งปวงถึงสิ่งที่ท่านได้เห็นและได้ยิน 16และบัดนี้ท่านมัวรีรออะไร? จงลุกขึ้นรับบัพติศมาและชำระล้างบาปทั้งหลายของท่านโดยร้องออกพระนามของพระองค์’

17“เมื่อข้าพเจ้ากลับมาที่กรุงเยรูซาเล็มขณะกำลังอธิษฐานอยู่ในพระวิหารข้าพเจ้าก็เข้าสู่ภวังค์ 18และเห็นองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสว่า ‘เร็วเข้า! จงออกไปจากกรุงเยรูซาเล็มทันทีเพราะพวกเขาจะไม่ยอมรับคำพยานของเจ้าเกี่ยวกับเรา’

19“ข้าพเจ้าทูลตอบว่า ‘พระองค์เจ้าข้า คนเหล่านี้รู้อยู่ว่าข้าพระองค์ได้ไปยังธรรมศาลาต่างๆ เพื่อจับกุมคุมขังและโบยตีบรรดาผู้ที่เชื่อในพระองค์ 20และเมื่อสเทเฟนพยาน22:20 หรือผู้พลีชีพเพื่อความเชื่อ ของพระองค์ถูกฆ่าตาย ข้าพระองค์ก็ยืนอยู่ที่นั่นเห็นชอบในการนั้นและเฝ้าเสื้อผ้าให้คนที่ฆ่าสเทเฟน’

21“แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าจึงตรัสกับข้าพเจ้าว่า ‘ไปเถิด เราจะส่งเจ้าไปไกลไปยังคนต่างชาติ’ ”

เปาโลพลเมืองโรมัน

22ฝูงชนฟังเปาโลพูดมาถึงตอนนี้ก็ร้องตะโกนว่า “กำจัดเขาเสียจากแผ่นดิน! คนเช่นนี้ไม่ควรมีชีวิตอยู่!”

23ขณะที่พวกเขากำลังร้องตะโกนถอดเสื้อคลุมออกและซัดฝุ่นขึ้นไปในอากาศ 24นายพันสั่งให้นำเปาโลเข้าไปในกองทหาร เขาสั่งให้เฆี่ยนเปาโลและไต่สวนหาสาเหตุที่ทำให้ประชาชนร้องตะโกนใส่เปาโลเช่นนั้น 25เมื่อพวกเขาจับเปาโลขึงจะเฆี่ยนเปาโลกล่าวกับนายร้อยซึ่งยืนอยู่ที่นั่นว่า “เป็นการถูกต้องตามกฎหมายหรือที่จะเฆี่ยนพลเมืองโรมันซึ่งยังไม่ได้ถูกตัดสินว่ามีความผิด?”

26เมื่อนายร้อยได้ยินเช่นนั้นก็ไปรายงานนายพันพร้อมกับถามว่า “ท่านจะทำอะไรกันนี่? ชายผู้นี้เป็นพลเมืองโรมัน”

27นายพันไปหาเปาโลและถามว่า “จงบอกเรามา ท่านเป็นพลเมืองโรมันหรือ?”

เปาโลตอบว่า “ใช่”

28นายพันจึงว่า “เราต้องจ่ายเงินจำนวนมากกว่าจะได้สัญชาติโรมัน”

เปาโลตอบว่า “แต่ข้าพเจ้าเป็นพลเมืองโรมันโดยกำเนิด”

29บรรดาผู้ที่จะไต่สวนเปาโลจึงผละไปทันที นายพันเองก็ตกใจที่ได้สั่งล่ามโซ่เปาโลซึ่งเป็นพลเมืองโรมัน

ต่อหน้าสภาแซนเฮดริน

30วันรุ่งขึ้นเนื่องจากอยากรู้ให้แน่ชัดว่าทำไมพวกยิวกล่าวหาเปาโลนายพันจึงสั่งปล่อยเขาและเรียกประชุมพวกหัวหน้าปุโรหิตกับทั้งสภาแซนเฮดรินจากนั้นก็นำเปาโลมายืนอยู่ต่อหน้าพวกเขา