New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 19:1-41

ጳውሎስ በኤፌሶን

1አጵሎስ በቆሮንቶስ በነበረበት ጊዜ፣ ጳውሎስ በላይኛው አገር ዐልፎ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ በዚያም አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን አግኝቶ፣ 2“ባመናችሁ19፥2 ወይም ካመናችሁ በኋላ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን?” አላቸው።

እነርሱም፣ “አልተቀበልንም፤ እንዲያውም መንፈስ ቅዱስ መኖሩን እንኳ አልሰማንም” አሉት።

3ጳውሎስም፣ “ታዲያ፣ በምን ተጠመቃችሁ?” አላቸው።

እነርሱም፣ “የዮሐንስን ጥምቀት” አሉት።

4ጳውሎስም፣ “የዮሐንስ ጥምቀትማ የንስሓ ጥምቀት ነበር፤ ዮሐንስም ራሱ ሰዎች ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ እንዲያምኑ ተናግሮአል” አላቸው። 5እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ። 6ጳውሎስም እጁን በላያቸው በጫነ ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤ በሌሎች ቋንቋዎች19፥6 ወይም ልሳን ተናገሩ፤ ትንቢትም ተናገሩ። 7ሰዎቹም በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ያህል ነበሩ።

8ጳውሎስም ወደ ምኵራብ እየገባ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያሳመናቸው ሦስት ወር ሙሉ ምንም ሳይፈራ ፊት ለፊት ይናገር ነበር። 9አንዳንዶቹ ግን ግትር በመሆን፣ ለማመን ፈቃደኞች አልነበሩም፤ የጌታንም መንገድ በገሃድ ያጥላሉ ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ ትቶአቸው ሄደ፤ ደቀ መዛሙርትንም ለብቻቸው ወስዶ በጢራኖስ የትምህርት አዳራሽ ውስጥ በየዕለቱ ያነጋግራቸው ነበር። 10ይህን ማድረጉንም ሁለት ዓመት ስለ ቀጠለ፣ በእስያ አውራጃ ይኖሩ የነበሩት የአይሁድና የግሪክ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ለመስማት ቻሉ።

11እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ እጅግ የሚያስደንቅ ታምራትን ያደርግ ነበር፤ 12መሐረብ ወይም ሰውነቱን የነካ ጨርቅ እንኳ ወደ ሕመምተኞች ሲወስዱ በሽታቸው ይለቃቸው ነበር፤ ርኵሳን መናፍስትም ይወጡ ነበር።

13እየዞሩ አጋንንትን ያስወጡ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶቹ፣ “ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ ስም እንድትወጡ አዛችኋለሁ” እያሉ የጌታን የኢየሱስን ስም ርኵሳን መናፍስት በያዟቸው ሰዎች ላይ ለመጥራት ሞከሩ፤ 14የአይሁዳዊው የካህናቱ አለቃ የአስቄዋ ሰባት ወንዶች ልጆችም ይህንኑ ያደርጉ ነበር። 15ርኩስ መንፈሱም፣ “ኢየሱስን ዐውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም ዐውቀዋለሁ፤ እናንተ ግን እነማን ናችሁ?” አላቸው። 16ከዚያም ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው ዘሎ ያዛቸው፤ በረታባቸውም፤ እጅግ ስላየለባቸውም ቤቱን ጥለው ዕራቁታቸውን ሸሹ።

17ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት፣ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ሁሉ ዘንድ በታወቀ ጊዜ፣ ሁሉም ፍርሀት ያዛቸው፤ በዚህም የጌታ የኢየሱስ ስም ተከበረ። 18ካመኑትም ሰዎች ብዙዎቹ እየቀረቡ ክፉ ሥራቸውን በግልጥ ተናዘዙ፤ 19ሲጠነቁሉ ከነበሩትም መካከል ብዙዎች መጽሐፋቸውን ሰብስበው በማምጣት በሕዝብ ፊት አቃጠሉ፤ ዋጋቸውም ሲሰላ አምሳ ሺህ ብር ያህል ሆኖ ተገኘ። 20በዚህ ሁኔታ የጌታ ቃል በኀይል እያደገና እያሸነፈ ሄደ።

21ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ በኩል ዐልፎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ ወስኖ፣ “እዚያ ከደረስሁ በኋላ ሮምን ደግሞ ማየት አለብኝ” አለ። 22ከረዳቶቹም ሁለቱን፣ ጢሞቴዎስንና ኤርስጦንን፣ ወደ መቄዶንያ ልኮ እርሱ ራሱ ግን በእስያ አውራጃ ጥቂት ቀን ተቀመጠ።

በኤፌሶን የተነሣው ሁከት

23በዚህ ጊዜ፣ ስለ ጌታ መንገድ ታላቅ ሁከት ተፈጠረ። 24ድሜጥሮስ የተባለ አንድ የብር አንጥረኛ የአርጤምስን ቤተ መቅደስ ምስሎች ከብር ቀጥቅጦ እየሠራ ለሠራተኞቹ የሚያስገኘው ገቢ ቀላል አልነበረም። 25እርሱም እነዚህን ሠራተኞችና በተመሳሳይ ሙያ የሚተዳደሩትን ሌሎቹን ሰዎች በአንድነት ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፤ “ሰዎች ሆይ፤ ይህ ሥራ ጥሩ ገቢ እንደሚያስገኝልን ታውቃላችሁ። 26ይህ ጳውሎስ የተባለ ሰው በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የእስያ አውራጃ የሚገኘውን በርካታ ሕዝብ እያሳመነ እንዳሳታቸው ይኸው የምታዩትና የምትሰሙት ነገር ነው፤ በሰው እጅ የተሠሩ አማልክት በፍጹም አማልክት እንዳልሆኑ ይናገራልና። 27የዚህ የሥራችን መልካም ስም ከመጒደፉም በላይ፣ መላው እስያና ዓለም የሚያመልካት የታላቋ አርጤምስ ቤተ መቅደስም ዋጋ ቢስ ይሆናል፤ ደግሞም ገናናው ክብሯ ይዋረዳል።”

28ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ክፉኛ ተቈጥተው፣ “የኤፌሶኗ አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ይጮኹ ጀመር። 29ወዲያውም በከተማው ሁሉ ሁከት ተነሣ፤ ሕዝቡም አንድ ላይ በማበር የመቄዶንያ ተወላጅ የሆኑትንና ከጳውሎስ ጋር ይጓዙ የነበሩትን ጓደኞቹን፣ ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ይዘው ወደ ጨዋታ ማሳያው ስፍራ እየሮጡ ገቡ። 30ጳውሎስም ወጥቶ ሕዝቡ ፊት ለመቅረብ ፈልጎ ነበር፤ ደቀ መዛሙርት ግን ከለከሉት። 31ከአውራጃው ባለ ሥልጣኖች አንዳንድ ወዳጆቹ እንኳ፣ ጳውሎስ ወደ ጨዋታ ማሳያው ስፍራ ደፍሮ እንዳይገባ ሰው ልከው ለመኑት።

32ጉባኤውም ተበጣብጦ፣ አንዱ አንድ ነገር ሲናገር ሌላውም ሌላ እየተናገረ ይጯጯኽ ነበር፤ አብዛኛውም ሰው ለምን እዚያ እንደ ተሰበሰበ እንኳ አያውቅም ነበር። 33አይሁድም እስክንድሮስን ከሕዝቡ መካከል ገፍተው ወደ ፊት ባወጡት ጊዜ፤ አንዳንዶቹ እንዲናገርላቸው ጮኹ፤ እርሱም ሊከራከርላቸው ፈልጎ ዝም እንዲሉ በምልክት ጠቀሳቸው። 34ነገር ግን እርሱ አይሁዳዊ መሆኑን ባወቁ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ፣ “የኤፌሶኗ አርጤምስ ታላቅ ናት” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ።

35የከተማዪቱም ዋና ጸሓፊ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አለ፤ “የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፤ የታላቋ የአርጤምስ ቤተ መቅደስና ከሰማይ የወረደው ምስሏ ጠባቂ የኤፌሶን ከተማ ሕዝብ መሆኑን የማያውቅ ማን አለ? 36ስለዚህ፣ ይህ ሐቅ የማይካድ እንደ መሆኑ መጠን፣ ልትረጋጉና አንዳች ነገር በጥድፊያ ከመፈጸም ልትጠቡ ይገባችኋል። 37እነዚህን ሰዎች ቤተ መቅደስን ሳይዘርፉ ወይም አምላካችን በሆነችው ላይ የስድብ ቃል ሳይሰነዝሩ ይዛችሁ እዚህ ድረስ እንዲያው አምጥታችኋቸዋል። 38እንግዲህ፣ ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉት አንጥረኞች በማንም ላይ አቤቱታ ካላቸው፣ ፍርድ ቤቱ ክፍት ነው፤ ዳኞችም አሉ፤ ክስ ማቅረብ ይችላሉ። 39ከዚህ ሌላ ልታቀርቡ የፈለጋችሁት ነገር ካለ፣ በሕጋዊ ጉባኤ ይታያል። 40አለበለዚያ ዛሬ ስለ ሆነው ነገር፣ በሁከት አነሣሽነት እንዳንከሰስ ያሠጋናል፤ አጥጋቢ ምክንያት ስለሌለንም፣ ስለ ሁከቱ ብንጠየቅበት መልስ መስጠት አንችልም።” 41ይህን ከተናገረ በኋላም ጉባኤው እንዲበተን አደረገ።

Thai New Contemporary Bible

กิจการของอัครทูต 19:1-41

เปาโลในเมืองเอเฟซัส

1ขณะอปอลโลอยู่ที่เมืองโครินธ์เปาโลเดินทางไปตามถนนที่ผ่านดินแดนด้านในและมาที่เมืองเอเฟซัส เขาพบสาวกบางคนที่นั่น 2และถามว่า “เมื่อ19:2 หรือหลังจาก ท่านเชื่อท่านได้รับพระวิญญาณบริสุทธิ์หรือไม่?”

พวกเขาตอบว่า “ไม่ เราไม่เคยแม้แต่ได้ยินว่ามีพระวิญญาณบริสุทธิ์”

3ดังนั้นเปาโลจึงถามว่า “ถ้าเช่นนั้น ท่านได้รับบัพติศมาอะไร?”

พวกเขาตอบว่า “บัพติศมาของยอห์น”

4เปาโลจึงกล่าวว่า “บัพติศมาของยอห์นคือบัพติศมาที่แสดงการกลับใจใหม่ ยอห์นได้บอกประชาชนให้เชื่อในพระองค์ผู้ซึ่งมาภายหลังท่านคือให้เชื่อในพระเยซู” 5เมื่อได้ฟังเช่นนี้พวกเขาก็รับบัพติศมาเข้าใน19:5 หรือบัพติศมาในพระนามขององค์พระเยซูเจ้า 6เมื่อเปาโลวางมือบนพวกเขาพระวิญญาณบริสุทธิ์ก็เสด็จมายังคนเหล่านี้ พวกเขาก็พูดภาษาแปลกๆ19:6 หรือภาษาอื่นๆและพยากรณ์ 7คนทั้งหมดนี้เป็นผู้ชายมีประมาณสิบสองคน

8เปาโลเข้าไปในธรรมศาลาและกล่าวด้วยใจกล้าเป็นเวลาสามเดือน ชี้แจงเรื่องอาณาจักรของพระเจ้าด้วยเหตุผลอย่างน่าเชื่อถือ 9แต่บางคนใจดื้อด้านไม่ยอมเชื่อและพูดให้ร้าย “ทางนั้น” ต่อหน้าสาธารณชน ดังนั้นเปาโลจึงพาพวกสาวกแยกไปและพวกเขาไปอภิปรายกันที่ห้องประชุมของทีรันนัสทุกวัน 10เขาทำเช่นนี้อยู่สองปีจนชาวยิวและชาวกรีกทั้งปวงในแคว้นเอเชียได้ยินพระวจนะขององค์พระผู้เป็นเจ้า

11พระเจ้าทรงกระทำการอัศจรรย์ที่พิเศษกว่าปกติผ่านทางเปาโล 12กระทั่งเมื่อนำผ้าเช็ดหน้ากับผ้ากันเปื้อนที่แตะถูกตัวเขาไปวางบนตัวคนเจ็บป่วย คนเหล่านั้นก็จะหายโรคและวิญญาณชั่วก็ออกไปจากเขา

13ชาวยิวบางคนไปตามที่ต่างๆ แล้วขับไล่วิญญาณชั่วโดยพยายามออกพระนามขององค์พระเยซูเจ้าเหนือคนที่ถูกผีสิง พวกเขาจะสั่งว่า “ในพระนามพระเยซูซึ่งเปาโลประกาศ เราสั่งเจ้าให้ออกมา” 14บุตรชายเจ็ดคนของเสวาหัวหน้าปุโรหิตชาวยิวก็ทำเช่นนี้ 15วันหนึ่งวิญญาณชั่วตอบพวกเขาว่า “พระเยซูน่ะข้ารู้จักและข้าก็เคยได้ยินเรื่องเปาโลแต่พวกเจ้าเป็นใครกัน?” 16แล้วคนที่มีวิญญาณชั่วสิงก็กระโจนเข้าใส่และเอาชนะพวกเขาทั้งหมด คนนั้นทุบตีพวกเขาจนต้องเผ่นหนีจากบ้านทั้งๆ ที่เปลือยกายและเลือดไหล

17เมื่อเรื่องนี้ไปถึงหูชาวยิวและชาวกรีกในเมืองเอเฟซัสพวกเขาทั้งปวงพากันเกรงกลัวจับใจและพระนามขององค์พระเยซูเจ้าก็เป็นที่ยกย่องอย่างสูง 18บัดนี้หลายคนที่เชื่อมาสารภาพการกระทำที่ชั่วร้ายอย่างเปิดเผย 19คนที่ใช้เวทมนตร์คาถานำม้วนตำราของตนมาเผาทิ้งต่อหน้าสาธารณชน ตำราเหล่านั้นรวมแล้วคิดเป็นเงินถึง 50,000 แดรกมา19:19 1 แดรกมาคือเหรียญเงิน 1 เหรียญมีค่าเท่ากับค่าแรง 1 วัน 20โดยเหตุนี้พระวจนะขององค์พระผู้เป็นเจ้าจึงแพร่ออกไปอย่างกว้างไกลและเกิดผลมากยิ่งขึ้น

21ภายหลังเหตุการณ์เหล่านี้เปาโลตกลงใจว่าจะไปกรุงเยรูซาเล็มโดยผ่านทางแคว้นมาซิโดเนียและอาคายา เขากล่าวว่า “หลังจากได้ไปที่นั่นแล้วเราต้องไปเยี่ยมกรุงโรมด้วย” 22เปาโลส่งผู้ช่วยของเขาสองคนคือทิโมธีกับเอรัสทัสไปแคว้นมาซิโดเนียขณะที่เขาอยู่ในแคว้นเอเชียต่ออีกหน่อยหนึ่ง

การจลาจลในเมืองเอเฟซัส

23ครั้งนั้นเกิดเหตุวุ่นวายครั้งใหญ่เกี่ยวกับ “ทางนั้น” 24ช่างเงินคนหนึ่งชื่อเดเมตริอัสเป็นคนทำรูปจำลองสถานบูชาของเทวีอารเทมิสด้วยเงิน ซึ่งทำรายได้ให้พวกช่างฝีมือไม่น้อย 25เขาเรียกประชุมช่างเหล่านั้นกับคนงานในธุรกิจที่เกี่ยวข้องมาและกล่าวว่า “ท่านทั้งหลาย ท่านย่อมทราบอยู่ว่าธุรกิจนี้สร้างรายได้ให้เราอย่างมาก 26ท่านก็ได้เห็นและได้ยินที่เปาโลคนนี้ชักจูงผู้คนมากมายให้หลงทางทั้งในเอเฟซัสนี้กับทั่วแคว้นเอเชียก็ว่าได้ เขาพูดว่ารูปเคารพที่มนุษย์สร้างขึ้นไม่ได้เป็นเทพเจ้าเลย 27สิ่งนี้เป็นอันตรายเพราะไม่เพียงแต่จะทำให้การค้าของเราเสียชื่อ ยังทำให้ผู้คนเสื่อมศรัทธาในวิหารของเทวีอารเทมิสผู้ยิ่งใหญ่ด้วย และเทวีเองที่ผู้คนกราบไหว้ทั่วแคว้นเอเชียและทั่วโลกจะถูกปล้นความยิ่งใหญ่อันศักดิ์สิทธิ์ของพระนางไป”

28เมื่อพวกเขาทั้งหลายได้ยินดังนั้นก็โกรธจัดและเริ่มตะโกนว่า “เทวีอารเทมิสของชาวเอเฟซัสนั้นยิ่งใหญ่!” 29ไม่ช้าทั่วทั้งเมืองก็โกลาหล ผู้คนจับกายอัสกับอาริสทารคัสผู้เป็นเพื่อนร่วมทางของเปาโลจากแคว้นมาซิโดเนียและพากันกรูเข้าไปในที่ซึ่งคนทั้งเมืองใช้ประชุมกัน 30เปาโลอยากจะแสดงตัวต่อหน้าฝูงชนแต่พวกสาวกไม่ยอม 31แม้แต่เจ้าหน้าที่บางคนของแคว้นนั้นซึ่งเป็นเพื่อนของเปาโลยังส่งข่าวมาขอร้องไม่ให้เขาเข้าไปในสถานที่นั้น

32ที่ประชุมวุ่นวายมากบางคนตะโกนว่าอย่างนี้บางคนว่าอย่างนั้น ประชาชนส่วนใหญ่ไม่รู้ด้วยซ้ำว่าตัวเองไปที่นั่นทำไม 33พวกยิวผลักอเล็กซานเดอร์ให้ออกไปข้างหน้าและบางคนในฝูงชนก็ตะโกนแนะว่าเขาควรพูดอะไร เขาโบกมือให้เงียบเพื่อจะแก้ต่างต่อหน้าประชาชน 34แต่เมื่อพวกนั้นเห็นว่าเขาเป็นยิวก็ร้องเป็นเสียงเดียวกันราวสองชั่วโมงว่า “เทวีอารเทมิสของชาวเอเฟซัสนั้นยิ่งใหญ่!”

35เจ้าหน้าที่ของเมืองนั้นทำให้ฝูงชนเงียบแล้วกล่าวว่า “ชนชาวเอเฟซัส ใครๆ ก็รู้ไม่ใช่หรือว่าเมืองเอเฟซัสคือผู้ดูแลวิหารของเทวีอารเทมิสผู้ยิ่งใหญ่ตลอดจนเทวรูปของพระนางซึ่งตกลงมาจากฟ้าสวรรค์? 36ฉะนั้นในเมื่อข้อเท็จจริงเหล่านี้ไม่อาจปฏิเสธได้ท่านทั้งหลายก็ควรนิ่งสงบ ไม่ทำอะไรวู่วาม 37พวกท่านนำตัวคนเหล่านี้มาที่นี่ทั้งๆ ที่พวกเขาก็ไม่ได้ปล้นวิหารต่างๆ หรือลบหลู่เทวีของเรา 38แล้วถ้าเดเมตริอัสกับพวกพ้องช่างฝีมือมีเรื่องจะร้องทุกข์เกี่ยวกับใครคนใดคนหนึ่งศาลก็เปิดอยู่และผู้ตรวจการก็มี พวกเขาสามารถฟ้องร้องได้ 39หากท่านมีข้อหาอื่นใดก็ต้องตกลงกันในที่ประชุมตามกฎหมาย 40เหตุการณ์วันนี้ทำให้เราเสี่ยงต่อการตกเป็นผู้ก่อการจลาจลเพราะเราไม่มีเหตุผลที่จะอธิบายความวุ่นวายครั้งนี้” 41หลังจากกล่าวเช่นนี้แล้วเขาก็ให้เลิกชุมนุม