New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 15:1-41

የኢየሩሳሌም ጉባኤ

1አንዳንድ ሰዎችም ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ወርደው፣ “በሙሴ ሥርዐት መሠረት ካልተገረዛችሁ ልትድኑ አትችሉም” በማለት ወንድሞችን ማስተማር ጀመሩ። 2ይህም ጳውሎስንና በርናባስን ከእነርሱ ጋር ወደ ከረረ ጠብና ክርክር ውስጥ ከተታቸው። ስለዚህ ጳውሎስና በርናባስ ከሌሎች አንዳንድ ምእምናን ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ስለ ዚሁ ጒዳይ ሐዋርያትንና ሽማግሌዎችን እንዲጠይቁ ተወሰነ። 3ቤተ ክርስቲያኒቱም እግረ መንገዳቸውን በፊንቄና በሰማርያ በኩል እንዲያልፉ ላከቻቸው፤ እነርሱም በእነዚህ ቦታዎች ለነበሩት የአሕዛብን መመለስና ማመን ነገሯቸው፤ ወንድሞችም ሁሉ በዚህ እጅግ ደስ አላቸው። 4ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም፣ ቤተ ክርስቲያንና ሐዋርያት እንዲሁም ሽማግሌዎች ተቀበሏቸው፤ የተላኩትም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሠራውን ሁሉ ነገሯቸው።

5ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው በመቆም፣ “አሕዛብ እንዲገረዙና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው” አሉ።

6ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ይህንኑ ጒዳይ ለማጤን ተሰበሰቡ። 7ከብዙ ክርክር በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞች ሆይ፤ እግዚአብሔር ከጥቂት ጊዜ በፊት በእናንተ መካከል እኔን መርጦ፣ አሕዛብ የወንጌልን ቃል ከእኔ አንደበት ሰምተው እንዲያምኑ ማድረጉን ታውቃላችሁ። 8ልብን የሚያውቅ አምላክ ለእኛ እንደ ሰጠን ሁሉ፣ ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት የተቀበላቸው መሆኑን መሰከረላቸው፤ 9ልባቸውንም በእምነት በማንጻት በእኛና በእነርሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም። 10እንግዲህ፣ አባቶቻችንም እኛም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ? 11እኛም የዳንነው ልክ እንደ እነርሱ በጌታ በኢየሱስ ጸጋ መሆኑን እናምናለን።”

12ጉባኤውም በሙሉ ዝም ብሎ፣ በርናባስና ጳውሎስ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት በአሕዛብ መካከል ስላደረጋቸው ታምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ሲናገሩ ያዳምጣቸው ነበር። 13እነርሱም ተናግረው ሲጨርሱ፣ ያዕቆብ ተነሥቶ በመቆም እንዲህ አለ፤ “ወንድሞች ሆይ፤ ስሙኝ፤ 14እግዚአብሔር ከአሕዛብ ወገን ለእርሱ የሚሆነውን ሕዝብ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን15፥14 እርሱም ጴጥሮስ ነው። አስረድቶናል። 15እንዲህ ተብሎ የተጻፈው የነቢያቱም ቃል ከዚህ ጋር ይስማማል፤

16“ ‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤

የፈረሰውን የዳዊትን ቤት እገነባለሁ።

ፍርስራሹን መልሼ አቆማለሁ፤

እንደ ገናም እሠራዋለሁ፤

17ይኸውም የቀሩት ሰዎች ጌታን እንዲፈልጉ፣

ስሜን የተሸከሙ አሕዛብም እንዲሹኝ ነው፤

እነዚህን ያደረገ ጌታ እንዲህ ይላል፤’

18እነርሱም ከጥንት ጀምሮ የታወቁ ናቸው።15፥17-18 አንዳንድ ቅጆች … ለጌታ ከጥንት ጀምሮ የታወቀው የራሱ ሥራ ነው ይላሉ።

19“ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን አሕዛብ እንዳናስጨንቃቸው ይህ የእኔ ብያኔ ነው። 20ይልቁን በጣዖት ከረከሰ ነገር፣ ከዝሙት ርኵሰት፣ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ ከመብላትና ደም ከመመገብ እንዲርቁ ልንጽፍላቸው ይገባል፤ 21የሙሴ ሕግማ ከጥንት ጀምሮ በየሰንበቱ በምኵራብ ሲነበብና በየከተማው ሲሰበክ ኖሮአልና።”

ላመኑት አሕዛብ ከጉባኤው የተላከ ደብዳቤ

22በዚህ ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከመላው ቤተ ክርስቲያን ጋር ሆነው ከመካከላቸው አንዳንድ ሰዎችን መርጠው፣ ከጳውሎስና ከበርንባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ ከወንድሞችም መካከል ዋነኛ የነበሩትን በርስያን የተባለውን ይሁዳንና ሲላስን መረጡ፤ 23በእነርሱም እጅ ቀጥሎ ያለውን ደብዳቤ ላኩ፤

ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ከሐዋርያትና ከሽማግሌዎች፤

ከአሕዛብ ወገን አምነው በአንጾኪያ፣ በሶሪያና በኪልቅያ ለሚገኙ ወንድሞች፤

ሰላምታችን ይድረሳችሁ።

24አንዳንድ ሰዎች ያለ እኛ ፈቃድ ከእኛ ዘንድ ወጥተው በንግግራቸው ልባችሁን እንዳወኩና እንዳናወጧችሁ ሰምተናል። 25ስለዚህ ጥቂት ሰዎች መርጠን ከተወዳጆቹ ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ ለመላክ ሁላችንም ተስማምተናል፤ 26በርናባስና ጳውሎስም ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ናቸው። 27ስለዚህ እኛ የጻፍነውን በቃል እንዲያረጋግጡላችሁ፣ እነሆ፤ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። 28ከእነዚህ አስፈላጊ ነገሮች በስተቀር ሌላ ተጨማሪ ሸክም እንዳ ንጭንባችሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ለእኛም መልካም መስሎ ታይቶናል፤ ይኸውም፦ 29ለጣዖት ከተሠዋ ነገር፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከዝሙት ርኵሰት እንድትርቁ ነው። ከእነዚህ ዐይነት ነገሮች ብትርቁ ለእናንተ መልካም ነው።

ደኅና ሁኑ።

30የተላኩትም ሰዎች ከተሰናበቱ በኋላ ወደ አንጾኪያም ወረዱ፤ በዚያም የምእመናኑን ጉባኤ በአንድነት ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጧቸው። 31ሕዝቡም ካነበቡት በኋላ አበረታታች በሆነው ቃሉ ደስ ተሰኙ። 32ይሁዳና ሲላስም ራሳቸው ነቢያት ስለ ነበሩ፣ ወንድሞችን ብዙ ንግግር በማድረግ መከሯቸው፤ አበረቷቸውም። 33በዚያም ጥቂት ጊዜ ከቈዩ በኋላ፣ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ላኳቸው ሰዎች ተመለሱ። 34ሲላስ ግን እዚያው ለመቅረት ወሰነ15፥34 አንዳንድ ቅጆች ይህ ቁጥር የላቸውም።35ጳውሎስና በርናባስም ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋር ሆነው የጌታን ቃል እያስተማሩና እየሰበኩ በአንጾኪያ ተቀመጡ።

ጳውሎስና በርናባስ በሐሳብ ተለያዩ

36ጳውሎስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በርናባስን፣ “ተነሣና የጌታን ቃል ወደ ሰበክንባቸው ከተሞች ሁሉ እንሂድ፤ በዚያ ያሉ ወንድሞችም በምን ሁኔታ እንዳሉ ለማወቅ እንጐብኛቸው” አለው። 37በርናባስም ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ አብሮአችው እንዲሄድ ፈለገ፤ 38ጳውሎስ ግን እርሱን ይዞ ለመሄድ አልፈለገም፤ ምክንያቱም፣ ቀደም ሲል ማርቆስ ከእነርሱ ተለይቶ በጵንፍልያ ስለ ቀረና ወደ ሥራ አብሮአቸው ስላልሄደ ነበር። 39እንዲህ የከረረ አለመግባባት በመካከላቸው ስለ ተፈጠረ እርስ በርስ ተለያዩ፤ ስለዚህ በርናባስ ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። 40ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለጌታ ጸጋ ዐደራ ከሰጡት በኋላ ተለይቶአቸው ሄደ፤ 41አብያተ ክርስቲያናትንም እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ በኩል ዐለፈ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

使徒行傳 15:1-41

耶路撒冷會議

1有幾個從猶太下來的人教導弟兄們說:「你們若不照著摩西的規條接受割禮,就不能得救。」 2保羅巴拿巴為這件事與他們激烈地辯論,最後大家決定派保羅巴拿巴和幾個當地的信徒上耶路撒冷去跟使徒和長老討論這件事。

3於是教會為他們送行。他們經過腓尼基撒瑪利亞,沿途報告外族人悔改信主的消息,弟兄姊妹都大受鼓舞。 4他們到了耶路撒冷,受到教會、使徒和長老的接待,並詳述了上帝藉他們所做的一切事。 5有幾個信了主的法利賽人站起來說:「外族的信徒必須接受割禮,而且還要遵守摩西的律法。」

6使徒和長老們聚集商議這個問題。 7經過許多辯論之後,彼得站起來對大家說:「弟兄們,你們都知道,上帝早已在你們當中揀選我去向外族人傳道,讓他們也可以聽到福音並信主。 8洞悉人心的上帝把聖靈賜給他們,正如賜給我們一樣,以表明祂也接納外族人。 9上帝對他們和我們一視同仁,祂因他們的信心而潔淨了他們的心靈。 10現在你們為什麼要試探上帝,把我們祖先和我們不能負的重擔強加在這些門徒身上? 11我們相信,他們和我們一樣都是靠主耶穌的恩典得救。」

12眾人都沉默不語,繼續聽巴拿巴保羅敘述上帝藉著他們在外族人中所行的神蹟奇事。 13他們報告完了,雅各站起來說:「弟兄們,請聽我說。 14剛才西門講述了上帝當初如何眷顧外族人,從他們當中揀選人歸在祂的名下。 15這完全與眾先知的話相符,正如聖經上說,

16『此後,我要回來重建已傾覆的大衛王朝,

將它從廢墟中重建、恢復,

17好叫其餘的百姓,

就是凡歸在我名下的外族人都尋求主。』

這是上帝說的, 18祂從亙古就顯明了這事。

19「所以,我認為不應該為難那些信上帝的外族人。 20我們只須寫信吩咐他們遠避被偶像玷污之物,不可淫亂,不可吃血和勒死的牲畜。 21因為自古以來,在各城都有人宣講摩西的律法,每逢安息日,都有人在會堂裡誦讀。」

給外族信徒的信

22最後,使徒、長老和全教會都決定從他們當中選派代表,隨保羅巴拿巴安提阿。他們選了別號巴撒巴猶大西拉,這兩位都是教會的領袖。 23他們帶去的書信這樣說:「安提阿敘利亞基利迦的外族弟兄姊妹,你們的弟兄——眾使徒和長老向你們問安!

24「聽說有幾個人從我們這裡去了你們那裡,教導你們必須接受割禮並遵守摩西的律法15·24 有古卷無「教導你們必須接受割禮並遵守摩西的律法。」。他們的言論使你們大感困惑。其實我們從來沒有授權他們這樣做。 25所以我們一致決定選派代表,隨我們敬愛的巴拿巴保羅去你們那裡。 26他們二人為我們主耶穌基督的緣故已將生死置之度外。 27我們選派猶大西拉兩位代表跟他們一起去,向你們報告我們的決定。 28因為聖靈和我們都認為不應把重擔加在你們身上。但請務必注意以下幾件事, 29要遠避祭拜偶像的事,不可吃血,不可吃勒死的牲畜,不可淫亂。你們一一遵守這些事就好了。祝平安!」

30他們奉命下到安提阿,召集眾人,交付書信。 31眾人讀過這封信之後,都因信中勸勉的話而歡喜。 32猶大西拉也是先知,他們講了許多勉勵、堅立弟兄姊妹的話。 33住了些日子後,安提阿的弟兄姊妹以平安的祝福為他們送行,讓他們回耶路撒冷覆命。 34西拉決定留在那裡。15·34 有古卷無「但西拉決定留在那裡。」 35保羅巴拿巴則繼續留在安提阿,與許多人一起教導、傳揚上帝的道。

保羅與巴拿巴分手

36過了一些日子,保羅巴拿巴說:「我們回到曾傳過福音的各城鎮去探望弟兄姊妹吧,好知道他們的情況。」 37巴拿巴想要帶約翰·馬可同去, 38保羅堅持不帶他同行,因為他在旁非利亞離開了他們,沒有和他們一起做工。

39二人激烈地爭執起來,僵持不下,只好分道揚鑣。巴拿巴約翰·馬可一同乘船去塞浦路斯40保羅則選了西拉同行,弟兄姊妹把他們交託在主的恩典中。 41保羅走遍了敘利亞基利迦,鞏固當地的各教會。