New Amharic Standard Version

ሆሴዕ 7:1-16

1እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣

የኤፍሬም ኀጢአት፣

የሰማርያም ክፋት ይገለጣል።

እነርሱ ያጭበረብራሉ፤

ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤

ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።

2ነገር ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ፣

እነርሱ አይገነዘቡም፤

ኀጢአታቸው ከቦአቸዋል፤

ሁልጊዜም በፊቴ ናቸው።

3“ንጉሡን በክፋታቸው፣

አለቆችንም በሐሰታቸው ያስደስታሉ።

4ሊጡ ቦክቶ ኩፍ እንደሚል፣

ዳቦ ጋጋሪው እሳት መቈስቈስ እስከማያስፈልገው ድረስ፣

እንደሚነድ ምድጃ፣

ሁሉም አመንዝራ ናቸው።

5በንጉሣችን የበዓል ቀን፣

አለቆች በወይን ጠጅ ስካር ጋሉ፤

እርሱም ከፌዘኞች ጋር ተባበረ።

6ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤

በተንኰል ይቀርቡታል፤

ቍጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ይጤሳል፤

እንደሚነድም እሳት በማለዳ ይንበለበላል።

7ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤

ገዦቻቸውን ፈጁ፤

ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤

ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም።

8“ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤

ኤፍሬም ያልተገላበጠ ቂጣ ነው።

9እንግዶች ጒልበቱን በዘበዙ፤

እርሱ ግን አላስተዋለም።

ጠጒሩም ሽበት አወጣ፤

እርሱ ግን ልብ አላለም።

10የእስራኤል ትዕቢት በራሱ ላይ መሰከረበት፤

ይህ ሁሉ ሆኖ ግን፣

ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤

እርሱንም አልፈለገም።

11ኤፍሬም በቀላሉ እንደምትታለል፣

አእምሮም እንደሌላት ርግብ ነው፤

አንድ ጊዜ ወደ ግብፅ ይጣራል፤

ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አሦር ይዞራል።

12ሲበሩ፣ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤

እንደ ሰማይ ወፎችም ጐትቼ

አወርዳቸዋለሁ፤

ስለ ክፉ ሥራቸውም በጒባኤ መካከል እቀጣቸዋለሁ።

13ወዮ ለእነርሱ፤

ከእኔ ርቀው ሄደዋልና!

ጥፋት ይምጣባቸው!

በእኔ ላይ ዐምፀዋልና።

ልታደጋቸው ፈለግሁ፤

እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።

14ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፤

ነገር ግን በዐልጋቸው ላይ ሆነው ያለቅሳሉ።

ስለ እህልና ስለ አዲስ የወይን ጠጅ

ይሰበሰባሉ፤

ነገር ግን ከእኔ ዘወር ብለዋል።

15እኔ አሠለጠንኋቸው፤ አጠነከርኋቸውም፤

እነርሱ ግን አደሙብኝ።

16ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤

ዒላማውን እንደሳተ ቀስት ናቸው፤

መሪዎቻቸው ስለ ክፉ ቃላቸው፣

በሰይፍ ይወድቃሉ፤

በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር፣

መዘባበቻ ይሆናሉ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

何西阿書 7:1-16

「每當我要使子民復興的時候,

1每當我要醫治以色列的時候,

卻看見以法蓮的罪,撒瑪利亞7·1 撒瑪利亞」為北國以色列的首都,此處代指以色列。本卷書中下同。的惡。

他們行事詭詐;

盜賊進屋偷竊,強盜外出搶劫。

2他們沒有想到我記得他們的所有惡行。

如今他們的罪惡環繞他們,

都暴露在我面前。

3他們以罪惡取悅君王,

以謊言討好首領。

4他們都是通姦之徒7·4 通姦之徒」此處指以色列人背棄耶和華,祭拜偶像。

就像熱烘烘的烤爐,

從揉麵到麵團發起,

烤餅的人不用挑爐火。

5君王宴樂的時候,

首領們醉酒成病,

君王也與輕慢上帝的人聯手。

6他們的心如烤爐,燃燒著陰謀。

他們的怒氣如整夜悶燒的爐火,

早晨爆發出熊熊烈焰。

7他們像炙熱的烤爐,

吞滅他們的首領。

他們的君王都倒地而亡,

沒有一個向我求救。

8以法蓮與外族人混雜,

就像沒有翻過的餅7·8 沒有翻過的餅」指一面烤焦一面生的餅,不能食用,意義見下節。

9外族人耗盡了他的力量,

他卻茫然不知。

他頭髮斑白,

卻渾然不覺。

10以色列人被自己的傲慢指控,

他們卻不歸向他們的上帝耶和華,

也不去尋求祂。

11以法蓮像鴿子一樣愚蠢無知,

他們向埃及求救,又投奔亞述

12他們去的時候,

我要張網網住他們,

我要像打落飛鳥一樣打落他們。

我要按他們的惡行7·12 他們的惡行」希伯來文是「他們的會眾所聽到的」。懲罰他們。

13他們有禍了,

因為他們背棄我!

他們要被毀滅了,

因為他們背叛我!

我要救贖他們,

他們卻向我撒謊。

14他們沒有真心呼求我,

只是在床上哭號。

他們為求五穀和新酒而割傷自己,

卻背棄了我。

15我訓練他們,使他們臂膀強壯,

他們卻陰謀作惡抗拒我。

16他們回轉,卻不肯轉向至高者,

他們就像無用的斷弓。

他們的首領要因出言狂妄而喪身刀下,

成為埃及人的笑柄。