New Amharic Standard Version

ሆሴዕ 4:1-19

በእስራኤል ላይ የቀረበ ክስ

1በምድሪቱ በምትኖሩ በእናንተ ላይ

እግዚአብሔር የሚያቀርበው ክስ ስላለው፣

እናንት እስራኤላውያን ይህን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤

“ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤

እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።

2በዚያ ያለው ርግማን፣4፥2 መርገምን ያመለክታል መዋሸት፣ መግደል፣

መስረቅና ማመንዘር ብቻ ነው፤

ቃል ኪዳንን ሁሉ ያፈርሳሉ፤

ደም ማፍሰስና ግድያ ይበዛል።

3ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤4፥3 ወይም ደረቀች

በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤

የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣

የባሕርም ዓሦች አለቁ።

4“ነገር ግን ማንም ሰው አይከራከር፤

ማንም ሌላውን አይወንጅል፤

በካህናት ላይ ክስን እንደሚያቀርቡ፣

ሕዝብህ እንደዚያው ናቸውና።

5ቀንና ሌሊት ትደናበራላችሁ፤

ነቢያትም ከእናንተ ጋር ይደናበራሉ፤

ስለዚህ እናታችሁን አጠፋታለሁ፤

6ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል።

“ዕውቀትን ስለናቃችሁ፣

እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤

የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣

እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።

7ካህናት በበዙ ቊጥር፣

በእኔ ላይ የሚያደርጉት ኀጢአት በዝቶአል፤

ክብራቸውንም4፥7 ማሶሬቲክ የሚለው እንዲሁ ሲሆን የጥንት ዕብራውያን ጸሐፍት ትውፊት ግን ክብሬን ይላል በውርደት ለውጠዋል።4፥7 ሱርስትና የጥንት ዕብራውያን ጸሓፍት ትውፊት የሚሉት እንዲሁ ሲሆን ማሶሬቲክ ግን እለውጠዋለሁ ይላል

8የሕዝቤ ኀጢአት ለመብል ሆኖላቸዋል፤

ርኵሰታቸውንም እጅግ ወደዱ።

9ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤

ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤

እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።

10“ይበላሉ ግን አይጠግቡም፤

ያመነዝራሉ ግን አይበዙም፤

እግዚአብሔርን በመተው፣

ራሳቸውን 11ለአመንዝራነት፣

ለአሮጌና ለአዲስ የወይን ጠጅ አሳልፈው ሰጡ፤

በእነዚህም

12የሕዝቤ ማስተዋል ተወሰደ፤

ከዕንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቃሉ፤

ዘንጋቸውም ይመልስላቸዋል።

የአመንዝራነት መንፈስ ያስታቸዋል፤

ለአምላካቸውም ታማኝ አልሆኑም።

13በተራሮችም ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፤

መልካም ጥላ ባለው፣ በባሉጥ፣

በኮምቦልና በአሆማ ዛፍ ሥር፣

በኰረብቶችም ላይ የሚቃጠል ቊርባን ያቀርባሉ።

ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማዊ፣

ምራቶቻችሁም አመንዝራ ይሆናሉ።

14“ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ሲሆኑ፣

የልጆቻችሁም ሚስቶች ሲያመነዝሩ

አልቀጣቸውም።

ወንዶች ከጋለሞቶች ጋር ይሴስናሉ፤

ከቤተ ጣዖት ዘማውያን ጋር ይሠዋሉና፤

የማያስተውል ሕዝብ ወደ ጥፋት ይሄዳል!

15“እስራኤል ሆይ፤ አንቺ ብታመነዝሪም፣

ይሁዳ በበደለኛነት አትጠየቅ።

“ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤

ወደ ቤትአዌንም4፥15 ቤትአዌን የእግዚአብሔር ቤት የተባለችው ቤቴል ስትሆን፣ ያቃሉ ትርጒም የክፋት ቤት ማለት ነው። አትውጡ፤

‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁም አትማሉ።

16እስራኤላውያን እንደ እልኸኛ ጊደር፣

እልኸኞች ናቸው፤

ታዲያ እግዚአብሔር እነርሱን በመልካም መስክ ውስጥ እንዳሉ የበግ ጠቦቶች

እንዴት ያሰማራቸዋል?

17ኤፍሬም ከጣዖት ጋር ተጣምሮአል፤

እስቲ ተውት፤

18መጠጣቸው ባለቀ ጊዜ እንኳ፣

ዘማዊነታቸውን አያቆሙም፤

ገዦቻቸውም ነውርን አጥብቀው ይወዳሉ።

19ዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤

መሥዋዕቶቻቸውም ኀፍረት ያመጡባቸዋል።

New International Version – UK

Hosea 4:1-19

The charge against Israel

1Hear the word of the Lord, you Israelites,

because the Lord has a charge to bring

against you who live in the land:

‘There is no faithfulness, no love,

no acknowledgment of God in the land.

2There is only cursing,4:2 That is, to pronounce a curse on lying and murder,

stealing and adultery;

they break all bounds,

and bloodshed follows bloodshed.

3Because of this the land dries up,

and all who live in it waste away;

the beasts of the field, the birds in the sky

and the fish in the sea are swept away.

4‘But let no-one bring a charge,

let no-one accuse another,

for your people are like those

who bring charges against a priest.

5You stumble day and night,

and the prophets stumble with you.

So I will destroy your mother –

6my people are destroyed from lack of knowledge.

‘Because you have rejected knowledge,

I also reject you as my priests;

because you have ignored the law of your God,

I also will ignore your children.

7The more priests there were,

the more they sinned against me;

they exchanged their glorious God4:7 Syriac (see also an ancient Hebrew scribal tradition); Masoretic Text me; / I will exchange their glory for something disgraceful.

8They feed on the sins of my people

and relish their wickedness.

9And it will be: like people, like priests.

I will punish both of them for their ways

and repay them for their deeds.

10‘They will eat but not have enough;

they will engage in prostitution but not flourish,

because they have deserted the Lord

to give themselves 11to prostitution;

old wine and new wine

take away their understanding.

12My people consult a wooden idol,

and a diviner’s rod speaks to them.

A spirit of prostitution leads them astray;

they are unfaithful to their God.

13They sacrifice on the mountaintops

and burn offerings on the hills,

under oak, poplar and terebinth,

where the shade is pleasant.

Therefore your daughters turn to prostitution

and your daughters-in-law to adultery.

14‘I will not punish your daughters

when they turn to prostitution,

nor your daughters-in-law

when they commit adultery,

because the men themselves consort with harlots

and sacrifice with shrine-prostitutes –

a people without understanding will come to ruin!

15‘Though you, Israel, commit adultery,

do not let Judah become guilty.

‘Do not go to Gilgal;

do not go up to Beth Aven.4:15 Beth Aven means house of wickedness (a derogatory name for Bethel, which means house of God).

And do not swear, “As surely as the Lord lives!”

16The Israelites are stubborn,

like a stubborn heifer.

How then can the Lord pasture them

like lambs in a meadow?

17Ephraim is joined to idols;

leave him alone!

18Even when their drinks are gone,

they continue their prostitution;

their rulers dearly love shameful ways.

19A whirlwind will sweep them away,

and their sacrifices will bring them shame.