ሆሴዕ 13 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

ሆሴዕ 13:1-16

የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ

1ኤፍሬም ሲናገር ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤

በእስራኤልም የተከበረ ነበር፤

ነገር ግን በኣልን ስላመለከ በደለ፤ ሞተም።

2አሁንም ኀጢአትን መሥራት አበዙ፤

ብራቸውን አቅልጠው ለራሳቸው ጣዖት ሠሩ፣

በጥበብ የተሠሩ ምስሎችን አበጁ፤

ሁሉም የባለ እጅ ሥራ ናቸው።

ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ተብሏል፤

“ሰውን መሥዋዕት አድርገው ያቀርባሉ፤

የጥጃ ጣዖቶችንም ይስማሉ”13፥2 ወይም መሥዋዕት የሚያቀርቡ ሰዎች… ይስማሉ

3ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣

ፈጥኖ እንደሚጠፋ የጧት ጤዛ፣

ከዐውድማ እንደሚጠረግ እብቅ፣

በመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።

4“እኔ ግን ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣13፥4 ወይም በግብፅ ከነበራችሁበት ጊዜ አንሥቶ

አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤

ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፤

ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።

5በምድረ በዳ፣

በሐሩር ምድርም ተንከባከብሁህ።

6ካበላኋቸው በኋላ ጠገቡ፤

በጠገቡ ጊዜ ታበዩ፤

ከዚያም ረሱኝ።

7ስለዚህ እንደ አንበሳ እመጣባቸዋለሁ፤

እንደ ነብርም በመንገድ አደባባቸዋለሁ።

8ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ፣

እመታቸዋለሁ፤ እዘነጣጥላቸዋለሁ።

እንደ አንበሳም ሰልቅጬ እውጣቸዋለሁ፤

የዱር አራዊትም ይገነጣጥላቸዋል።

9“እስራኤል ሆይ፤ በእኔ ላይ ስለ ተነሣህ፣

ረዳትህንም ስለ ተቃወምህ ትጠፋለህ።

10‘ንጉሥንና አለቆችን ስጠኝ፤’

ብለህ እንደ ጠየቅኸው፣

ያድንህ ዘንድ ንጉሥህ የት አለ?

በከተሞችህ ሁሉ የነበሩ ገዦችህስ የት አሉ?

11በቍጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤

በመዓቴም ሻርሁት።

12የኤፍሬም በደል ተከማችቷል፤

ኀጢአቱም በመዝገብ ተይዟል።

13በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤

እርሱ ግን ጥበብ የሌለው ልጅ ነው፤

የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ፣

ከእናቱ ማሕፀን መውጣት የማይፈልግ ሕፃን ነው።

14“ከመቃብር ኀይል እታደጋቸዋለሁ፤

ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤

ሞት ሆይ፤ መቅሠፍትህ የት አለ?

መቃብር ሆይ፤13፥14 በዕብራይስጥ ሲኦል ማለት ነው ማጥፋትህ የት አለ?

“ከእንግዲህ ወዲህ አልራራለትም፤

15በወንድሞቹ መካከል ቢበለጽግም እንኳ፣

የምሥራቅ ነፋስ ከምድረ በዳ እየነፈሰ፣

ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል፤

ምንጩ ይነጥፋል፤

የውሃ ጕድጓዱም ይደርቃል።

የከበረው ሀብቱ ሁሉ፣

ከግምጃ ቤቱ ይበዘበዛል።

16የሰማርያ ሰዎች በደላቸውን ይሸከማሉ፤

በአምላካቸው ላይ ዐምፀዋልና፤

በሰይፍ ይወድቃሉ፤

ሕፃኖቻቸውም በምድር ላይ ይፈጠፈጣሉ፤

የእርጉዝ ሴቶቻቸውም ሆድ ይቀደዳል።”

Japanese Contemporary Bible

ホセア書 13:1-16

13

イスラエルに対する神の怒り

1かつてはイスラエルが何か言うと、

国々は恐れのあまり震え上がったものです。

イスラエルが強力な君主だったからです。

ところが、イスラエルはバアルを拝んで、

滅びを決定的なものにしました。

2今や民はますます不従順になっています。

銀を溶かして鋳型に入れ、

人の手で巧みに偶像を作っています。

「これにいけにえをささげろ」と言い、

子牛の像に口づけしているのです。

3彼らは朝もやのように、すぐ乾いてしまう露のように、

風で吹き散らされるもみがらのように、

煙のように、消え去ります。

4「わたしだけが神であり、あなたの主だ。

そのことは、エジプトからあなたを連れ出した時から、

ずっと変わらない。

わたしのほかに神はいない。

わたしのほかに救い主はいない。

5あの乾いて一滴の水もない荒野で、

わたしはあなたの面倒を見た。

6だが、あなたは食べて満足すると、高慢になり、

わたしを忘れてしまった。

7だから、わたしはライオンのように、

道で待ち伏せるひょうのように襲いかかる。

8子を奪われた熊のようにあなたを引き裂き、

ライオンのように食い尽くす。

9ああ、イスラエルよ。

わたしが滅ぼしたなら、だれがあなたを救えよう。

10あなたの王はどこにいる。

なぜ、その王に助けてもらわないのか。

この地の指導者はどこにいるのか。

あなたは王や指導者を頼みにした。

それなら、彼らに救ってもらうがいい。

11わたしは怒って王を与え、憤って王を取り上げた。

12エフライムの罪は刈り取られ、

罰せられるために積み上げられている。

13イスラエルは、新生の機会が与えられているのに、

母親の胎から出ようとしない子どものようだ。

なんと頑固で、愚かなことか。

14わたしは身代金を払って

イスラエルを地獄から救い出そうか。

死から買い戻そうか。

死よ、その恐ろしさをイスラエルに存分に味わわせよ。

墓よ、その災いをはっきりと示せ。

わたしはもうあわれまない。

15イスラエルは、

兄弟たちの中で一番実り豊かな者と呼ばれた。

だが、東風、荒野からの主の風が吹きまくり、

イスラエルを干上がらせてしまう。

そのあふれる湧き水も泉も枯れて、

イスラエルは渇きで死ぬ。

16サマリヤは自分の神に反逆したので、

刑罰を受けなければならない。

住民は侵略軍に殺され、赤子は地面にたたきつけられ、

妊婦は剣で切り裂かれる。」