Genesis 3 – NIV & NASV

New International Version

Genesis 3:1-24

The Fall

1Now the serpent was more crafty than any of the wild animals the Lord God had made. He said to the woman, “Did God really say, ‘You must not eat from any tree in the garden’?”

2The woman said to the serpent, “We may eat fruit from the trees in the garden, 3but God did say, ‘You must not eat fruit from the tree that is in the middle of the garden, and you must not touch it, or you will die.’ ”

4“You will not certainly die,” the serpent said to the woman. 5“For God knows that when you eat from it your eyes will be opened, and you will be like God, knowing good and evil.”

6When the woman saw that the fruit of the tree was good for food and pleasing to the eye, and also desirable for gaining wisdom, she took some and ate it. She also gave some to her husband, who was with her, and he ate it. 7Then the eyes of both of them were opened, and they realized they were naked; so they sewed fig leaves together and made coverings for themselves.

8Then the man and his wife heard the sound of the Lord God as he was walking in the garden in the cool of the day, and they hid from the Lord God among the trees of the garden. 9But the Lord God called to the man, “Where are you?”

10He answered, “I heard you in the garden, and I was afraid because I was naked; so I hid.”

11And he said, “Who told you that you were naked? Have you eaten from the tree that I commanded you not to eat from?”

12The man said, “The woman you put here with me—she gave me some fruit from the tree, and I ate it.”

13Then the Lord God said to the woman, “What is this you have done?”

The woman said, “The serpent deceived me, and I ate.”

14So the Lord God said to the serpent, “Because you have done this,

“Cursed are you above all livestock

and all wild animals!

You will crawl on your belly

and you will eat dust

all the days of your life.

15And I will put enmity

between you and the woman,

and between your offspring3:15 Or seed and hers;

he will crush3:15 Or strike your head,

and you will strike his heel.”

16To the woman he said,

“I will make your pains in childbearing very severe;

with painful labor you will give birth to children.

Your desire will be for your husband,

and he will rule over you.”

17To Adam he said, “Because you listened to your wife and ate fruit from the tree about which I commanded you, ‘You must not eat from it,’

“Cursed is the ground because of you;

through painful toil you will eat food from it

all the days of your life.

18It will produce thorns and thistles for you,

and you will eat the plants of the field.

19By the sweat of your brow

you will eat your food

until you return to the ground,

since from it you were taken;

for dust you are

and to dust you will return.”

20Adam3:20 Or The man named his wife Eve,3:20 Eve probably means living. because she would become the mother of all the living.

21The Lord God made garments of skin for Adam and his wife and clothed them. 22And the Lord God said, “The man has now become like one of us, knowing good and evil. He must not be allowed to reach out his hand and take also from the tree of life and eat, and live forever.” 23So the Lord God banished him from the Garden of Eden to work the ground from which he had been taken. 24After he drove the man out, he placed on the east side3:24 Or placed in front of the Garden of Eden cherubim and a flaming sword flashing back and forth to guard the way to the tree of life.

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 3:1-24

የሰው ውድቀት

1እባብ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከፈጠራቸው የዱር አራዊት ሁሉ ተንኰለኛ ነበረ፤ ሴቲቱንም፣ “በርግጥ እግዚአብሔር (ኤሎሂም)፣ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ዛፎች ከማናቸውም እንዳትበሉ’ ብሏልን?” አላት።

2ሴቲቱም እባቡን እንዲህ አለችው፤ “በአትክልቱ ስፍራ ካሉት ዛፎች ፍሬ መብላት እንችላለን፤ 3ነገር ግን እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ‘በአትክልቱ ስፍራ መካከል ከሚገኘው ዛፍ ፍሬ እንዳትበሉ፤ እንዳትነኩትም፤ አለዚያ ትሞታላችሁ’ ብሏል።”

4እባቡም ሴቲቱን እንዲህ አላት፤ “መሞት እንኳ አትሞቱም፤ 5ከፍሬው በበላችሁ ጊዜ ዐይናችሁ እንደሚከፈትና መልካምና ክፉን በማወቅ፣ እንደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) እንደምትሆኑ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ስለሚያውቅ ነው።”

6ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዐይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ፣ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከእርሷም ጋር ለነበረው ለባሏ ሰጠችው፤ እርሱም በላ። 7የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ ዕራቍታቸውን መሆናቸውንም ተገነዘቡ። ስለዚህ የበለስ ቅጠል ሰፍተው አገለደሙ።

8ቀኑ መሸትሸት ሲል፣ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) በአትክልቱ ስፍራ ሲመላለስ አዳምና ሔዋን ድምፁን ሰምተው ከእግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ፊት በዛፎቹ መካከል ተሸሸጉ። 9እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ግን አዳምን ተጣርቶ፣ “የት ነህ?” አለው።

10አዳምም፣ “ድምፅህን በአትክልቱ ስፍራ ሰማሁ፤ ዕራቍቴን ስለሆንሁ ፈራሁ፤ ተሸሸግሁም” ብሎ መለሰ።

11እግዚአብሔርም(ያህዌ)፣ “ዕራቍትህን መሆንህን ማን ነገረህ? ‘ከእርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ዛፍ በላህን?” አለው።

12አዳምም፣ “ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት፣ እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለ።

13እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሴቲቱን፣ “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” አላት።

እርሷም፣ “እባብ አሳሳተኝና በላሁ” አለች።

14እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) እባብን እንዲህ አለው፤ “ይህን ስለ ሠራህ፣

“ከከብቶችና ከዱር እንስሳት ሁሉ

ተለይተህ የተረገምህ ሁን፤

በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ በደረትህ

እየተሳብህ ትሄዳለህ፤

ዐፈርም ትበላለህ።

15በአንተና በሴቲቱ፣

በዘርህና በዘሯ መካከል፣

ጠላትነትን አደርጋለሁ፤

እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤3፥15 ወይም ይመታል

አንተም ተረከዙን ትቀጠቅጣለህ።”

16ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤

“በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤

በሥቃይም ትወልጃለሽ፤

ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤

እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”

17አዳምንም እንዲህ አለው፤ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ፣ ‘ከእርሱ አትብላ’ ብዬ ያዘዝሁህን ዛፍ በልተሃልና፣

“ከአንተ የተነሣ ምድር የተረገመች ትሁን፤

በሕይወትህ ዘመን ሁሉ

ምግብህን ጥረህ ግረህ ከእርሷ ታገኛለህ።

18ምድርም እሾኽና አሜከላ

ታበቅልብሃለች፤

ከቡቃያዋም ትበላለህ።

19ከምድር ስለ ተገኘህ፣

ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስ

ድረስ

እንጀራህን በፊትህ ላብ ትበላለህ፤

ዐፈር ነህና

ወደ ዐፈር ትመለሳለህ።”

20አዳምም3፥20 ወይም ሰውየው የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና ሚስቱን ሔዋን3፥20 ሔዋን ማለት ሕያው ማለት ሳይሆን አይቀርም። ብሎ ጠራት። 21እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከቈዳ ልብስ አዘጋጅቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።

22ከዚያም እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም)፣ “ሰው መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማወቅ ረገድ አሁን ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል፤ አሁን ደግሞ እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ቀጥፎ እንዳይበላ፣ ለዘላለምም እንዳይኖር ይከልከል” አለ። 23ስለዚህ የተገኘበትን ምድር እንዲያርስ፣ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰውን ከዔድን የአትክልት ስፍራ አስወጣው፤ 24ሰውንም ካስወጣው በኋላ፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሠይፍ ከዔድን በስተ ምሥራቅ አኖረ።3፥24 ወይም ፊት ለፊት አስቀመጠ