Znakovi Dana Gospodnjega
1A glede dolaska našega Gospodina Isusa Krista i našega okupljanja oko njega, 2ne dajte se zavesti kakvim proroštvom, riječju ili pismom o tomu kako je on već tu. 3Ne dajte se prevariti.
Jer taj dan neće doći prije velike pobune protiv Boga i prije nego što se pojavi čovjek bezakonja—koji će završiti u paklu. 4On će se uzdignuti iznad svih bića koje ljudi štuju i nazivaju bogovima. Zasjest će u Božji hram i sebe proglasiti Bogom. 5Zar se ne sjećate da sam vam o tomu govorio dok sam još bio s vama? 6Znate što ga zadržava—on može doći tek kad za to bude vrijeme.
7To zlo već potajno djeluje dok se ne ukloni onaj tko ga sada zadržava. 8Tada će se otkriti Bezakonik, kojega će Gospodin Isus pogubiti dahom iz svojih usta i uništiti svojim slavnim dolaskom. 9Taj će Bezakonik doći da sotonskom silom čini različita lažna znamenja i čudesa. 10Pokvareno će zavarati sve one koji idu u propast jer su odbili vjerovati u istinu da se spase. 11Zato će im Bog poslati djelotvornu obmanu da povjeruju u laž 12i da budu osuđeni svi koji nisu povjerovali istini, nego su odabrali živjeti u zlu.
Poticaj na ustrajnost
13Draga braćo i sestre, ne možemo a da uvijek ne zahvaljujemo Bogu za vas. Gospodin vas ljubi. Zahvalni smo Bogu što vas je od početka odabrao za spasenje koje dolazi kroz posvećenje Duha i kroz vjeru u istinu. 14Na spasenje vas je pozvao kad smo vam propovijedali Radosnu vijest, da sada budete dionicima slave našega Gospodina Isusa Krista.
15Budite, braćo, zato postojani i držite se predaja kojima smo vas poučili osobno ili u pismu.
16Neka naš Gospodin Isus Krist i naš Bog Otac, koji nas je ljubio i koji nam je po svojoj milosti dao vječnu utjehu i dobru nadu, 17utješi vaša srca i učvrsti ih u svakome dobrom djelu i riječi.
የዐመፅ ሰው
1ወንድሞች ሆይ፤ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱም ስለ መሰብሰባችን ይህን እንለምናችኋለን፤ 2በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደ ተላከ መልእክት የጌታ ቀን ደርሷል ብላችሁ ፈጥናችሁ ከአእምሯችሁ አትናወጡ፤ አትደንግጡም። 3ማንም ሰው በምንም መንገድ አያታልላችሁ፤ አስቀድሞ ዐመፅ ሳይነሣ፣ ለጥፋት የተመደበውም የዐመፅ2፥3 አንዳንድ ቅጆች የኀጢአት ይላሉ። ሰው ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና። 4እርሱም አምላክ ከተባለና ከሚመለከው ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተቀምጦ፣ “እኔ አምላክ ነኝ” እያለ ዐዋጅ ያስነግራል።
5ከእናንተ ጋር በነበርሁበት ጊዜ፣ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችሁ እንደ ነበር ትዝ አይላችሁምን? 6በራሱ ጊዜ ይገለጥ ዘንድ አሁን ምን እንደሚከለክለው ታውቃላችሁ። 7የዐመፅ ምስጢር አሁንም እንኳ እየሠራ ነውና፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው የሚከለክለው ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ ብቻ ነው 8ከዚያም በኋላ ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚያስወግደውና በምጽአቱም ክብር ፈጽሞ የሚያጠፋው ዐመፀኛ ይገለጣል። 9የዐመፀኛው አመጣጥ በሰይጣን አሠራር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ይህም በሐሰተኛ ታምራት በምልክቶችና በድንቅ ነገሮች ሁሉ ይሆናል፤ 10እንዲሁም ይድኑ ዘንድ እውነትን ባለመውደድ የሚጠፉትን ሰዎች በሚያታልል በተለያየ የክፋት ሥራ ይመጣል። 11በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በሐሰት እንዲያምኑ የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል፤ 12ይህም የሚሆነው እውነትን ያላመኑት ነገር ግን በክፋት ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ እንዲፈረድባቸው ነው።
ጸንታችሁ ቁሙ
13በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ ግን ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ይገባናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር እናንተን ከመጀመሪያ አንሥቶ በመንፈስ ተቀድሳችሁና በእውነትም አምናችሁ እንድትድኑ መርጧችኋል2፥13 አንዳንድ ቅጆች እግዚአብሔር በኵራቱ እንድትሆኑ መርጧችኋል ይላሉ።። 14የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ተካፋዮች እንድትሆኑም በወንጌላችን አማካይነት ጠርቷችኋል። 15እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በአንደበታችንም ሆነ በመልእክታችን ያስተላለፍንላችሁን ትምህርት2፥15 ወይም ወግ አጥብቃችሁ ያዙ።
16ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞም እኛን የወደደንና በጸጋው የዘላለም መጽናናትና መልካም ተስፋን የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን፣ 17ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎ ሥራና በቃል ሁሉ ያበርቷችሁ።