撒迦利亚书 12 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

撒迦利亚书 12:1-14

耶路撒冷必蒙拯救

1以下是耶和华关于以色列的启示。

铺展穹苍、奠立大地的根基、塑造人灵魂的耶和华说: 2“看啊,我要使耶路撒冷成为令周围万民昏醉的酒杯。耶路撒冷被围困时,犹大也必受困。 3到那天,当地上的列国聚集起来攻击耶路撒冷的时候,我要使耶路撒冷成为一块沉重的石头。凡试图举起它的,必伤自己。 4到那天,我要使所有的战马惊恐,使马上的骑士癫狂。我必看顾犹大家,使列邦的马匹瞎眼。这是耶和华说的。 5那时,犹大的族长必心里说,‘耶路撒冷的居民从他们的上帝——万军之耶和华那里得到了力量。’

6“到那天,我必使犹大的族长像木柴中的火盆,像禾捆中的火把,吞噬左右四围的列邦,但耶路撒冷人必仍在原处——耶路撒冷安居。

7“耶和华必首先拯救犹大的帐篷,免得大卫家和耶路撒冷居民的荣耀超过犹大8到那天,耶和华必保护耶路撒冷的居民,使他们当中最软弱的像大卫一样刚强,使大卫家像上帝一样,像耶和华的天使一样带领他们。 9到那天,我必毁灭前来攻击耶路撒冷的列国。

10“我必将施恩和祷告的灵浇灌在大卫家和耶路撒冷的居民身上。他们必仰望我——他们所刺的那位,如丧独子一般为祂哀伤,如丧长子一般为祂痛哭。 11到那天,耶路撒冷必一片哀声,犹如米吉多平原的哈达临门的哀声。 12境内家家户户都必哀哭。大卫家的男子在一处,女子在一处;拿单家的男子在一处,女子在一处; 13利未家的男子在一处,女子在一处;示每家的男子在一处,女子在一处。 14其余各家也都哀哭,男女分开。

New Amharic Standard Version

ዘካርያስ 12:1-14

የኢየሩሳሌም ጠላቶች እንደሚደመሰሱ የተነገረ ንግር

1ስለ እስራኤል የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ሰማያትን የዘረጋ፣ ምድርን የመሠረተ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ 2“ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ሕዝቦች ሁሉ የሚያንገደግድ ጽዋ አደርጋታለሁ፤ ይሁዳም እንደ ኢየሩሳሌም ሁሉ ትከበባለች። 3የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሷ ላይ በሚሰበሰቡበት በዚያ ቀን፣ ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ የማይነቃነቅ ዐለት አደርጋታለሁ፤ ለማነቃነቅ የሚሞክሩ ሁሉ ራሳቸውን ይጐዳሉ። 4በዚያን ቀን እያንዳንዱን ፈረስ በድንጋጤ፣ የተቀመጡባቸውንም ሰዎች እብደት እመታለሁ” ይላል እግዚአብሔር። “የይሁዳን ቤት በዐይኔ እጠብቃለሁ፤ ነገር ግን የአሕዛብን ፈረሶች ሁሉ አሳውራለሁ። 5የይሁዳ መሪዎች በልባቸው፣ ‘የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ብርቱ ናቸው፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ጸባኦት ነውና’ ይላሉ።

6“በዚያ ቀን የይሁዳን መሪዎች በዕንጨት ክምር ውስጥ እንዳለ የእሳት ምድጃ፣ በነዶም መካከል እንዳለ የፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፤ በግራና በቀኝ ዙሪያውን ያሉትን ሕዝቦች ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌም ግን ከስፍራዋ ንቅንቅ አትልም።

7“የዳዊት ቤትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከይሁዳ ክብር እንዳይበልጥ እግዚአብሔር በመጀመሪያ የይሁዳን መኖሪያዎች ያድናል። 8ከመካከላቸው እጅግ ደካማ የሆነው እንደ ዳዊት፣ የዳዊት ቤትም ፊት ፊታቸው እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር መልአክ፣ እንደ አምላክ ይሆንላቸው ዘንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እግዚአብሔር ይከልላቸዋል። 9በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን በወጓት አሕዛብ ሁሉ ላይ እወጣለሁ።

ስለ ወጉት የተደረገ ሐዘን

10“በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የልመና መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ ወጉኝ ወደ12፥10 ወይም ለእኔ ሊሆን ይችላል። እኔም ይመለከታሉ፤ እነርሱም ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ያለቅሱለታል፤ ለበኵር ልጅ ምርር ተብሎ እንደሚለቀስም አምርረው ያለቅሱለታል።” 11በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ ለሐዳድሪሞን እንደ ተለቀሰ ሁሉ በኢየሩሳሌም የሚለቀሰውም እንደዚሁ ታላቅ ልቅሶ ይሆናል። 12ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ የየነገዱ ወንዶች ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ ሚስቶቻቸውም ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ በዚህም ዐይነት የዳዊት ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የናታን ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ 13የሌዊ ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የሰሜኢ ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ 14የቀሩትም ነገዶች ወንዶች ሁሉ ከነሚስቶቻቸው ያለቅሳሉ።