历代志下 8 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志下 8:1-18

所罗门的功绩

1所罗门用二十年的时间兴建了耶和华的殿和他自己的王宫。 2他重修希兰送给他的城邑,让以色列人居住。

3所罗门去攻打哈马琐巴,并攻取了此城。 4他兴建旷野里的达莫以及哈马境内所有的储货城, 5把上伯·和仑与下伯·和仑建成有墙、有门、有闩的坚城, 6还建造巴拉、所有的储货城、屯车城、养马城和他想在耶路撒冷黎巴嫩及其统治的全境兴建的城邑。 7当时国中有人、亚摩利人、比利洗人、希未人和耶布斯人的后裔, 8以色列人没有灭绝他们。所罗门让他们服劳役,至今如此。 9所罗门王没有让以色列人服劳役,而是让他们做战士、将领、战车长和骑兵长。 10他还任命二百五十名监工负责监管工人。

11所罗门带法老的女儿离开大卫城,来到为她建造的宫中,因为所罗门说:“我的妻子不可住在以色列大卫的宫里,因为约柜所到之处都是圣洁的。”

12所罗门在门廊前他所筑的耶和华的坛上向耶和华献燔祭, 13并照摩西的规定,在安息日、朔日和每年特定的三个节期,即除酵节、七七节和住棚节献上当献的祭。

14所罗门照着他父亲大卫的吩咐,指派祭司分班供职,让利未人负责颂赞、辅助祭司尽每天的职责,还指派殿门守卫分班守门。这些都是上帝的仆人大卫规定的。 15他们没有违背大卫王就库房等工作对祭司和利未人的吩咐。

16从耶和华的殿奠基直到完工,所罗门所有的计划都已顺利完成。这样,耶和华的殿落成了。

17之后,所罗门前往以东地区靠海的以旬·迦别以禄18希兰派懂得航海的仆人乘船只与所罗门的仆人一同到俄斐,从那里为所罗门王运回十五吨黄金。

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 8:1-18

ሰሎሞን ያከናወናቸው ሌሎች ሥራዎች

8፥1-18 ተጓ ምብ – 1ነገ 9፥10-28

1ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የራሱን ቤተ መንግሥት የሠራባቸው ሃያ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ፣ 2ኪራም የሰጠውን ከተሞች አድሶ እስራኤላውያን እንዲሰፍሩባቸው አደረገ። 3ከዚያም ሰሎሞን ወደ ሐማት ሱባ ዘመተ፤ ያዛትም። 4በምድረ በዳውም ውስጥ ተድሞርንና ቀድሞ በሐማት ሠርቷቸው የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ ሠራ። 5እንዲሁም የላይኛውን ቤት ሖሮንና የታችኛውን ቤትሖሮን የተመሸጉ ከተሞች አድርጎ ከቅጥሮቻቸው፣ ከበሮቻቸውና ከመዝጊያዎቻቸው ጋር ሠራ። 6ደግሞም ባዕላትንና የዕቃ ቤት ከተሞቹን ሁሉ፣ ሠረገሎችና8፥6 ወይም ሠረገለኞች ተብሎ መተርጐም ይችላል። ፈረሶች የሚኖሩባቸውን ከተሞች ሁሉ፣ በአጠቃላይ በኢየሩሳሌም፣ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ ለመሥራት የፈለጋቸውን ነገሮች ሁሉ ሠራ።

7እስራኤላውያን ያልሆኑ ግን ከኬጢያውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፌርዜያውያን፣ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን የቀሩት ሕዝቦች ሁሉ፣ 8እስራኤላውያን ያላጠፏቸውን፣ በምድሪቱ የቀሩ ዘሮቻቸውን የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው፤ እስከ ዛሬም ይሠራሉ።8፥8 ወይም ከሌቦ ሐማት ተብሎ መተርጐም ይችላል። 9ይሁን እንጂ ሰሎሞን ማንም እስራኤላዊ ባሪያ ሆኖ በግዳጅ ሥራውን እንዲሠራ አላደረገም፤ እነርሱ ተዋጊዎች፣ የሻምበል አዛዦች፣ የሠረገሎችና የሠረገላ ነጂዎች አዛዦች ነበሩና። 10ከእነዚህም ሁለት መቶ አምሳዎቹ የንጉሥ ሰሎሞን ሹማምት ሰዎቹን የሚቈጣጠሩ ነበሩ።

11ሰሎሞንም፣ “የእግዚአብሔር ታቦት የገባበት ቦታ ሁሉ ቅዱስ ስለሆነ፣ ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤተ መንግሥት መኖር አይገባትም” በማለት የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ እርሱ ወደ ሠራላት ቤተ መንግሥት አመጣት።

12ሰሎሞንም በቤተ መቅደሱ መመላለሻ ፊት ለፊት ባሠራው የእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ። 13ሙሴ ስለ መሥዋዕት አቀራረብ ባዘዘው መሠረት በእያንዳንዱ የበዓል ቀን ይኸውም በየሰንበቱ፣ በየወሩ መባቻና በሦስቱ የዓመት በዓላት ማለትም በቂጣ በዓል፣ በመከር በዓልና በዳስ በዓል ጊዜ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ። 14የአባቱን የዳዊትን ሥርዐት በመከተልም፣ ካህናቱን በየአገልግሎት ክፍላቸው ሌዋውያኑንም ምስጋናውን እንዲመሩና በየዕለቱ ሥራቸው ካህናቱን እንዲረዱ መደባቸው። ደግሞም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት፣ የቤተ መቅደሱን በር ጠባቂዎች በልዩ ልዩ በሮች ጥበቃ ላይ በየክፍላቸው መደባቸው። 15እነርሱም ንጉሡ ግምጃ ቤቱን ጨምሮ ስለ ማናቸውም ነገር ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሰጠውን ትእዛዝ አልተላለፉም ነበር።

16የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት ከተጣለበት ዕለት አንሥቶ እስከ ፍጻሜው ድረስ ያለው የሰሎሞን ሥራ ሁሉ ተከናወነለት፤ በዚሁ ሁኔታም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ከፍጻሜ ደረሰ።

17ከዚያም ሰሎሞን የኤዶም የባሕር ጠረፍ ወደ ሆኑት ወደ ዔጽዮንጋብርና ወደ ኤሎት ሄደ። 18ኪራምም ባሕሩን በሚያውቁት በራሱ መኰንኖች የሚታዘዙ መርከቦችን ላከለት፤ እነዚህም ከሰሎሞን ሰዎች ጋር በመሆን ወደ ኦፊር ተጓዙ፤ ከዚያም አራት መቶ አምሳ መክሊት8፥18 ዐሥራ ስድስት ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ወርቅ አምጥተው ለንጉሥ ሰሎሞን ሰጡት።