利未记 21 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

利未记 21:1-24

祭司保持圣洁的条例

1耶和华对摩西说:“你把以下条例告诉祭司——亚伦的子孙。

“祭司不可因接触死去的族人而使自己不洁净, 2但骨肉至亲,如父母、儿女、兄弟、 3以及未出嫁仍是处女的姊妹例外。 4祭司不可因姻亲的关系而玷污自己。21:4 或译“作为民中的首领,祭司不可玷污自己。” 5祭司不可剃光头、修剪胡须或割伤身体。 6他们要做上帝的圣洁之民,不可亵渎我的名。因为他们负责献我的火祭,即我的食物,所以要保持圣洁。 7他们不可娶妓女或被休的女人为妻,因为祭司要为了我而保持圣洁。 8要视祭司为圣洁的,因为他们负责献你们上帝的食物。要视他们为圣洁的,因为使你们圣洁的我——耶和华是圣洁的。 9如果有祭司的女儿做妓女,辱没自己,她就是辱没自己的父亲,必须烧死她。

10“大祭司在众祭司中职分最高,头上浇过膏油,已经承受圣职、穿上圣衣,他不可披头散发、撕裂衣服。 11他不可接近死者,即使是父母也不可,以免玷污自己。 12他不可因丧事走出他上帝的圣所,以免亵渎圣所,因为我的膏油已经使他圣洁。我是耶和华。 13他必须娶处女为妻, 14不可娶寡妇、被休的女人或妓女,只可娶本族中的处女为妻, 15以免在民中玷污自己的子孙,因为我是使他们圣洁的耶和华。”

16耶和华对摩西说: 17“你把以下条例告诉亚伦

“你的子孙中,任何有残疾的人都不可前来献他上帝的食物,这是世世代代都要遵守的律例。 18瞎眼的、跛脚的、五官不正的、畸形的、 19四肢不全的、 20驼背的、矮小的、患眼疾的、长疥癣的或睪丸受损的,都不可近前来献祭。 21亚伦祭司子孙中有残疾的都不可向耶和华献火祭。他们既然有残疾,就不可近前来献我的食物。 22他们可以吃我的食物,圣的和至圣的都可以吃。 23但他们不可走近幔子或祭坛,因为他们有残疾。这样做是为了避免他们亵渎我的圣所。我是使圣所圣洁的耶和华。”

24摩西把这些条例告诉了亚伦父子们和所有的以色列人。

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 21:1-24

ለካህናት የተሰጠ መመሪያ

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤ 2ነገር ግን የቅርብ ዘመዶቹ ስለ ሆኑት እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣ ወይም ወንድሙ፣ 3እንዲሁም ባለማግባቷ ከእርሱ ጋር ስለምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል። 4ከእርሱ ጋር በጋብቻ ለሚዛመዱት21፥4 ወይም እንደ መሪነቱ በሕዝቡ መካከል ራሱን አያርክስ። ግን ራሱን አያርክስ።

5“ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤ 6ለአምላካቸው (ኤሎሂም) የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም (ኤሎሂም) ስም አያርክሱ። ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን (ኤሎሂም) ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ።

7“ ‘ካህናት በዝሙት የረከሱትንም ሆነ ከባሎቻቸው የተፋቱትን ሴቶች አያግቡ፤ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም) የተቀደሱ ናቸውና። 8የአምላክህን (ኤሎሂም) ምግብ የሚያቀርብ ነውና ቀድሰው፤ እኔ የምቀድሳችሁ21፥8 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያችሁ እኔ እግዚአብሔር እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ቅዱስ ነኝና ቅዱስ ይሁንላችሁ።

9“ ‘የካህን ሴት ልጅ ዝሙት ዐዳሪ ሆና ራሷን ብታረክስ፣ አባቷን ታዋርዳለች፤ በእሳት ትቃጠል።

10“ ‘ከወንድሞቹ መካከል ተለይቶ በራሱ ላይ ዘይት የፈሰሰበትና የክህነት ልብስ እንዲለብስ የተቀባው ካህን የራስ ጠጕሩን አይንጭ፤21፥10 ወይም ጠጕሩን አይላጭ። ወይም ልብሱን አይቅደድ። 11አስከሬን ወዳለበት ስፍራ አይግባ፤ ስለ አባቱም ሆነ ስለ እናቱ ራሱን አያርክስ፤ 12የተቀደሰበት የአምላኩ (ኤሎሂም) የቅባት ዘይት በላዩ ስለሆነ የአምላኩን (ኤሎሂም) መቅደስ ትቶ በመሄድ መቅደሱን አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

13“ ‘ካህኑ የሚያገባት ሴት ድንግል ትሁን። 14ባል የሞተባትን፣ የተፋታችውን ወይም በዝሙት ዐዳሪነት የረከሰችውን ሴት አያግባ፤ ነገር ግን ከወገኖቹ መካከል ድንግሊቱን ያግባ። 15በወገኖቹ መካከል ዘሩን አያርክስ። እርሱን የምቀድሰው21፥15 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለየው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

16እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 17“አሮንን እንዲህ በለው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይሠዋ ዘንድ አይቅረብ። 18ዕውር ወይም ዐንካሳ፣ የፊቱ ገጽታ ወይም የሰውነቱ ቅርጽ የተበላሸ ማንኛውም የአካል ጕድለት ያለበት ሰው አይቅረብ። 19እንዲሁም እግሩ ወይም እጁ ሽባ የሆነ፣ 20ጐባጣ ወይም ድንክ፣ ማንኛውም ዐይነት የዐይን እንከን ያለበት፣ የሚያዥ ቍስል ወይም እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ አይቅረብ። 21ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጕድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለሆነ፣ የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ለማቅረብ አይምጣ። 22እርሱም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይብላ። 23ነገር ግን እንከን ያለበት ስለሆነ መቅደሴን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይቅረብ ወይም ወደ መሠዊያው አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው21፥23 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያቸው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

24ሙሴም ይህን ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን ሁሉ ነገራቸው።