利未记 19 – CCB & NASV

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

利未记 19:1-37

有关圣洁生活的条例

1耶和华对摩西说: 2“你把以下条例告诉以色列全体会众。

“你们要圣洁,因为我——你们的上帝耶和华是圣洁的。 3你们每个人都必须孝敬父母,遵守我的安息日。我是你们的上帝耶和华。 4不要祭拜虚无的神明,也不要为自己铸造神像。我是你们的上帝耶和华。 5你们献平安祭给我时,要使你们所献的蒙悦纳。 6要在献祭当天或第二天吃完祭物。如果第三天还有剩余,都要烧掉。 7如果有人第三天还吃那些祭物,祭物就不洁净,我不会悦纳。 8那人要自担罪责,因为他亵渎了我的圣物。要将他从民中铲除。

9“你们收割的时候,不要割净田角地边的庄稼,也不要捡那些掉在田里的穗子。 10不要摘净葡萄园里的葡萄,也不要捡掉在地上的葡萄。要把这些留给穷人和寄居在你们中间的外族人。我是你们的上帝耶和华。 11不可偷盗,不可撒谎,不可互相欺骗。 12不可以我的名义起假誓,从而亵渎你们上帝的名。我是耶和华。 13不可欺压邻居,也不可抢夺他的东西。要当天支付雇工的工钱,不可拖到第二天。 14不可咒骂聋子,也不可绊倒盲人,应当敬畏你们的上帝。我是耶和华。 15不可徇私枉法,不可偏袒穷人,不可谄媚权贵之人,要秉公审判。 16不可到处搬弄是非,不可危害邻居的生命安全。我是耶和华。 17对同胞不可心中怀恨。同胞有错,要当面指正,免得自己因他而担罪。 18不可报复,不可埋怨同胞,要爱邻如己。我是耶和华。

19“你们要遵守我的律例。不可让牲畜杂交;不可在同一块田播撒两种不同的种子;不可穿两种材料织成的衣服。

20“一个已经许配人的婢女尚未被赎或未获自由时,如果有人与她同寝,就要受到处罚,但不可处死他们,因为那婢女还未获自由。 21和她同寝的人要把一只公绵羊牵到会幕门口,作为赎过祭献给耶和华。 22祭司要用作赎过祭的公绵羊为那人赎罪,他的罪便得到赦免。

23“你们到了迦南,在那里栽种各样果树后,前三年不可吃树上的果子,要视它们是不洁净的19:23 不洁净的”希伯来文是“未受割礼的”。24第四年,树上的所有果子都是圣洁的,要献给耶和华作颂赞之祭。 25第五年,你们可以吃树上的果子。你们这样做,果树会为你们结出更多果子。我是你们的上帝耶和华。

26“不可吃带血的肉,不可占卜或行巫术。 27不可修剪鬓角或胡须。 28不可因哀悼死人而割伤身体或纹身。我是耶和华。 29不可辱没自己的女儿,使她沦为娼妓,免得你们居住的地方充满淫乱和邪恶。 30要遵守我的安息日,敬畏我的圣所。我是耶和华。 31不可求问灵媒或巫师,玷污自己。我是你们的上帝耶和华。

32“在年长者面前,要恭敬站立,要敬重年长者。要敬畏你们的上帝。我是耶和华。 33不可欺负住在你们境内的外族人, 34要视他们如同胞,爱他们如爱自己,因为你们也曾经寄居埃及。我是你们的上帝耶和华。 35在称重和度量时,不可骗人。 36要使用准确的秤、尺子和升斗。我是你们的上帝耶和华,曾带领你们离开埃及37你们要遵行我的一切律例和典章。我是耶和华。”

New Amharic Standard Version

ዘሌዋውያን 19:1-37

ልዩ ልዩ ሕግጋት

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ጉባኤ እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።

3“ ‘ከእናንተ እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፤ ሰንበታቴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

4“ ‘ወደ ጣዖታት ዘወር አትበሉ፤ ወይም ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልክት አትሥሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

5“ ‘የኅብረት መሥዋዕት19፥5 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት ይባላል ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በምታቀርቡበት ጊዜ፣ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት እንዲያገኝላችሁ አድርጋችሁ አቅርቡ። 6መሥዋዕቱም ባቀረባችሁት ዕለት ወይም በማግስቱ ይበላ፤ እስከ ሦስተኛው ቀን የተረፈ ማንኛውም ነገር ይቃጠል። 7በሦስተኛውም ቀን ቢበላ ርኩስ ነው፤ ተቀባይነትም የለውም። 8ከመሥዋዕቱ የሚበላ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተቀደሰውን ነገር አርክሷልና ይጠየቅበታል፤ ያም ሰው ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ።

9“ ‘የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ፣ በዕርሻችሁ ዳርና ዳር ያለውን አትጨዱ፤ ቃርሚያውንም አትልቀሙ። 10የወይንህን ዕርሻ አትቃርም፤ የወደቀውንም አትልቀም፤ ለድኾችና ለመጻተኞች ተውላቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

11“ ‘አትስረቁ፤

“ ‘አትዋሹ፤

“ ‘ከእናንተ አንዱ ሌላውን አያታልል።

12“ ‘በስሜ በሐሰት አትማሉ፤ በዚህም የአምላካችሁን (ኤሎሂም) ስም አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

13“ ‘ባልንጀራህን አታጭበርብር፤ አትቀማውም፤

“ ‘የሙያተኛውን ደመወዝ ሳትከፍል አታሳድር።

14“ ‘ደንቈሮውን አትርገም፤ በዐይነ ስውሩም ፊት ዕንቅፋት አታኑር፤ ነገር ግን አምላክህን (ኤሎሂም) ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

15“ ‘ፍርድ አታዛቡ፤ ለድኻው አታድላለት፤ ለትልቁም ሰው ልዩ አክብሮት አትስጥ፤ ለብርቱው አታዳላ፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በትክክል ፍረድ።

16“ ‘በሕዝብህ መካከል ሐሜት አትንዛ፤

“ ‘የባልንጀራህን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም ነገር አታድርግ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

17“ ‘ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ የበደሉ ተካፋይ እንዳትሆን ባልንጀራህን በግልጽ ገሥጸው።

18“ ‘ወገንህን አትበቀል፤ ወይም ምቀኛ አትሁንበት፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

19“ ‘ሥርዐቴን ጠብቁ፤

“ ‘የተለያዩ እንስሳትን አታዳቅል፤

“ ‘በዕርሻህ ላይ ሁለት ዐይነት ዘር አትዝራ፤

“ ‘ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።

20“ ‘አንድ ሰው ለሌላ ከታጨች ሴት ባሪያ ጋር ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ ሴቲቱም ያልተዋጀች ወይም ነጻ ያልወጣች ብትሆን ይቀጣል፤ ነገር ግን ሴቲቱ ነጻ ስላልወጣች አይገደሉም። 21ሰውየውም ለበደል መሥዋዕት የሚሆን አንድ አውራ በግ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያምጣ። 22ካህኑም በበደል መሥዋዕቱ አውራ በግ፣ ሰውየው ስለ ሠራው ኀጢአት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።

23“ ‘ወደ ምድሪቱ ገብታችሁ ማንኛውንም ዐይነት ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ በምትተክሉበት ጊዜ፣ ፍሬው ለመብላት የተከለከለ መሆኑን ዕወቁ፤ ለሦስት ዓመትም የተከለከለ19፥23 ዕብራይስጡ ያልተገረዘ ይላል በመሆኑ አይበላ። 24በአራተኛውም ዓመት ፍሬው ሁሉ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተቀደሰ የምስጋና መሥዋዕት ይሆናል። 25በአምስተኛው ዓመት ግን ፍሬውን ትበላላችሁ፤ በዚህም ሁኔታ ፍሬው ይበዛላችኋል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

26“ ‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ሥጋ አትብሉ፤

“ ‘ጥንቈላ ወይም አስማት አትሥሩ።

27“ ‘የራስ ጠጕራችሁን ዙሪያ አትከርከሙ፤ ጢማችሁንም አሳጥራችሁ አትቍረጡ።

28“ ‘ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትንጩ፤ በሰውነታችሁም ላይ ንቅሳት አታድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

29“ ‘ምድሪቱ ወደ ግልሙትና አዘንብላ በርኩሰት እንዳትሞላ፣ ሴት ልጅህ ጋለሞታ ትሆን ዘንድ አታዋርዳት።

30“ ‘ሰንበታቴን ጠብቁ፤ መቅደሴንም አክብሩ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

31“ ‘እንዳትረክሱባቸው ወደ ሙታን ጠሪዎች ዘወር አትበሉ፤ መናፍስት ጠሪዎችንም አትፈልጉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

32“ ‘ዕድሜው ለገፋ ተነሥለት፤ ሽማግሌውን አክብር፤ አምላክህንም (ኤሎሂም) ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

33“ ‘መጻተኛ በምድራችሁ ላይ አብሯችሁ በሚኖርበት ጊዜ አትበድሉት፤ 34አብሯችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደ ገዛ ወገናችሁ ይታይ፤ እንደ ራሳችሁም ውደዱት፤ እናንተም በግብፅ መጻተኞች ነበራችሁና፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

35“ ‘በመስፈሪያ ወይም በሚዛን አታጭበርብሩ። 36እውነተኛ መለኪያ፣ እውነተኛ መመዘኛ፣ እውነተኛ የኢፍ19፥36 ኢፍ የደረቅ ነገር መለኪያ ወይም መስፈሪያ ነው። መስፈሪያ፣ እውነተኛ የኢን19፥36 ኢን የፈሳሽ ነገር መለኪያ ነው መስፈሪያም ይኑራችሁ። ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

37“ ‘ሥርዐቴንና ሕጌን ሁሉ ጠብቁ፤ ተከተሏቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”