呼吁百姓悔改
1-2不知羞耻的国民啊,
趁命令尚未发出、
日子尚未如风中的糠疾飞而去、
耶和华的烈怒尚未临到你们、
祂向你们发怒的日子尚未来临,
要聚集,聚集起来!
3世上所有遵守耶和华典章的谦卑人啊,
要寻求耶和华,追求公义,为人谦卑。
也许在耶和华发怒的日子,
你们可以得到庇护。
审判以色列的邻国
4迦萨必被抛弃,
亚实基伦必沦为废墟,
亚实突的居民必在中午被赶走,
以革伦必被连根拔除。
5住在海边的基利提人啊,
你们有祸了!
非利士人的土地——迦南啊,
耶和华宣告要毁灭你,
使你杳无人烟。
6沿海地区必成为草场,
有牧人的居所和羊圈。
7那里必归给犹大家的余民,
他们必在那里放牧,
晚上睡在亚实基伦的房屋里,
因为他们的上帝耶和华必眷顾他们,
使他们回到故土。
8-9以色列的上帝——万军之耶和华说:
“我听见了摩押人的毁谤和亚扪人的辱骂。
他们毁谤我的子民,扬言侵占他们的土地。
我凭自己的永恒起誓,
摩押和亚扪必刺草丛生、盐坑遍地、永远荒废,
如所多玛和蛾摩拉一样。
我余下的子民必掳掠他们,
我幸存的百姓必承受他们的土地。”
10这是他们的报应,
因为他们狂妄自大,
毁谤万军之耶和华的子民。
11耶和华必令他们恐惧,
因为祂要消灭世上的神明。
天下万民必各在本地敬拜祂。
12古实人啊,
你们必死在耶和华的刀下。
13祂必伸手攻击北方,毁灭亚述,
使尼尼微一片荒凉,
如干旱的旷野。
14牲畜和野兽必躺卧在那里,
猫头鹰和刺猬栖身在房柱上,
窗口传来鸟鸣,
门庭都已破败,
露出香柏木梁。
15这就是那欢乐安逸、
自以为无与伦比的城,
现在竟然如此荒凉,
成为野兽栖息之地!
路过的人都摇手嘲笑它。
ይሁዳና ኢየሩሳሌም ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ተፈረደባቸው
ይሁዳ ለንስሓ ተጠራ
1እናንት ዕረፍት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፤
በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ተከማቹም፤
2የተወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣
ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣
የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣ፣
የእግዚአብሔር የመዓት ቀን
ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ።
3እናንት የምድር ትሑታን ሁሉ፣
ትእዛዙን የምትፈጽሙ፣ እግዚአብሔርን እሹ፤
ጽድቅንና ትሕትናን ፈልጉ፤
በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣
ትሰወሩ ይሆናል።
በፍልስጥኤም ላይ የተነገረ ጥፋት
4ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤
አስቀሎናም ፈራርሳ ትቀራለች፤
አዛጦን በቀትር ባዶ ትሆናለች፤
አቃሮንም ትነቀላለች።
5እናንት በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፣
የከሊታውያን ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁ!
የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፤
በአንቺ ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤
“ፍጹም አጠፋሻለሁ፤
ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም።”
6የቀርጤስ2፥6 የዕብራይስጡ ትርጕም በትክክል አይታወቅም። ሰዎች የሚኖሩበት በባሕሩ
ዳር ያለው ምድር፣
የእረኞች መኖሪያና የበጎች በረት ይሆናል፤
7ይህም ለይሁዳ ቤት ትሩፍ ይሰጣል፤
እነርሱም በዚያ መሰማሪያ ያገኛሉ።
በአስቀሎና ቤቶች ውስጥም
በምሽት ይተኛሉ፤
አምላካቸው እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤
ምርኳቸውንም ይመልስላቸዋል።
በሞዓብና በአሞን ላይ የተነገረ ጥፋት
8“የሞዓብን ስድብ፣
የአሞናውያንንም ፌዝ ሰምቻለሁ፤
ሕዝቤን ሰድበዋል፤
በምድራቸውም ላይ ዝተዋል።”
9ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“በሕያውነቴ እምላለሁ፤
ሞዓብ እንደ ሰዶም፣
አሞናውያን እንደ ገሞራ፣
ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው
ጕድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ።
ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤
ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን
ይወርሳሉ።”
10ከትዕቢታቸው የተነሣ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤
የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕዝብ
ሰድበው ዘብተውበታልና፣
11እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክት
ሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣
በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤
በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣
እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።
በኢትዮጵያ ላይ የተነገረ ጥፋት
12“ኢትዮጵያውያን ሆይ፤ እናንተም፣
በሰይፌ ትገደላላችሁ።”
በአሦር ላይ የተነገረ ጥፋት
13እጁን በሰሜን ላይ ይዘረጋል፤
አሦርንም ያጠፋል፤
ነነዌን ፍጹም ባድማ፣
እንደ ምድረ በዳም ደረቅ ያደርጋታል።
14የበግና የከብት መንጋዎች፣
የፍጥረት ዐይነት ሁሉ በውስጧ ይመሰጋሉ፤
ጕጕትና ጃርት፣
በግንቦቿ ላይ ያድራሉ።
ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤
ፍርስራሽ በየደጃፉ ይከመራል፤
ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይገለጣሉ።
15ተዘልላ የኖረች፣
ደስተኛዪቱ ከተማ ይህች ናት፤
እርሷም በልቧ፣
“እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ማንም የለም” ያለች፣
ታዲያ እንዴት የዱር አራዊት የሚመሰጉባት፣
ባድማ ሆና ቀረች?
በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ፣
ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል።