መዝሙር 98:1-9 NASV

መዝሙር 98:1-9

መዝሙር 98

የዓለም ሁሉ ዳኛ

መዝሙር።

ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤

እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጓልና፤

ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም

ማዳንን አድርገውለታል።

እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤

ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።

ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣

ታማኝነቱንም ዐሰበ፤

የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣

የአምላካችንን ማዳን አዩ።

ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤

ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤

ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤

በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤

በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣

በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።

ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣

ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።

ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፣

ተራሮችም በአንድነት ይዘምሩ፤

እነዚህ በእግዚአብሔር ፊት ይዘምሩ፤

እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤

በዓለም ላይ በጽድቅ፣

በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።

Read More of መዝሙር 98