መዝሙር 74:18-23 NASV

መዝሙር 74:18-23

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላት እንዴት እንደሚያሾፍ፣

ከንቱ ሕዝብም ስምህን እንዴት እንዳቃለለ ዐስብ።

የርግብህን ነፍስ አሳልፈህ ለዱር አራዊት አትስጥ፤

የችግረኞች ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለሙ አትርሳ።

ኪዳንህን ዐስብ፤

የዐመፅ መናኸሪያ በምድሪቱ ጨለማ ስፍራዎች ሞልተዋልና።

የተጨቈኑት ዐፍረው አይመለሱ፤

ድኾችና ችግረኞች ስምህን ያመስግኑ።

አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ ለዐላማህ ተሟገት፤

ከንቱ ሰው ቀኑን ሙሉ እንደሚያላግጥብህ ዐስብ።

የባላጋራዎችህን ድንፋታ፣

ዘወትር የሚነሣውን የጠላቶችህን ፉከራ አትርሳ።

Read More of መዝሙር 74