መዝሙር 53:1-6 NASV

መዝሙር 53:1-6

መዝሙር 53

አምላክ የለሾች

53፥1-6 ተጓ ምብ – መዝ 14፥1-7

ለመዘምራን አለቃ፤ በማኸላት፤ የዳዊት ትምህርት53 ርእሱ ምናልባት የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

ቂል በልቡ፣

“እግዚአብሔር የለም” ይላል።

ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤

በጎ ነገርን የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም።

በማስተዋል የሚመላለስ፣

እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት፣

እግዚአብሔር ከሰማይ

ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።

ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤

በአንድነትም ተበላሹ፤

አንድ እንኳ

በጎ የሚያደርግ የለም።

ሰው እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉት፣

እግዚአብሔርንም ጠርተው የማያውቁት፣

እነዚያ ክፉ አድራጊዎች ከቶ አይማሩምን?

የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣

በዚያ፣ በፍርሀት ተዋጡ፤

እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤

እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው።

ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በወጣ!

እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣

ያዕቆብ ሐሤት ያድርግ፤ እስራኤል ደስ ይበለው።

Read More of መዝሙር 53