መዝሙር 119:121-128 NASV

መዝሙር 119:121-128

ፍትሕና ጽድቅ ያለበትን ሠርቻለሁ፤

ለሚጨቍኑኝ አሳልፈህ አትስጠኝ።

ለባሪያህ በጎነት ዋስትና ሁን፤

እብሪተኞች እንዲጨቍኑኝ አትፍቀድላቸው።

ዐይኖቼ ማዳንህን፣

የጽድቅ ቃልህን በመጠባበቅ ደከሙ።

ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ መጠን አድርግ፤

ሥርዐትህንም አስተምረኝ።

እኔ ባሪያህ ነኝ፤

ምስክርነትህን ዐውቅ ዘንድ ማስተዋልን ስጠኝ።

እግዚአብሔር ሆይ፤

ሕግህ እየተጣሰ ነውና፣

ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው።

ስለዚህ ከወርቅ፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ፣

ትእዛዞችህን ወደድሁ።

መመሪያህ ሙሉ በሙሉ ልክ ነው አልሁ፤

ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

פ ፔ

Read More of መዝሙር 119