ዘፍጥረት 9:18-29, ዘፍጥረት 10:1-32, ዘፍጥረት 11:1-9 NASV

ዘፍጥረት 9:18-29

የኖኅ ልጆች

ከመርከቧ የወጡትም የኖኅ ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ነበሩ፤ ካም የከነዓን አባት ነው። ሦስቱ የኖኅ ልጆች እነዚህ ሲሆኑ፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚሁ ነው።

ኖኅ ገበሬ ነበረና ወይን ተከለ፤9፥20 ወይም የመጀመሪያ ነበር ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ ዕርቃኑን ተኛ። የከነዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ።

ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፣ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤ እንዲህም አለ፤

“ከነዓን የተረገመ ይሁን፤

ለወንድሞቹም፣ የባሪያ ባሪያ ይሁን።”

ደግሞም፤

“የሴም አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ይባረክ፤

ከነዓንም የሴም9፥26 ወይም የእርሱ ባሪያ ይሁን ባሪያ ይሁን።

እግዚአብሔር (ኤሎሂም) የያፌትን9፥27 ያፌት የሚለው ቃል መዘርጋት የሚል ትርጕም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው። ግዛት ያስፋ፤

ያፌት በሴም ድንኳኖች ይኑር፤

ከነዓንም የእርሱ9፥27 ወይም የእነርሱ ባሪያ ይሁን” አለ።

ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ፤ ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖሮ ሞተ።

Read More of ዘፍጥረት 9

ዘፍጥረት 10:1-32

የኖኅ ልጆች ትውልድ

የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ እነርሱም ራሳቸው ከጥፋት ውሃ በኋላ ወንዶች ልጆችን ወለዱ።

የያፌት ዝርያዎች

10፥2-5 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥5-7

የያፌት ልጆች፦10፥2 ልጆች ማለት ዘርዐ ትውልዶች ወይም ወራሾች ወይም ሕዝቦች ማለት ሊሆን ይችላል፤ በ3፡4፡6፡7፡20-23፡29 እና 31 እንዲሁ፤

ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ ናቸው።

የጋሜር ልጆች፦

አስከናዝ፣ ራፋት፣ ቴርጋማ ናቸው።

የያዋን ልጆች፦

ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮዲኢ10፥4 ጥቂት የማሶሬቲክ የጥንት ጽሑፎች፣ ከኦሪተ ሳምራውያን፣ ሰብዓ ሊቃናትና አብዛኞቹ የማሶሬቲክ የጥናት ጽሑፎች የሚሉት ዶዳኒም ነው። ናቸው። ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።

የካም ዝርያዎች

10፥6-20 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥8-16

የካም ልጆች፦

ኵሽ፣ ምጽራይም፣10፥6 13ትንም ጨምሮ ግብፅን ያመለክታል። ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።

የኵሽ ልጆች፦

ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰበቅታ ናቸው።

የራዕማ ልጆች፦

ሳባ፣ ድዳን ናቸው።

ኵሽ የናምሩድ አባት10፥8 13፡15፡24 እና 26ትን ጨምሮ አባት ማለት ቅድመ አያት ወይም ተተኪ ወይም መሥራች ማለት ሊሆን ይችላል። ነበረ፤ ናምሩድም በምድር ላይ ኀያል ሰው እየሆነ ሄደ። በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ብርቱ ዐዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ ዐዳኝ” ይባል ነበር። የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች፦ ባቢሎን፣ ኦሬክ፣ አርካድና ካልኔ ናቸው፤ እነዚህ በ10፥10 ወይም ኦሬክና አርካድ፣ ሁሉም ሰናዖር10፥10 ባቢሎን ነው ምድር ነበሩ። ከዚያም ምድር ወደ አሦር ወጥቶ ነነዌን፣ ረሆቦትን፣10፥11 ወይም ነነዌ ከነከተማዋ አደባባዮች ካለህን እንዲሁም በነነዌና በካለህ መካከል ሬስን ቈረቈረ፤ ታላቁንም ከተማ መሠረተ።

ምጽራይም፦

የሉዳማውያን፣ የዕሚማውያን፣ ላህቢያውያን፣ የነፍታሌማውያን፣ የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የኮስሉሂማውያን፣ የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።

ከነዓንም፦

የበኵር ልጁ10፥15 ወይም ከሲዶናውያን የመጀመሪያው የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣ የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርሳውያን አባት ነበረ፤ እንዲሁም የኤዊያውያን፣ የዑር ኬዋናውያን፣ የሲኒያውያን፣ የአራዴዎናውያን፣ የሰማሪናውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነበረ።

ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።

እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ናቸው።

የሴም ዝርያዎች

10፥21-31 ተጓ ምብ – ዘፍ 11፥10-271ዜና 1፥17-27

ለያፌት ታላቅ ወንድም10፥21 ወይም ሴም፣ የ…ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።

የሴም ልጆች፦

ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።

የአራም ልጆች፦

ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ10፥23 ሰብዓ ሊቃናትንና 1ዜና 1፥17 ይመ፤ በዕብራይስጡ ማሽ ይለዋል። ናቸው።

አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤10፥24 ከዕብራይስጡ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ሰብዓ ሊቃናት ግን የቃይናን አባት፣ ቃይናንም የ…አባት ነበረ ይላል።

ሳላም ዔቦርን ወለደ።

ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤

አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፍሌቅ10፥25 ፍሌቅ ማለት ክፍፍል ማለት ነው። ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።

ዮቅጣንም፦

የኤልሞሳድ፣ የሣሌፍ፣ የሐስረሞት፣ የያራሕ፣ የሀደራም፣ የአውዛል፣ የደቅላ አባት ነበረ፤ እንዲሁም የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣ የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባል አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።

መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል።

እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው።

የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።

Read More of ዘፍጥረት 10

ዘፍጥረት 11:1-9

የባቤል ግንብ

በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር። ሰዎቹም ምሥራቁን11፥2 ወይም ከምሥራቅ፣ በምሥራቅ ይዘው ሲጓዙ፣ በሰናዖር11፥2 ባቢሎንን ያመላክታል። አንድ ሜዳ አግኝተው በዚያ ሰፈሩ።

እነርሱም እርስ በርሳቸው፣ “ኑ፤ ጡብ እንሥራ፤ እስኪበቃውም በእሳት እንተኵሰው” ተባባሉ። በድንጋይ ፈንታ ጡብ፣ ለማያያዣም ቅጥራን ተጠቀሙ። ከዚያም “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆንና በምድር ላይ እንዳንበተን፣ ኑ፤ ከተማ፣ ሰማይ የሚደርስ ግንብም ለራሳችን እንሥራ” አሉ።

እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን ሰዎቹ ይሠሩ የነበሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “እንዲህ እንደ አንድ ሕዝብ አንድ ቋንቋ በመናገር ይህን ማድረግ ከጀመሩ፣ ከእንግዲህ ያቀዱትን ሁሉ ማከናወን አያዳግታቸውም። ኑ እንውረድ፤ እርስ በርሳቸውም እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።”

ስለዚህ እግዚአብሔር (ያህዌ) በምድር ሁሉ ላይ በታተናቸው፤ ከተማዋንም መሥራት አቆሙ። እግዚአብሔር (ያህዌ) በዚያ የመላውን ዓለም ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዪቱ ስም ባቤል11፥9 ባቢሎንን ያመላክታል። ባቤል የሚለው ቃል ድንግርታ የሚል ትርጕም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር አንድ ዐይነት ድምፅ አለው። ተባለ። ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሰዎቹን በምድር ሁሉ በተናቸው።

Read More of ዘፍጥረት 11