โยชูวา 16 – TNCV & NASV

Thai New Contemporary Bible

โยชูวา 16:1-10

ดินแดนของเผ่าเอฟราอิมและมนัสเสห์

1ดินแดนที่เป็นส่วนของเผ่าโยเซฟเริ่มจากจอร์แดนแห่งเยรีโค16:1 อาจจะเป็นชื่อโบราณของแม่น้ำจอร์แดนทางตะวันออกของห้วงน้ำแห่งเยรีโค ผ่านถิ่นกันดารเข้าสู่แถบเทือกเขาแห่งเบธเอล 2จากเบธเอล (คือลูส)16:2 ภาษาฮีบรูว่าเบธเอลไปถึงลูส ข้ามไปสู่เขตแดนของชาวอารคีในอาทาโรท 3ลงมาทางตะวันตกถึงเขตแดนของชาวยาเฟลที มายังเบธโฮโรนล่าง ไปเกเซอร์แล้วสุดที่ทะเล

4เผ่ามนัสเสห์และเอฟราอิมวงศ์วานของโยเซฟได้รับกรรมสิทธิ์ตามนั้น

5ดินแดนของเอฟราอิมแบ่งตามแต่ละตระกูล ได้แก่

พรมแดนด้านตะวันออกของพวกเขาเริ่มจากอาทาโรทอัดดาร์ ไปยังเบธโฮโรนตอนบน 6และต่อเนื่องไปถึงทะเล จากมิคเมธัททางเหนือ เลี้ยวไปทางตะวันออกสู่ทาอานาทชิโลห์ มายังยาโนอาห์ทางด้านตะวันออก 7จากยาโนอาห์มาทางใต้สู่อาทาโรทและนาอาราห์ จดเมืองเยรีโค สิ้นสุดลงที่แม่น้ำจอร์แดน 8จากทัปปูวาห์มาทางทิศตะวันตกสู่ลำห้วยคานาห์ มาสิ้นสุดที่ทะเล นี่คือกรรมสิทธิ์ของเผ่าเอฟราอิมตามแต่ละตระกูล 9และยังรวมเมืองต่างๆ กับหมู่บ้านในเขตของเผ่ามนัสเสห์ที่แยกไว้ให้ชาวเอฟราอิมอีกด้วย

10พวกเขาไม่ได้ขับไล่ชาวคานาอันซึ่งอาศัยอยู่ในเกเซอร์ออกไป ชาวคานาอันจึงยังคงอาศัยอยู่ในหมู่คนเอฟราอิม แต่ถูกเกณฑ์เป็นทาสแรงงานจนถึงทุกวันนี้

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 16:1-10

ለኤፍሬምና ለምናሴ ነገድ የተመደበው ድርሻ

1ለዮሴፍ ዝርያዎች የተመደበው ድርሻ፣ ከዮርዳኖስ ኢያሪኮ16፥1 ምናልባት፣ ዮርዳኖስ ዘኢያሪኮ የዮርዳኖስ ወንዝ የጥንት መጠሪያ ሊሆን ይችላል።፣ ማለት ከኢያሪኮ ምንጮች በስተ ምሥራቅ ይነሣና፣ ምድረ በዳውን በማቋረጥ በኰረብታማው አገር አድርጎ ወደ ቤቴል ይወጣል። 2ሎዛ ከምትባለው ከቤቴል ይነሣና በአጣሮት ወደሚገኘው ወደ አርካውያን ግዛት ይሻገራል፣ 3በዚያም በምዕራብ በኩል ቍልቍል ወደ የፍሌጣውያን ግዛት እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ምድር ይወርድና ወደ ጌዝር ዘልቆ ባሕሩ ላይ ይቆማል።

4ስለዚህ የዮሴፍ ዘሮች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ተቀበሉ።

5ለኤፍሬም ወገን በየጐሣ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፤

ድንበሩ በምሥራቅ በኩል ከአጣሮት አዳር ተነሥቶ እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣና፣ 6እስከ ባሕሩ ይዘልቃል። በስተ ሰሜን ደግሞ ከሚክምታት ተነሥቶ በምሥራቅ በኩል ወደ ተአናት ሴሎ ይታጠፍና ከዚያ በማለፍ እስከ ኢያኖክ ምሥራቅ ይዘልቃል። 7ከኢያኖክም በመነሣት ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ቍልቍል ይወርድና በኢያሪኮ በኩል አድርጎ ዮርዳኖስ ላይ ብቅ ይላል። 8ድንበሩ አሁንም ከታጱዋ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ቃና ወንዝ ይወርድና ከባሕሩ ላይ ይቆማል። እንግዲህ የኤፍሬም ነገድ በየጐሣ በየጐሣቸው የተካፈሉት ርስት ይህ ነበር።

9ይህም በምናሴ ነገድ ርስት ውስጥ ለኤፍሬም ዘሮች የተመደቡትን ከተሞች በሙሉና መንደሮቻቸውን የሚያጠቃልል ነው።

10ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋር አብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።