ฮีบรู 12 – TNCV & NASV

Thai New Contemporary Bible

ฮีบรู 12:1-29

1เพราะฉะนั้นในเมื่อเรามีพยานหมู่ใหญ่พรั่งพร้อมรอบด้านเช่นนี้แล้ว ก็ให้เราละทิ้งทุกอย่างที่ถ่วงอยู่และบาปที่เกาะแน่น ให้เราวิ่งด้วยความอดทนบากบั่นไปตามลู่ที่ทรงกำหนดไว้สำหรับเรา 2ให้เราเพ่งมองที่พระเยซูผู้ทรงลิขิตความเชื่อและทรงทำให้ความเชื่อของเราสมบูรณ์ พระองค์ทรงทนรับกางเขนและไม่ใส่พระทัยในความอัปยศของไม้กางเขนเพราะเห็นแก่ความชื่นชมยินดีที่อยู่เบื้องหน้า และพระองค์ได้ประทับที่เบื้องขวาพระที่นั่งของพระเจ้า 3ท่านทั้งหลายจงใคร่ครวญถึงพระองค์ผู้ทรงทนการต่อต้านเช่นนั้นจากคนบาป เพื่อว่าท่านจะได้ไม่อ่อนล้าและท้อแท้ใจ

พระเจ้าทรงตีสอนบุตรของพระองค์

4ในการขับเคี่ยวกับบาป ท่านยังไม่ได้ต่อสู้จนถึงกับหลั่งเลือด 5และท่านได้ลืมถ้อยคำให้กำลังใจซึ่งมีมาถึงท่านในฐานะบุตรว่า

“ลูกเอ๋ย อย่าละเลยการตีสอนขององค์พระผู้เป็นเจ้า

อย่าท้อใจเมื่อพระองค์ทรงตำหนิท่าน

6เพราะองค์พระผู้เป็นเจ้าทรงตีสอนผู้ที่พระองค์ทรงรัก

และทรงลงโทษทุกคนที่ทรงรับเป็นบุตร”12:5,6 สภษ. 3:11,12

7จงทนความทุกข์ยากโดยถือเสมือนว่าเป็นการตีสอน พระเจ้าทรงปฏิบัติต่อท่านในฐานะบุตร เพราะบุตรคนไหนบ้างที่บิดาไม่เคยตีสอน? 8หากท่านไม่ถูกตีสอน (และทุกคนได้รับการตีสอน) ท่านก็เป็นบุตรนอกกฎหมายและไม่ใช่บุตรแท้ 9ยิ่งไปกว่านั้นเราทั้งปวงล้วนมีบิดาซึ่งเป็นมนุษย์ผู้ตีสอนเราและเราเคารพนับถือท่านที่ทำเช่นนั้น ยิ่งกว่านั้นสักเพียงใดที่เราควรอยู่ในโอวาทของพระบิดาแห่งจิตวิญญาณของเราและมีชีวิตอยู่! 10บิดาของเราตีสอนเราชั่วระยะหนึ่งตามที่คิดเห็นว่าดีที่สุด แต่พระเจ้าทรงตีสอนเราเพื่อประโยชน์ของเรา เพื่อเราจะได้มีส่วนในความบริสุทธิ์ของพระองค์ 11ไม่มีการตีสอนใดดูน่าชื่นใจในเวลานั้น มีแต่จะเจ็บปวด แต่ภายหลังจะเกิดผลเป็นความชอบธรรมและสันติสุขแก่บรรดาผู้รับการฝึกฝนโดยการตีสอนนั้น

12เพราะฉะนั้นจงทำให้แขนที่อ่อนแรงและเข่าที่อ่อนล้าเข้มแข็งขึ้น 13“จงทำทางที่ราบเรียบสำหรับเท้าของท่าน”12:13 สภษ. 4:26 เพื่อคนง่อยจะไม่พิการแต่กลับเป็นปกติดี

เตือนไม่ให้ปฏิเสธพระเจ้า

14จงเพียรพยายามที่จะอยู่อย่างสงบสุขร่วมกับคนทั้งปวงและเป็นผู้บริสุทธิ์ เพราะถ้าปราศจากความบริสุทธิ์แล้วก็ไม่มีใครจะได้เห็นองค์พระผู้เป็นเจ้าเลย 15จงระวังอย่าให้ใครพลาดไปจากพระคุณของพระเจ้า และอย่าให้มีรากขมขื่นงอกขึ้นมาสร้างความเดือดร้อน และทำให้คนเป็นอันมากแปดเปื้อนมลทิน 16จงระวัง อย่าให้ใครผิดศีลธรรมทางเพศ หรือไม่อยู่ในทางพระเจ้าแบบเอซาวผู้ขายสิทธิบุตรหัวปีแลกกับอาหารมื้อเดียว 17ท่านทั้งหลายทราบอยู่ว่าในภายหลังเมื่อเอซาวต้องการรับพรนี้เป็นมรดกก็ถูกปฏิเสธ เขาไม่อาจแก้ไขอะไรได้แม้เขาจะแสวงหาพรนั้นด้วยน้ำตา

18ท่านทั้งหลายไม่ได้มายังภูเขาที่จับต้องได้และที่ลุกเป็นไฟ ไม่ได้มายังความมืด ความมืดมนและพายุ 19ไม่ได้มายังเสียงแตรกระหึ่มหรือพระสุรเสียงตรัสซึ่งบรรดาผู้ที่ได้ยินแล้ววอนขออย่าได้ตรัสคำใดๆ กับเขาอีก 20เพราะพวกเขาไม่อาจทนกับคำบัญชาที่ว่า “แม้แต่สัตว์ที่แตะต้องภูเขานั้นก็จะต้องถูกหินขว้างตาย”12:20 อพย.19:12,13 21สิ่งที่เห็นนั้นน่าหวาดกลัวยิ่งนักจนโมเสสกล่าวว่า “ข้าพเจ้ากลัวจนตัวสั่น”12:21 ฉธบ.9:19

22แต่ท่านทั้งหลายได้มาถึงภูเขาศิโยน คือถึงนครของพระเจ้าผู้ทรงพระชนม์อยู่ คือเยรูซาเล็มแห่งสวรรค์ ท่านได้มาถึงที่ซึ่งทูตสวรรค์มากมายได้ชุมนุมกันอย่างร่าเริงยินดี 23มาสู่คริสตจักรแห่งบุตรหัวปีผู้มีชื่อจารึกไว้ในสวรรค์ ท่านได้มาถึงพระเจ้าผู้ทรงพิพากษามวลมนุษย์ มายังวิญญาณจิตของคนชอบธรรมซึ่งทรงทำให้สมบูรณ์แล้ว 24มาสู่พระเยซูผู้ทรงเป็นคนกลางแห่งพันธสัญญาใหม่ และมาถึงโลหิตประพรมซึ่งกล่าวถึงสิ่งที่ดียิ่งกว่าโลหิตของอาแบล

25จงระวังอย่าปฏิเสธพระองค์ผู้ตรัสอยู่ ถ้าพวกเขายังหนีไม่พ้นเมื่อปฏิเสธพระองค์ผู้ตรัสเตือนในโลก เราย่อมจะหนีไม่พ้นยิ่งขึ้นเพียงใดหากเราหันหนีพระองค์ผู้ทรงเตือนเราจากสวรรค์? 26ครั้งนั้นพระสุรเสียงของพระองค์ทำให้โลกสะเทือนสะท้าน แต่บัดนี้พระองค์ทรงสัญญาไว้ว่า “เราจะไม่เพียงเขย่าโลกนี้อีกครั้งหนึ่ง แต่จะเขย่าฟ้าสวรรค์ด้วย”12:26 ฮกก. 2:6 27คำว่า “อีกครั้งหนึ่ง” บ่งบอกว่าสิ่งที่สั่นคลอนได้คือสิ่งที่ทรงสร้างขึ้นนั้นจะถูกขจัดทิ้ง เพื่อให้เหลืออยู่แต่สิ่งที่ไม่สั่นคลอน

28เพราะฉะนั้นในเมื่อเรากำลังได้รับอาณาจักรอันไม่อาจสั่นคลอนได้ ก็ให้เราขอบพระคุณและนมัสการพระเจ้าอย่างที่ทรงพอพระทัย ด้วยความยำเกรงและด้วยความครั่นคร้าม 29เพราะว่า “พระเจ้าทรงเป็นไฟอันเผาผลาญ”12:29 ฉธบ.4:24

New Amharic Standard Version

ዕብራውያን 12:1-29

እግዚአብሔር ልጆቹን ይቀጣል

1እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ ሸክም የሚሆንብንን ሁሉ፣ በቀላሉም ተብትቦ የሚይዘንን ኀጢአት አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ። 2የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል። 3እንግዲህ ዝላችሁ ተስፋ እንዳትቈርጡ፣ ከኀጢአተኞች የደረሰበትን እንዲህ ያለውን ተቃውሞ የታገሠውን እርሱን አስቡ።

4ከኀጢአት ጋር ስትታገሉ ገና ደማችሁን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም። 5ልጆች እንደ መሆናችሁ እንዲህ በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ቃልም ረስታችኋል፦

“ልጄ ሆይ፤ የጌታን ቅጣት አታቃልል፤

በሚገሥጽህም ጊዜ ተስፋ አትቍረጥ፤

6ምክንያቱም ጌታ የሚወድደውን ይገሥጻል፤

እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ይቀጣል።”

7እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ይዟችኋልና የተግሣጽን ምክር ታገሡ፤ ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? 8ልጆች ሁሉ በሚቀጡበት ቅጣት ተካፋይ ካልሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። 9ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም? 10አባቶቻችን መልካም መስሎ እንደ ታያቸው ለጥቂት ጊዜ ይቀጡን ነበር፤ እግዚአብሔር ግን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለእኛ ጥቅም ሲል ይቀጣናል። 11ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ ያስገኝላቸዋል።

12ስለዚህ የዛለውን ክንዳችሁንና የደከመውን ጕልበታችሁን አበርቱ። 13ዐንካሳው እንዲፈወስ እንጂ የባሰውኑ እንዳያነክስ “ለእግራችሁ ቀና መንገድ አብጁ።”

እግዚአብሔርን ስላለመታዘዝ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

14ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ለመቀደስም ፈልጉ፤ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ማየት አይችልም። 15ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት፣ ደግሞም መራራ ሥር በቅሎ ችግር እንዳያስከትልና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ። 16ለአንድ ጊዜ መብል ሲል ብኵርናውን እንደ ሸጠው እንደ ዔሳው፣ ማንም ሴሰኛ ወይም እግዚአብሔርን የማያከብር ሆኖ እንዳይገኝ ተጠንቀቁ። 17በኋላም ይህንኑ በረከት ሊወርስ በፈለገ ጊዜ እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ በረከቱን በእንባ ተግቶ ቢፈልግም መልሶ ሊያገኘው አልቻለም።

18ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፣ ወደ ጨለማው፣ ወደ ጭጋጉና ወደ ዐውሎ ነፋሱ አልደረሳችሁም፤ 19ወደ መለከት ድምፅ ወይም ቃልን ወደሚያሰማ ድምፅ አልመጣችሁም፤ የሰሙትም ሌላ ቃል ተጨምሮ እንዳይናገራቸው ለመኑ። 20ምክንያቱም “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ፣ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት” የሚለውን ትእዛዝ መሸከም አልቻሉም። 21በዚያ ይታይ የነበረውም ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነበርና፣ ሙሴ “በፍርሀት ተንቀጠቀጥሁ” አለ።

22እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ፣ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም፣ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ መጥታችኋል፤ በደስታ ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፣ 23ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈው ወደ በኵራት ማኅበር ቀርባችኋል፤ የሁሉ ዳኛ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር፣ ፍጹምነትን ወዳገኙት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፣ 24የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፣ እንዲሁም ከአቤል ደም የተሻለ ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋል።

25የሚናገረውን እርሱን እንቢ እንዳትሉት ተጠንቀቁ። እነዚያ ከምድር ሆኖ ሲያስጠነቅቃቸው የነበረውን እንቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፣ እኛ ከሰማይ የመጣው ሲያስጠነቅቀን ከእርሱ ብንርቅ እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? 26በዚያን ጊዜ ድምፁ ያናወጠው ምድርን ነበር፤ አሁን ግን፣ “ምድርን ብቻ ሳይሆን፣ ሰማያትንም አንድ ጊዜ ደግሜ አናውጣለሁ” ብሎ ቃል ገብቷል። 27አንድ ጊዜ “ደግሜ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይናወጡት ጸንተው ይኖሩ ዘንድ፣ የሚናወጡት ይኸውም፣ የተፈጠሩት የሚወገዱ መሆናቸውን ነው።

28ስለዚህ ከቶ የማይናወጥ መንግሥት ስለምንቀበል እግዚአብሔርን እናመስግን፤ ደግሞም ደስ በሚያሰኘው መንገድ በአክብሮትና በፍርሀት እናምልከው፤ 29አምላካችን የሚያጠፋ እሳት ነውና።