วิวรณ์ 22 TNCV - ራእይ 22 NASV

วิวรณ์
Elegir capítulo 22

Thai New Contemporary Bible

วิวรณ์ 22:1-21

แม่น้ำแห่งชีวิต

1แล้วทูตนั้นสำแดงให้ข้าพเจ้าเห็นแม่น้ำที่มีน้ำแห่งชีวิตใสดั่งแก้วไหลจากพระที่นั่งของพระเจ้าและพระเมษโปดก 2ลงมากลางถนนใหญ่ของนครนั้น สองฟากแม่น้ำมีต้นไม้แห่งชีวิตซึ่งออกผลสิบสองครั้ง คือออกผลทุกๆ เดือน และใบของต้นไม้นั้นใช้รักษาบรรดาประชาชาติให้หาย 3ไม่มีการสาปแช่งใดๆ อีกต่อไป พระที่นั่งของพระเจ้าและพระเมษโปดกจะตั้งอยู่ในนครนั้นและบรรดาผู้รับใช้ของพระองค์จะปรนนิบัติพระองค์ 4เขาทั้งหลายจะเห็นพระพักตร์ของพระองค์และมีพระนามของพระองค์ประทับบนหน้าผากของพวกเขา 5จะไม่มีกลางคืนอีกแล้ว เขาทั้งหลายไม่ต้องการแสงตะเกียงหรือแสงแดดเพราะพระเจ้าผู้เป็นองค์พระผู้เป็นเจ้าจะประทานความสว่างแก่พวกเขาและพวกเขาจะครอบครองสืบๆ ไปเป็นนิตย์

6ทูตนั้นกล่าวกับข้าพเจ้าว่า “ข้อความเหล่านี้จริงแท้และเชื่อถือได้ องค์พระผู้เป็นเจ้าพระเจ้าแห่งดวงวิญญาณของเหล่าผู้เผยพระวจนะทรงส่งทูตสวรรค์ของพระองค์มาสำแดงแก่บรรดาผู้รับใช้ของพระองค์ให้เห็นสิ่งต่างๆ ที่จะต้องเกิดขึ้นในไม่ช้านี้”

พระเยซูกำลังจะเสด็จมา

7“ดูเถิด เราจะมาในไม่ช้า! ความสุขมีแก่ผู้ที่ยึดถือคำเผยพระวจนะในหนังสือนี้”

8ข้าพเจ้ายอห์นคือผู้ได้ยินได้เห็นสิ่งเหล่านี้ และเมื่อเห็นแล้วได้ยินแล้วข้าพเจ้าก็หมอบลงเพื่อนมัสการแทบเท้าทูตสวรรค์ผู้สำแดงแก่ข้าพเจ้า 9แต่ทูตนั้นบอกข้าพเจ้าว่า “อย่าทำเช่นนี้! เราเป็นเพื่อนผู้รับใช้ร่วมกับท่านและร่วมกับพี่น้องของท่าน คือเหล่าผู้เผยพระวจนะและคนทั้งปวงที่ถือรักษาถ้อยคำในหนังสือนี้ จงนมัสการพระเจ้าเถิด!”

10แล้วทูตนั้นบอกข้าพเจ้าว่า “อย่าปิดผนึกคำเผยพระวจนะในหนังสือนี้เพราะใกล้จะถึงเวลาแล้ว 11ผู้ที่ทำผิดก็ให้ทำผิดต่อไป ผู้ที่ชั่วช้าก็ให้ชั่วช้าต่อไป ผู้ที่ทำสิ่งที่ถูกต้องก็ให้ทำสิ่งที่ถูกต้องต่อไป และผู้ที่บริสุทธิ์ก็ให้รักษาตัวให้บริสุทธิ์ต่อไป”

12“ดูเถิด เราจะมาในไม่ช้านี้! บำเหน็จอยู่ที่เราและเราจะให้แก่ทุกคนตามการกระทำของเขา 13เราคืออัลฟาและโอเมกา เป็นเบื้องต้นและเบื้องปลาย เป็นปฐมและอวสาน

14“ความสุขมีแก่บรรดาผู้ชำระเสื้อผ้าของตนเพื่อเขาจะได้มีสิทธิ์ในต้นไม้แห่งชีวิตและผ่านประตูเข้าสู่นครนั้นได้ 15พวกที่อยู่ภายนอกคือสุนัข คนที่ใช้คาถาอาคม คนที่ผิดศีลธรรมทางเพศ ฆาตกร คนกราบไหว้รูปเคารพ และทุกคนที่รักการมุสาและประพฤติตามนั้น

16“เรา เยซู ส่งทูตสวรรค์ของเรามาเป็นพยานถึงสิ่งเหล่านี้แก่ท่านเพื่อคริสตจักรต่างๆ เราเป็นทายาท22:16 ภาษากรีกว่ารากและเป็นเชื้อสายของดาวิดและเราเป็นดาวแห่งรุ่งอรุณอันสุกใส”

17พระวิญญาณและเจ้าสาวตรัสว่า “มาเถิด!” และให้ผู้ที่ได้ยินกล่าวว่า “มาเถิด!” ผู้ใดกระหายให้ผู้นั้นเข้ามาและผู้ใดปรารถนาให้ผู้นั้นมารับน้ำแห่งชีวิตโดยไม่ต้องเสียอะไรเลย

18ข้าพเจ้าขอเตือนทุกคนที่ได้ยินคำเผยพระวจนะในหนังสือนี้ ผู้ใดเพิ่มเติมสิ่งใดลงไป พระเจ้าจะทรงเพิ่มภัยพิบัติที่บรรยายไว้ในหนังสือนี้แก่เขา 19และถ้าผู้ใดตัดทอนข้อความจากคำเผยพระวจนะนี้ พระเจ้าจะทรงตัดส่วนแบ่งของเขาในต้นไม้แห่งชีวิตและในนครบริสุทธิ์นั้นซึ่งบรรยายไว้ในหนังสือนี้

20พระองค์ผู้ทรงเป็นพยานถึงสิ่งเหล่านี้ตรัสว่า “แน่นอนเราจะมาในไม่ช้า” อาเมน องค์พระเยซูเจ้า โปรดเสด็จมาเถิด

21ขอให้พระคุณขององค์พระเยซูเจ้าดำรงอยู่กับประชากรของพระเจ้าเถิด อาเมน

New Amharic Standard Version

ራእይ 22:1-21

የሕይወት ወንዝ

1ከዚህ በኋላ መልአኩ ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ መስተዋት የጠራውን የሕይወት ውሃ ወንዝ አሳየኝ፤ 2ወንዙም በከተማዪቱ አውራ መንገድ መካከል ይፈስ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ በየወሩ እያፈራ ዐሥራ ሁለት ጊዜ ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ሕዝቦች የሚፈወሱባቸው ነበሩ። 3ከእንግዲህ ወዲህ ርግማን ከቶ አይኖርም፤ የእግዚአብሔርና የበጉ ዙፋን በከተማዪቱ ውስጥ ይሆናል፤ አገልጋዮቹም ያመልኩታል፤ 4ፊቱን ያያሉ፤ ስሙም በግምባራቸው ላይ ይሆናል። 5ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሓይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።

6መልአኩም፣ “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኞች ናቸው። የነቢያት መናፍስት ጌታ አምላክ በቅርብ የሚሆነውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ መልአኩን ልኮአል” አለኝ።

ኢየሱስ ይመጣል

7“እነሆ፤ ቶሎ እመጣለሁ፤ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”

8እነዚህን ነገሮች የሰማሁና ያየሁ እኔ ዮሐንስ ነኝ። እነዚህን ነገሮች በሰማሁና ባየሁ ጊዜ፣ እነዚህን ነገሮች ላሳየኝ መልአክ ልሰግድ በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ 9እርሱ ግን፣ “ተው፤ ይህን አታድርግ እኔ ከአንተና ከወንድሞችህ ከነቢያት እንዲሁም የዚህን መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁት ሁሉ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ” አለኝ።

10እንዲህም አለኝ፤ “ጊዜው ስለ ደረሰ፣ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው፤ 11ዐመፀኛው በዐመፁ ይቀጥል፤ ርኩሱም ይርከስ፤ ጻድቁም ይጽደቅ፤ ቅዱሱም ይቀደስ።”

12“እነሆ፤ ቶሎ እመጣለሁ፤ ዋጋዬ በእኔ ዘንድ አለ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍለዋለሁ። 13አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።

14“ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስና በበሮቿም በኩል ወደ ከተማዪቱ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው። 15ውሾች፣ አስማተኞች፣ ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸትን የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።

16“እኔ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች እንዲመሰክር መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያናት ልኬአለሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፣ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”

17መንፈስና ሙሽራዪቱ፣ “ና” ይላሉ፤ የሚሰማም፣ “ና” ይበል፤ የተጠማም ሁሉ ይምጣ፤ የሚፈልግም ሁሉ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ።

18የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል የሚሰማውን ሁሉ አስጠነቅቃለሁ፤ ማንም በዚህ ቃል ላይ አንዳች ቢጨምር፣ እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤ 19ማንም በዚህ የትንቢት መጽሐፍ ከተጻፈው ቃል አንዳች ቢያጐድል፣ እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ ዕድሉን ያጐድልበታል።

20እነዚህን ነገሮች የሚመሰክረው፣ “አዎ፣ ቶሎ እመጣለሁ” ይላል።

አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ና።

21የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከእግዚአብሔር ሕዝብ22፥21 አንዳንድ ቅጆች … ከቅዱሳን ጋር ይሁን ይላሉ። ጋር ይሁን፤ አሜን።22፥21 አንዳንድ ቅጆች አሜን የሚለውን አይጨምሩም።