Псалтирь 60 – NRT & NASV

New Russian Translation

Псалтирь 60:1-9

Псалом 60

1Дирижеру хора. На струнных инструментах. Псалом Давида.

2Боже, услышь мой крик,

внемли молитве моей!

3С края земли я к Тебе взываю;

сердце мое в унынии.

Возведи меня на скалу, которая мне недоступна,

4ведь Ты – прибежище мое,

крепкая башня от врага.

5Да живу я вечно в жилище Твоем

и под кровом крыльев Твоих покоюсь. Пауза

6Ты услышал, Боже, мои обеты;

Ты дал мне наследие тех, кто боится Твоего имени.

7Умножь дни жизни царя,

продли его годы из поколения в поколение.

8Да восседает он вечно перед Богом;

сохрани его Своей милостью и истиной.

9И буду я Твое имя воспевать всегда,

день за днем исполняя мои обеты.

New Amharic Standard Version

መዝሙር 60:1-12

መዝሙር 60

ከሽንፈት በኋላ የቀረበ ብሔራዊ ጸሎት

60፥5-12 ተጓ ምብ – መዝ 108፥6-13

ለመዘምራን አለቃ፤ “የኪዳን ጽጌረዳ” በሚለው ቅኝት የሚዘመር፤60 ርእሱ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። በሰሜናዊ ምዕራብ መስጴጦምያና60 ርእሱ የአራማውያን ወይም የሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ነው። በማእከላዊ ሶርያ የሚኖሩትን አራማውያን60 ርእሱ በመካከለኛው ሶርያ የሚገኙት አራማውያንን የሚያመለክት ነው። በወጋቸው ጊዜ፣ ኢዮአብም ተመልሶ በጨው ሸለቆ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ኤዶማውያንን በፈጀ ጊዜ፣ ለትምህርት፤ የዳዊት ቅኔ።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ጣልኸን፤ አንኰታኰትኸን፤

ተቈጣኸንም፤ አሁን ግን መልሰህ አብጀን።

2ምድሪቱን አናወጥሃት፤ ፍርክስክስ አደረግሃት፤

ትንገዳገዳለችና ስብራቷን ጠግን።

3ለሕዝብህ አበሳውን አሳየኸው፤

ናላ የሚያዞር የወይን ጠጅ እንድንጠጣም ሰጠኸን።

4ነገር ግን ከቀስት እንዲያመልጡ፣

ለሚፈሩህ ምልክት አቆምህላቸው። ሴላ

5ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣

በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስም ስጠን።

6እግዚአብሔር ከመቅደሱ እንዲህ ሲል ተናገረ፤

“ደስ እያለኝ የሴኬምን ምድር እሸነሽናለሁ፤

የሱኮትን ሸለቆ አከፋፍላለሁ።

7ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤

ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤

ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።

8ሞዓብ የመታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤

በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤

በፍልስጥኤም ላይ በድል እልል እላለሁ።”

9ወደ ተመሸገው ከተማ ማን ያመጣኛል?

ማንስ ወደ ኤዶምያስ ይመራኛል?

10አምላክ ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?

እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰራዊታችን ጋር እኮ አልወጣ አልህ!

11በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤

የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና።

12በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤

ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።