Jeremiah 48 – NIVUK & NASV

New International Version – UK

Jeremiah 48:1-47

A message about Moab

1Concerning Moab:

This is what the Lord Almighty, the God of Israel, says:

‘Woe to Nebo, for it will be ruined.

Kiriathaim will be disgraced and captured;

the stronghold48:1 Or captured; / Misgab will be disgraced and shattered.

2Moab will be praised no more;

in Heshbon48:2 The Hebrew for Heshbon sounds like the Hebrew for plot. people will plot her downfall:

“Come, let us put an end to that nation.”

You, the people of Madmen,48:2 The name of the Moabite town Madmen sounds like the Hebrew for be silenced. will also be silenced;

the sword will pursue you.

3Cries of anguish arise from Horonaim,

cries of great havoc and destruction.

4Moab will be broken;

her little ones will cry out.48:4 Hebrew; Septuagint / proclaim it to Zoar

5They go up the hill to Luhith,

weeping bitterly as they go;

on the road down to Horonaim

anguished cries over the destruction are heard.

6Flee! Run for your lives;

become like a bush48:6 Or like Aroer in the desert.

7Since you trust in your deeds and riches,

you too will be taken captive,

and Chemosh will go into exile,

together with his priests and officials.

8The destroyer will come against every town,

and not a town will escape.

The valley will be ruined

and the plateau destroyed,

because the Lord has spoken.

9Put salt on Moab,

for she will be laid waste48:9 Or Give wings to Moab, / for she will fly away;

her towns will become desolate,

with no-one to live in them.

10‘A curse on anyone who is lax in doing the Lord’s work!

A curse on anyone who keeps their sword from bloodshed!

11‘Moab has been at rest from youth,

like wine left on its dregs,

not poured from one jar to another –

she has not gone into exile.

So she tastes as she did,

and her aroma is unchanged.

12But days are coming,’ declares the Lord,

‘when I will send men who pour from pitchers,

and they will pour her out;

they will empty her pitchers

and smash her jars.

13Then Moab will be ashamed of Chemosh,

as Israel was ashamed

when they trusted in Bethel.

14‘How can you say, “We are warriors,

men valiant in battle”?

15Moab will be destroyed and her towns invaded;

her finest young men will go down in the slaughter,’

declares the King, whose name is the Lord Almighty.

16‘The fall of Moab is at hand;

her calamity will come quickly.

17Mourn for her, all who live around her,

all who know her fame;

say, “How broken is the mighty sceptre,

how broken the glorious staff!”

18‘Come down from your glory

and sit on the parched ground,

you inhabitants of Daughter Dibon,

for the one who destroys Moab

will come up against you

and ruin your fortified cities.

19Stand by the road and watch,

you who live in Aroer.

Ask the man fleeing and the woman escaping,

ask them, “What has happened?”

20Moab is disgraced, for she is shattered.

Wail and cry out!

Announce by the Arnon

that Moab is destroyed.

21Judgment has come to the plateau –

to Holon, Jahzah and Mephaath,

22to Dibon, Nebo and Beth Diblathaim,

23to Kiriathaim, Beth Gamul and Beth Meon,

24to Kerioth and Bozrah –

to all the towns of Moab, far and near.

25Moab’s horn48:25 Horn here symbolises strength. is cut off;

her arm is broken,’

declares the Lord.

26‘Make her drunk,

for she has defied the Lord.

Let Moab wallow in her vomit;

let her be an object of ridicule.

27Was not Israel the object of your ridicule?

Was she caught among thieves,

that you shake your head in scorn

whenever you speak of her?

28Abandon your towns and dwell among the rocks,

you who live in Moab.

Be like a dove that makes its nest

at the mouth of a cave.

29‘We have heard of Moab’s pride –

how great is her arrogance! –

of her insolence, her pride, her conceit

and the haughtiness of her heart.

30I know her insolence but it is futile,’ declares the Lord,

‘and her boasts accomplish nothing.

31Therefore I wail over Moab,

for all Moab I cry out,

I moan for the people of Kir Hareseth.

32I weep for you, as Jazer weeps,

you vines of Sibmah.

Your branches spread as far as the sea48:32 Probably the Dead Sea;

they reached as far as48:32 Two Hebrew manuscripts and Septuagint; most Hebrew manuscripts as far as the Sea of Jazer.

The destroyer has fallen

on your ripened fruit and grapes.

33Joy and gladness are gone

from the orchards and fields of Moab.

I have stopped the flow of wine from the presses;

no-one treads them with shouts of joy.

Although there are shouts,

they are not shouts of joy.

34‘The sound of their cry rises

from Heshbon to Elealeh and Jahaz,

from Zoar as far as Horonaim and Eglath Shelishiyah,

for even the waters of Nimrim are dried up.

35In Moab I will put an end

to those who make offerings on the high places

and burn incense to their gods,’ declares the Lord.

36‘So my heart laments for Moab like the music of a pipe;

it laments like a pipe for the people of Kir Hareseth.

The wealth they acquired is gone.

37Every head is shaved

and every beard cut off;

every hand is slashed

and every waist is covered with sackcloth.

38On all the roofs in Moab

and in the public squares

there is nothing but mourning,

for I have broken Moab

like a jar that no-one wants,’ declares the Lord.

39‘How shattered she is! How they wail!

How Moab turns her back in shame!

Moab has become an object of ridicule,

an object of horror to all those around her.’

40This is what the Lord says:

‘Look! An eagle is swooping down,

spreading its wings over Moab.

41Kerioth48:41 Or The cities will be captured

and the strongholds taken.

In that day the hearts of Moab’s warriors

will be like the heart of a woman in labour.

42Moab will be destroyed as a nation

because she defied the Lord.

43Terror and pit and snare await you,

you people of Moab,’

declares the Lord.

44‘Whoever flees from the terror

will fall into a pit,

whoever climbs out of the pit

will be caught in a snare;

for I will bring on Moab

the year of her punishment,’

declares the Lord.

45‘In the shadow of Heshbon

the fugitives stand helpless,

for a fire has gone out from Heshbon,

a blaze from the midst of Sihon;

it burns the foreheads of Moab,

the skulls of the noisy boasters.

46Woe to you, Moab!

The people of Chemosh are destroyed;

your sons are taken into exile

and your daughters into captivity.

47‘Yet I will restore the fortunes of Moab

in days to come,’

declares the Lord.

Here ends the judgment on Moab.

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 48:1-47

ስለ ሞዓብ የተነገረ መልክት

48፥29-36 ተጓ ምብ – ኢሳ 16፥6-12

1ስለ ሞዓብ፤

የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ናባው ትጠፋለችና ወዮላት፤

ቂርያታይም ትዋረዳለች፤ ትያዛለችም፤

ምሽጎች48፥1 ወይም ሚሥጋብ ይደፈራሉ፤ ይፈራርሳሉም።

2ከእንግዲህ ሞዓብ አትከበርም፤

ሰዎች በሐሴቦን48፥2 ሐሴቦን የሚለው የዕብራይስጡ ቃል አነባበብ መዶለት ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው። ተቀምጠው፣

‘ኑ ያቺን አገር እናጥፋት’ ብለው ይዶልቱባታል።

መድሜን48፥2 መድሜን የሚለው የሞዓባውያን ከተማ ስም አነባበብ ጸጥ ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው። ሆይ፤ አንቺም ደግሞ ጸጥ ትደረጊያለሽ፤

ሰይፍም ያሳድድሻል።

3ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣

የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ!

4ሞዓብ ትሰበራለች፤

ልጆቿም ጩኸት ያሰማሉ።48፥4 የዕብራይስጡና የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች ለዞአር ያውጃሉ ይላሉ።

5ክፉኛ እያለቀሱ፣

ወደ ሉሒት ሽቅብ ይወጣሉ፤

ስለ ደረሰባቸውም ጥፋት መራራ ጩኸት እያሰሙ፣

ወደ ሖርናይም ቍልቍል ይወርዳሉ።

6ሽሹ፤ ሕይወታችሁንም አትርፉ!

በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ48፥6 ወይም እንደ አሮኤር ሁኑ።

7በድርጊታችሁና በብልጽግናችሁ ስለምትታመኑ፣

እናንተም ትማረካላችሁ፤

ካሞሽም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር፣

በምርኮ ይወሰዳል።

8በእያንዳንዱ ከተማ ላይ አጥፊ ይመጣል፤

አንድም ከተማ አያመልጥም።

እግዚአብሔር ተናግሯልና፣

ሸለቆው ይጠፋል፤

ዐምባውም ይፈርሳል።

9በርራ እንድታመልጥ፣

ለሞዓብ ክንፍ ስጧት፤

ከተሞቿም ምንም እስከማይኖርባቸው ድረስ፣

ባድማ48፥9 ወይም የተተወች ምድር እንድትሆን/በሞዓብ ላይ ጨው ነስንሱባት ይሆናሉ።

10የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያከናውን ርጉም ይሁን፤

ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚከላከል የተረገመ ይሁን፤

11“ሞዓብ በአንቡላው ላይ እንዳረፈ የወይን ጠጅ፣

ከልጅነት ጀምሮ የተረጋጋ ነበረ፤

ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤

በምርኮም አልተወሰደም፤

ቃናው እንዳለ ነው፤

መዐዛውም አልተለወጠም።

12ስለዚህ ዕቃውን የሚገለብጡ ሰዎችን

የምልክበት ጊዜ ይመጣል፤”

ይላል እግዚአብሔር

“እነርሱም ይደፉታል፤

ዕቃውን ባዶ ያስቀራሉ፤

ማንቈርቈሪያዎቹንም ይሰባብራሉ።

13የእስራኤል ቤት፤

በቤቴል ታምኖ እንዳፈረ ሁሉ፣

ሞዓብም በካሞሽ ያፍራል።

14“እናንተ፣ ‘እኛ ተዋጊዎች ነን፤

በጦርነትም ብርቱ ነን’ ልትሉ እንዴት ቻላችሁ?

15ሞዓብ ትጠፋለች፤ ከተሞቿም ይወረራሉ፤

ምርጥ ወጣቶቿም ወደ መታረድ ይወርዳሉ፤”

ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ፤

16“የሞዓብ ውድቀት ተቃርቧል፤

ጥፋቱም ፈጥኖ ይመጣበታል።

17በዙሪያው የምትኖሩ ሁሉ፤

ዝናውን የምታውቁ ሁሉ አልቅሱለት፤

‘ብርቱው ከዘራ፣

የከበረው በትር እንዴት ሊሰበር ቻለ’ በሉ።

18“ሞዓብን የሚያጠፋ፣

በአንቺ ላይ ይመጣልና፤

የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤

አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፤

ከክብርሽ ውረጂ፤

በደረቅም መሬት ተቀመጪ።

19አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤

በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤

የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣

‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።

20ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤

ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤

የሞዓብን መደምሰስ፣

በአርኖን አጠገብ አስታውቁ።

21ፍርድ በዐምባው ምድር፦

በሖሎን፣ በያሳና በሜፍዓት ላይ፣

22በዲቦን፣ በናባውና በቤት ዲብላታይም ላይ፣

23በቂርያታይም፣ በቤት ጋሙልና በቤትምዖን ላይ፣

24በቂርዮትና በባሶራ ላይ፤

በሩቅና በቅርብ ባሉት በሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቷል።

25የሞዓብ ቀንድ48፥25 ቀንድ እዚህ ቦታ ኀይልን በትእምርትነት ይመለከታል። ተቈርጧል፤

እጁም ተሰባብሯል፤”

ይላል እግዚአብሔር

26እግዚአብሔርን ንቋልና፣

ሞዓብን በመጠጥ አስክሩት።

ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለል፤

ለመዘባበቻም ይሁን።

27በእስራኤል ላይ ስታላግጥ አልነበረምን?

ስለ እርሷ በተናገርህ ቍጥር፣

እያቃለልሃት ራስህን የምትነቀንቀውስ፣

ከሌቦች ጋር ስትሰርቅ ተይዛለችን?

28እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፤

ከከተማ ወጥታችሁ በዐለት መካከል ኑሩ፤

በገደል አፋፍ ላይ ጐጆዋን እንደምትሠራ፣

እንደ ርግብ ሁኑ።

29“ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣

ስለ እብሪቱና ስለ ኵራቱ፣

ስለ ትምክሕቱና ስለ መጓደዱ፣

ስለ ልቡም ማበጥ ሰምተናል።

30መዳፉን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ከንቱ ነው፤”

ይላል እግዚአብሔር

“ጕራውም ፋይዳ አይኖረውም።

31ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤

ለሞዓብ ምድር ሁሉ ዋይ እላለሁ፤

ለቂርሔሬስ ሰዎችም የልቅሶ ድምፅ አሰማለሁ።

32የሴባማ ወይን ሆይ፤

ለኢያዜር ካለቀስሁት እንኳ ይልቅ አለቅስልሻለሁ፤

ቅርንጫፎችሽ እስከ ባሕሩ ተዘርግተዋል፤

እስከ ኢያዜርም ደርሰዋል፤

ለመከር በደረሰው ፍሬሽና በወይንሽ ላይ፣

አጥፊው መጥቷል።

33ከሞዓብ የአትክልት ቦታና ዕርሻ፣

ሐሤትና ደስታ ርቋል፤

የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤

በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤

በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣

የእልልታ ድምፅ አይደለም።

34“ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣

ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣

ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤

የኔሞሬም ውሃ እንኳ ደርቋልና።

35በመስገጃ ኰረብቶች ላይ የሚሠዉትን፣

ለአማልክታቸው የሚያጥኑትን፣

ከሞዓብ አጠፋለሁ፤”

ይላል እግዚአብሔር

36“ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት ያንጐራጕራል፤

ለቂርሔሬስ ሰዎችም እንደ ዋሽንት ያንጐራጕራል።

ያከማቹት ንብረት ጠፍቷልና።

37የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣

ጢምም ሁሉ ተላጭቷል፤

እጅ ሁሉ ተቸፍችፏል፤

ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቋል።

38በሞዓብ ቤቶች ጣራ ሁሉ ላይ፣

በሕዝብም አደባባዮች፣

ሐዘን እንጂ ሌላ የለም፤

እንደማይፈለግ እንስራ፣

ሞዓብን ሰብሬአለሁና፤”

ይላል እግዚአብሔር

39“እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ!

ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ!

ሞዓብ የመሰደቢያ፣

በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”

40እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድበታል፤

ክንፎቹንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።

41ከተሞቹ48፥41 ወይም ቂርያት ይወረራሉ፤

ምሽጎቹም ይያዛሉ፤

በዚያን ቀን የሞዓብ ጦረኞች ልብ፣

በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።

42ሞዓብ እግዚአብሔርን አቃልሏልና ይጠፋል፤

መንግሥትነቱም ይቀራል።

43የሞዓብ ሕዝብ ሆይ፤

ሽብርና ጕድጓድ፣ ወጥመድም ይጠብቅሃል፤”

ይላል እግዚአብሔር

44“ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ፣

ጕድጓድ ውስጥ ይገባል፤

ከጕድጓዱም የሚወጣ፣

በወጥመድ ይያዛል፤

በሞዓብ ላይ፣

የቅጣቱን ዓመት አመጣለሁና፣”

ይላል እግዚአብሔር

45“የሞዓብን ግንባር፣

የደንፊዎችን ዐናት የሚያቃጥል፣

እሳት ከሐሴቦን፣

ነበልባል ከሴዎን ቤት ወጥቷልና፤

ኰብላዮች በሐሴቦን ጥላ ሥር፣

ተስፋ ቈርጠው ቆመዋል።

46ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ!

የካሞሽ ሕዝብ ተደምስሷል፤

ወንዶች ልጆችህ በምርኮ ተወስደዋል፤

ሴቶች ልጆችህም ተግዘዋል።

47“ነገር ግን የኋላ ኋላ፣

የሞዓብን ምርኮ እመልሳለሁ፤”

ይላል እግዚአብሔር

በሞዓብ ላይ የተወሰነው ፍርድ ይኸው ነው።