2 ዜና መዋዕል 9 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 9:1-31

የሳባ ንግሥት ሰሎሞንን ጐበኘች

9፥1-12 ተጓ ምብ – 1ነገ 10፥1-13

1የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ፣ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። ቅመማ ቅመም፣ እጅግ ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮችን በግመሎች አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ደረሰች፤ ወደ ሰሎሞንም ቀርባ በልቧ ያለውን ሁሉ አጫወተችው። 2ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ መለሰላት፤ ሊመልስላት የተሳነው አንዳች ነገር አልነበረም። 3የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን ጥበብና የሠራውን ቤተ መንግሥት፣ 4በገበታው ላይ የሚቀርበውን መብል፣ የሹማምቱን አቀማመጥ፣ አስተናባሪዎቹንና አለባበሳቸውን፣ ጠጅ አሳላፊዎቹንና አለባበሳቸውን እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያቀረባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች9፥4 ወይም ወደ ላይ የሚመጣባቸውን ደረጃዎች ተብሎ መተርጐም ይቻላል። ባየች ጊዜ እጅግ ተደነቀች። 5ንጉሡንም እንዲህ አለችው፤ “ስለ ሥራህና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ሁሉ እውነት ነው። 6ነገር ግን መጥቼ በዐይኔ እስካየሁ ጊዜ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም ነበር፤ በርግጥም የጥበብህ እኩሌታ እንኳ አልተነገረኝም፤ እኔ ከሰማሁት ዝና እጅግ ትልቃለህ። 7ሰዎችህ ምንኛ ታድለዋል! ዘወትር በፊትህ ቆመው ጥበብህን የሚሰሙ ሹማምትህስ ምንኛ ታድለዋል! 8ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ንጉሥ ሆነህ እንድትገዛ፣ በአንተ ደስ የተሰኘውና በዙፋኑ ላይ ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን፤ አምላክህ ለእስራኤል ካለው ፍቅርና ለዘላለም ሊያጸናቸው ካለው ፍላጎት የተነሣ፣ ፍትሕና ጽድቅ እንዲሰፍን ታደርግ ዘንድ አንተን በላያቸው ላይ አንግሦሃልና።”

9ከዚያም ለንጉሡ አንድ መቶ ሃያ መክሊት9፥9 4 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ወርቅ፣ እጅግ ብዙ ቅመማ ቅመምና የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰሎሞን እንደ ሰጠችው ዐይነት ቅመማ ቅመም ያለ ከቶ አልነበረም።

10የኪራም ሰዎችና የሰሎሞን ሰዎች ወርቅ ከኦፊር እንደዚሁም ሰንደልና9፥10 የአልሙግ ዕንጨት ሊሆን ይችላል የከበሩ ድንጋዮች አመጡ። 11ንጉሡም የሰንደሉን ዕንጨት ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና ለቤተ መንግሥቱ ደረጃ መሥሪያ እንደዚሁም ለመዘምራኑ የመሰንቆና የበገና መሥሪያ አደረገው፤ ይህን የመሰለ ነገር በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም።

12ንጉሥ ሰሎሞን ለሳባ ንግሥት የፈለገችውንና የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣት፤ ስጦታውም እርሷ ካመጣችለት በላይ ነበር። ከዚያም ከአጃቢዎቿ ጋር ወደ አገሯ ተመለሰች።

የሰሎሞን ብልጽግና

9፥13-28 ተጓ ምብ – 1ነገ 10፥14-292ዜና 1፥14-17

13ሰሎሞን በየዓመቱ የሚቀበለው ወርቅ ክብደቱ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት9፥13 23 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ነበር። 14ይህም ከታላላቅና ከተራ ነጋዴዎች ከሚገባው ቀረጥ ሌላ ነበር፤ እንዲሁም መላው የዐረብ ነገሥታትና የገዛ ምድሩ አገረ ገዦች ለሰሎሞን ወርቅና ብር ያመጡለት ነበር።

15ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ከጥፍጥፍ ወርቅ የተሠራ ታላላቅ ጋሻዎች አበጀ፤ በእያንዳንዱም ጋሻ የገባው ጥፍጥፍ ወርቅ ስድስት መቶ ሰቅል9፥15 3.5 ኪሎ ግራም ያህል ነው። ነበር። 16እንዲሁም ሦስት መቶ ትንንሽ ጋሻዎች በጥፍጥፍ ወርቅ ሠራ፤ በእነዚህም በእያንዳንዳቸው የገባው ጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል9፥16 1.7 ኪሎ ግራም ይህል ነው ነበር። ንጉሡም ጋሻዎቹን “የሊባኖስ ደን” በተባለው ቤተ መንግሥት ውስጥ አኖራቸው።

17ከዚያም ንጉሡ በዝኆን ጥርስ ያጌጠና በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ትልቅ ዙፋን ሠራ። 18ዙፋኑ ስድስት መውጫ መውረጃ ደረጃዎች ሲኖሩት፣ ከዙፋኑ ጋር የተያያዘ ከወርቅ የተሠራ የእግር መርገጫ ነበረው። መቀመጫውም ግራና ቀኙ መደገፊያ ያለው ሆኖም ከመደገፊያዎቹም አጠገብ አንዳንድ አንበሳ ቆሞ ነበር። 19እንዲሁም በስድስቱ ደረጃዎች ዳርና ዳር ላይ አንዳንድ አንበሳ፣ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር፤ ይህን የመሰለ ዙፋን በየትኛውም አገር ተሠርቶ አያውቅም። 20ንጉሥ ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ “የሊባኖስ ደንቃ” ተብሎ በሚጠራው ቤተ መንግሥት ውስጥ የነበሩትም ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ በሰሎሞን ዘመን ብር ዋጋ እንደሌለው ስለሚቈጠር ከብር የተሠራ አንድም ነገር አልነበረም። 21ንጉሡ በኪራም ሰዎች የሚነዱ የንግድ መርከቦች ነበሩት፤9፥21 ዕብራይስጡ፣ ወደ ተርሴስ ሊሄዱ የሚችሉ መርከቦች ይላል። እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብር፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች እየያዙ ይመለሱ ነበር።

22ንጉሥ ሰሎሞን በሀብትም ሆነ በጥበብ ከምድር ነገሥታት ሁሉ የበለጠ ነበር። 23የምድር ነገሥታት ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበብ ለመስማት ከሰሎሞን ጋር መገናኘት ይፈልጉ ነበር። 24በየዓመቱ ወደ እርሱ የሚመጡትም ሁሉ የብርና የወርቅ ዕቃ፣ የልብስ፣ የጦር መሣሪያና የቅመማ ቅመም እንደዚሁም የፈረስና የበቅሎ ገጸ በረከት ያመጡለት ነበር።

25ሰሎሞን አራት ሺሕ የፈረሶችና የሠረገሎች9፥25 ወይም፣ ሠረገለኞች ተብሎ መተርጐም ይችላል። ጋጥ ነበረው፤ እንዲሁም በሚኖርበት በኢየሩሳሌምና በሰረገላ ከተሞች ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት። 26እርሱም ከኤፍራጥስ ወንዝ9፥26 የኤፍራጥስ ወንዝ ነው፤ ነገር ግን አንዳንድ ቅጆች ኤፍራጥስ የሚለውን ቃል አይጨምሩም እስከ ፍልስጥኤም ምድርና እስከ ግብፅ ዳርቻ ድረስ ባሉት ነገሥታት ሁሉ ላይ ገዛ። 27ንጉሡ በኢየሩሳሌም ብሩን እንደ ማንኛውም ድንጋይ፣ የዝግባውንም ዕንጨት ብዛት በየኰረብታው ግርጌ እንደሚበቅል ሾላ አደረገው። 28ለሰሎሞን ከግብፅና9፥28 በኪልቂያ የምትገኘው ሙዙር ነች። ከሌሎች አገሮች ሁሉ ፈረሶች ያመጡለት ነበር።

የሰሎሞን መሞት

9፥29-31 ተጓ ምብ – 1ነገ 11፥41-43

29ሰሎሞን በዘመነ መንግሥቱ የሠራው ሌላው ነገር በነቢዩ በናታን ታሪክና በሴሎናዊው በአሒያ ትንቢት እንዲሁም ባለ ራእዩ አዶ ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው ራእይ ውስጥ የተጻፈ አይደለምን? 30ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ አርባ ዓመት ነገሠ። 31ከዚያም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ፤ በአባቱም በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁም ሮብዓም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

歷代志下 9:1-31

示巴女王拜訪所羅門

1示巴女王聽聞所羅門的名聲,便來用難題考問他。她率領許多隨從,用駱駝馱著香料、寶石和大量的黃金到耶路撒冷晉見所羅門王,與所羅門談論她心中的疑問。 2所羅門王解答了她所有的問題,沒有一樣難得住他。 3示巴女王看見所羅門的智慧,又看見他建的宮殿、 4席上的美味、入座的群臣、侍立一旁的僕人、他們的服裝、酒政、以及他在耶和華殿裡獻的燔祭,感到萬分驚奇。 5她對所羅門王說:「我在本國聽到的有關你的功業和智慧原來都是真的。 6若不是親眼目睹,我不會相信。事實上,我聽到的還不到一半!你的智慧遠超過我聽到的傳聞。 7你的臣僕經常侍立在你面前聆聽智慧之言,真有福氣! 8你的上帝耶和華當受稱頌!祂喜愛你,立你做王統治祂的子民。因為你的上帝愛以色列人,要使他們永遠堅立,所以立你為他們的王,使你秉公行義。」

9示巴女王將四噸黃金、大量香料和寶石獻給所羅門王。再無人像示巴女王那樣獻給所羅門王那麼多香料。 10希蘭的僕人和所羅門的僕人從俄斐運來黃金、檀香木和寶石。 11所羅門王用這些檀香木建造耶和華的殿和王宮的階梯,又製作歌樂手的琴瑟。在猶大從來沒有見過這樣的物品。 12所羅門王滿足了示巴女王的一切要求,回贈她的禮物超過了她帶來的。之後,女王和隨從就回示巴去了。

所羅門王的財富

13所羅門每年收到的黃金約二十三噸, 14此外還有商人、阿拉伯諸王和國內各總督送給他的金銀。 15所羅門王用錘好的金子打造了二百面大盾牌,每面用七公斤金子; 16又用錘好的金子打造了三百面小盾牌,每面用三點五公斤金子,全部放在黎巴嫩林宮。 17王又造了一個象牙大寶座,外面用純金包裹。 18這寶座有六級臺階,又有金腳凳與寶座相連,寶座兩旁有扶手,扶手兩邊各站著一頭獅子, 19六級臺階上共站著十二頭獅子,每級臺階兩端各站一頭。這寶座舉世無雙。 20所羅門王所有的杯子都是金的,黎巴嫩林宮裡所有的器皿都是純金的,沒有一件是用銀子造的,因為所羅門年間銀子不算什麼。 21王有船隊與希蘭的僕人一起出海去他施,每三年就運回金銀、象牙、猿猴和孔雀。 22所羅門王的財富和智慧超過天下諸王。 23天下的君王都紛紛來朝見所羅門,聆聽上帝賜給他的智言慧語。 24他們年年都帶來禮物,有金銀器皿、衣服、兵器、香料和騾馬。 25所羅門有四千個安置戰車和馬匹的棚,有一萬二千名騎兵,駐紮在屯車城和他所在的耶路撒冷26所羅門統管從幼發拉底河到非利士地區,遠至埃及邊境的諸王。 27王使耶路撒冷的金銀多如石頭,使香柏木多如丘陵的無花果樹。 28所羅門的馬匹都是從埃及和其他國家運來的。

所羅門逝世

29所羅門一生的事蹟,自始至終都記在拿單先知的史記、示羅亞希雅的《預言書》和易多先見論尼八的兒子耶羅波安的《啟示書》中。 30所羅門耶路撒冷統治以色列四十年, 31他與祖先同眠後,葬在他父親大衛的城裡。他兒子羅波安繼位。