2 ዜና መዋዕል 4 – New Amharic Standard Version NASV

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 4:1-22

የቤተ መቅደሱ ዕቃዎች መሟላት

4፥2-6፡10–5፥1 ተጓ ምብ – 1ነገ 7፥23-2638-51

1ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱ ዐሥር ክንድ4፥1 ርዝመቱና ወርዱ 9 ሜትር ቍመቱ 4.5 ሜትር ያህል ነው። የሆነ የናስ መሠዊያ ሠራ። 2እንዲሁም የጐኑ ስፋት ከጠርዝ እስከ ጠርዝ ዐሥር ክንድ፣ ቁመቱ አምስት4፥2 2.3 ሜትር ያህል ነው። ክንድ የሆነ ክብ በርሜል ቀልጦ ከፈሰሰ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ4፥2 13.5 ሜትር ይህል ነው። ሆነ። 3ከበርሜሉ ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኮርማ ቅርጾች4፥3 0.5 ሜትር ያህል ነው። ነበሩበት፤ ኮርማዎቹም ከበርሜሉ ጋር አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር።

4በርሜሉ በዐሥራ ሁለት ኮርማዎች ላይ የቆመ ሲሆን፣ ኮርማዎቹም ሦስቱ ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር። በርሜሉ በእነዚህ ላይ ያረፈ ሲሆን፣ የሁሉም ጀርባ ወደ መካከል የዞረ ነበር። 5የበርሜሉ ውፍረት አንድ ስንዝር፣4፥5 8 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው። ከንፈሩ ደግሞ የጽዋ ከንፈር ወይም የሱፍ አበባ ይመስል ነበር፤ ይህም ሦስት ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ4፥5 66 ኪሎ ሊትር ያህል ነው። የሚይዝ ነበር።

6እንዲሁም ዐሥር የመታጠቢያ ገንዳዎች አሠርቶ አምስቱን በደቡብ፣ አምስቱን ደግሞ በሰሜን በኩል አስቀመጠ፤ ገንዳዎቹ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡት ነገሮች የሚታጠቡባቸው ሲሆኑ፣ በርሜሉ ግን ለካህናት መታጠቢያ የሚያገለግል ነበር።

7በተሰጠው የአሠራር መመሪያ መሠረት፣ ዐሥር የወርቅ መቅረዞች ሠርቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት፣ አምስቱን በስተ ደቡብ፣ አምስቱን በስተ ሰሜን አኖራቸው።

8ዐሥር ጠረጴዛ ሠርቶም ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት አምስቱን በስተ ደቡብ፣ አምስቱን ደግሞ በስተ ሰሜን በኩል አኖራቸው፤ ደግሞም አንድ መቶ ጐድጓዳ የወርቅ ሳሕኖች ሠራ።

9የካህናቱንም አደባባይ ሠራ፤ እንዲሁም ታላቁን አደባባይና በሮቹን ከሠራ በኋላ በናስ ለበጣቸው። 10በርሜሉንም ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ ምሥራቅ ባለው ማእዘን በቀኝ በኩል አኖረው።

11እንዲሁም ምንቸቱን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ። ኪራምም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ለንጉሥ ሰሎሞን ሠርቶ ጨረሰ፤ እነዚህም፦

12ሁለቱ ዐምዶች፣

በአዕማዱ ጫፍ ላይ ያሉት ሁለት ባለ ሳሕን ቅርጽ ጕልላት በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለቱን፣

ባለ ሳሕን ቅርጽ ጕልላት የሚያስጌጡ ሁለት ዙር መርበቦች፤

13በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለቱን፣ ባለ ሳሕን ቅርጽ ጕልላት እንዲያስጌጡ ለእያንዳንዱ መርበብ ሁለት ዙር ሮማኖች ለሁለቱም ዙር መርበቦች በድምሩ አራት መቶ ሮማኖች፤

14መቆሚያዎች ከነመታጠቢያ ሳሕኖቻቸው፤

15በርሜሉና እርሱን የተሸከሙት ዐሥራ ሁለት ኮርማዎች፤

16ምንቸቶችና መጫሪያዎች፣ ሜንጦዎችና ከነዚሁም ጋር የተያያዙ ዕቃዎች።

ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆን ለሰሎሞን የሠራቸው ዕቃዎች በሙሉ ከተወለወለ ናስ የተሠሩ ነበሩ። 17ንጉሡም እነዚህ ዕቃዎች በዮርዳኖስ ሸለቆ፣ በሱኮትና በጽሬዳ መካከል ባለው በሸክላ ዐፈር ቦታ ቀልጠው በሸክላ ቅርጽ ተሠርተው እንዲወጡ አደረገ። 18እነዚህ ሰሎሞን ያሠራቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ ብዙዎች ስለሆኑ የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ሆነ አልታወቀም ነበር።

19እንደዚሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሠራ፤ እነዚህም፦

የወርቅ መሠዊያ፣

የገጸ ኅብስቱ ጠረጴዛ፣

20በተሰጠው መመሪያ መሠረት፣ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት እንዲነድዱ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞች ከነቀንዲሎቻቸው፣

21የወርቅ አበባ ቅርጽ ሥራዎች፣ ቀንዲሎችና መኰስተሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።

22ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ የመብራት ማጥፊያዎች፣ ለመርጨት የሚያገለግሉ ጐድጓዳ ሳሕኖች፣ ጭልፋዎችና ጥናዎች፣ እንደዚሁም የቤተ መቅደሱ የወርቅ መዝጊያዎች፣ ይኸውም የቅድስተ ቅዱሳኑ የውስጠኛው መዝጊያዎችና የቤተ መቅደሱ ዋናው አዳራሽ መዝጊያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።