2 ዜና መዋዕል 34 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 34:1-33

ኢዮስያስ ያደረገው ተሐድሶ

34፥1-2 ተጓ ምብ – 2ነገ 22፥1-2

34፥3-7 ተጓ ምብ – 2ነገ 23፥4-20

34፥8-13 ተጓ ምብ – 2ነገ 22፥3-7

1ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ። 2እርሱም በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር አደረገ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሳይል፣ በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄደ።

3በዘመነ መንግሥቱ በስምንተኛው ዓመት ገና ወጣት ሳለ፣ የአባቱን የዳዊትን አምላክ መፈለግ ጀመረ፤ በዐሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኰረብታ መስገጃ ስፍራዎች፣ ከአሼራ፣ ምስል ዐምዶች፣ ከተቀረጹ ጣዖታትና ቀልጠው ከተሠሩ ምስሎች አነጻ። 4በእርሱም ትእዛዝ የበኣሊም መሠዊያዎችን አፈራረሱ፤ እርሱም ከበላያቸው የነበሩትን የዕጣን መሠዊያዎችን አደቀቀ፤ የአሼራን ምስል ዐምዶችን፣ ጣዖታቱንና ምስሎቹን ሰባብሮ ከፈጫቸው በኋላ፣ ይሠዉላቸው በነበሩት ሰዎች መቃብር ላይ በተነ። 5የካህናቱን ዐጥንት በመሠዊያዎቻቸው ላይ አቃጠለ፤ በዚህ ዐይነትም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አነጻ። 6እስከ ንፍታሌም ባሉ በምናሴ፣ በኤፍሬምና በስምዖን ከተሞች እንዲሁም በዙሪያቸው ባሉ የፈራረሱ አካባቢዎች፣ 7መሠዊያዎችንና የአሼራ ምስል ዐምዶችን አፈራረሰ፤ ጣዖታቱን እንደ ዱቄት አደቀቀ፤ በመላው እስራኤል የሚገኙትንም የዕጣን መሠዊያዎች አነካከተ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

8ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፣ ምድሪቱንና ቤተ መቅደሱን ካነጻ በኋላ፣ የኤዜልያስን ልጅ ሳፋንን፣ የከተማዪቱን ገዥ መዕሤያንና የጸሓፊውን የኢዮአካዝን ልጅ ኢዮአክን የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ይጠግኑ ዘንድ ላካቸው።

9እነርሱም ወደ ሊቀ ካህኑ ወደ ኬልቅያስ ሄደው፣ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የመጣውን ገንዘብ ሰጡት፤ ገንዘቡም በር ጠባቂዎች የነበሩት ሌዋውያን፣ ከምናሴ፣ ከኤፍሬምና ከመላው የእስራኤል ቅሬታዎች እንደዚሁም ከመላው ይሁዳና ከብንያም፣ ከኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች የሰበሰቡት ነበር። 10እነርሱም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ እየተቈጣጠሩ እንዲያሠሩ ለተሾሙት ሰዎች ዐደራ ሰጡ፤ እነዚህም ሰዎች ገንዘቡን ቤተ መቅደሱን ለጠገኑትና ላደሱት ሰዎች ከፈሉ። 11እንዲሁም የይሁዳ ነገሥታት እንዲፈርሱ ላደረጓቸው ሕንጻዎች ጥርብ ድንጋዮችን፣ ሠረገላዎችንና ማገጣጠሚያ ዕንጨቶችን እንዲገዙ ለዐናጢዎችና ለግንበኞች ገንዘብ ሰጡ።

12ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት አከናወኑ። የበላይ ሆነው አመራር የሚሰጧቸውም ከሜራሪ ጐሣ የሆኑት ሌዋውያን፣ ኢኤትና አብድዩ፣ ከቀዓት ጐሣ ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። በዜማ ዕቃ የላቀ ችሎታ የነበራቸው ሌዋውያን ሁሉ፣ 13የጕልበት ሠራተኞች ኀላፊ በመሆን፣ በየሥራው ላይ የተመደቡትን ሠራተኞች ይቈጣጠሩ ነበር። ጥቂቶቹ ሌዋውያን ደግሞ ኀላፊዎች፣ ጸሓፊዎችና በር ጠባቂዎች ነበሩ።

የሙሴ ሕግ መጽሐፍ መገኘት

34፥14-28 ተጓ ምብ – 2ነገ 22፥8-20

34፥29-32 ተጓ ምብ – 2ነገ 23፥1-3

14ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የገባውን ገንዘብ በሚያወጡበት ጊዜ፣ ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ። 15ኬልቅያስም ጸሓፊውን ሳፋንን፣ “የሕጉን መጽሐፍ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አገኘሁት” አለው፤ ከዚያም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው።

16ሳፋንም መጽሐፉን ወደ ንጉሡ ወስዶ እንዲህ አለው፤ “ሹማምትህ የታዘዙትን ሁሉ በመፈጸም ላይ ናቸው፤ 17በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የነበረውንም ገንዘብ አውጥተው ለተቈጣጣሪዎቹና ለሠራተኞቹ አስረክበዋል።”

18ከዚያም ጸሓፊው ሳፋን ንጉሡን፣ “ካህኑ ኬልቅያስ መጽሐፍ ሰጥቶኛል” አለው። ሳፋንም መጽሐፉን ለንጉሡ አነበበለት።

19ንጉሡም የሕጉን ቃል በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ። 20እርሱም ለኬልቅያስ፣ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም፣ ለሚክያስ ልጅ ለዓብዶን፣ ለጸሓፊው ለሳፋንና ለንጉሡ የቅርብ አገልጋይ ለዓሳያ ይህን ትእዛዝ ሰጠ፤ 21“ሄዳችሁ ስለ እኔ እንደዚሁም በእስራኤልና በይሁዳ ስላሉት ቅሬታዎች በተገኘው መጽሐፍ ውስጥ ስለ ተጻፈው ነገር እግዚአብሔርን ጠይቁ። አባቶቻችን የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቁ በላያችን ላይ ታላቅ የእግዚአብሔር ቍጣ ፈስሷል፤ በዚህ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት አልተመላለሱምና።”

22ኬልቅያስና ንጉሡ ከእርሱ ጋር የላካቸው34፥22 አንድ የዕብራይስጥ ቅጅ እንዲሁም ቩልጌትና የሱርስት ትርጕሞች በዚህ ሲስማሙ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ከእርሱ ጋር የላካቸው የሚለውን አይጨምሩም። ሰዎች የአልባሳት ጠባቂ የነበረው የሐስራ ልጅ፣ የቲቁዋ ልጅ የሴሌም ሚስት ወደ ሆነችው ወደ ነቢዪቱ ወደ ሕልዳና ሄደው ነገሯት። እርሷም በኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው ክፍለ ከተማ ትኖር ነበር።

23ነቢዪቱም እንዲህ አለቻቸው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ 24እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ በተጻፈው ርግማን ሁሉ መሠረት፣ በዚህ ስፍራና በሕዝቡ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ። 25እኔን ትተውኝ ለሌሎች አማልክት ዕጣን ስላጠኑና እጃቸው በሠራው ነገር ሁሉ34፥25 ወይም ባደረጉት ነገር ሁሉ ለቍጣ ስላነሣሡኝ፣ ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።’ 26እግዚአብሔርን ለመጠየቅ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፤ ‘ስለ ሰማኸው ቃል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ 27በዚህ ስፍራና በሕዝቡ ላይ የተናገረውን በሰማህ ጊዜ፣ ልብህ ስለ ተነካና በእግዚአብሔርም ፊት ራስህን ስለ አዋረድህ፣ እንዲሁም በእኔ ፊት ራስህን ዝቅ ስላደረግህ፣ ልብስህንም በመቅደድ በፊቴ ስለ አለቀስህ፣ ሰምቼሃለሁ ይላል እግዚአብሔር28እነሆ፤ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላምም ትቀበራለህ፤ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ የማመጣውን መከራ ሁሉ በዐይንህ አታይም።’ ” መልሷንም ይዘው ወደ ንጉሡ ሄዱ።

29ከዚያም ንጉሡ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድ ላይ ሰበሰበ። 30እርሱም ከትንሽ እስከ ትልቅ ካሉት ከይሁዳ ሰዎች፣ ከኢየሩሳሌም ሕዝብ፣ ከካህናትና ከሌዋውያን ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወጣ። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተገኘውንም የኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ ለሕዝቡ አነበበላቸው 31ንጉሡም በዐምዱ አጠገብ ቆሞ፣ እግዚአብሔርን ይከተል ዘንድ በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ ትእዛዞቹን፣ ሕግጋቱንና ሥርዐቱን ለመጠበቅ፣ በዚህ መጽሐፍ ለተጻፈውም የኪዳን ቃል ለመታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ኪዳኑን ዐደሰ።

32ከዚህ በኋላ በኢየሩሳሌምና በብንያም የሚኖረው ሁሉ በዚህ ነገር ቃል እንዲገባ አደረገ፤ የኢየሩሳሌምም ሕዝብ የአባቶቹ አምላክ ባዘዘው የአምላክ ቃል ኪዳን መሠረት ፈጸሙ።

33ኢዮስያስም አስጸያፊ ጣዖታትን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ግዛት አስወገደ፤ በእስራኤል የነበሩትም ሁሉ አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አደረገ፤ እርሱ በሕይወት እያለም የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ አላሉም።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

歷代志下 34:1-33

猶大王約西亞

1約西亞八歲登基,在耶路撒冷執政三十一年。 2他做耶和華視為正的事,效法他祖先大衛,不偏不離。

約西亞清除偶像

3他執政第八年,雖然還年幼,卻開始尋求他祖先大衛的上帝。他執政第十二年,開始清除猶大耶路撒冷的邱壇、亞舍拉神像、雕刻和鑄造的偶像。 4眾人在他面前拆毀巴力的祭壇,他砍掉高高的香壇,又把亞舍拉神像及雕刻和鑄造的偶像磨成粉末,撒在祭拜它們之人的墳墓上, 5把它們祭司的骸骨放在它們的壇上焚燒。這樣,他潔淨了猶大耶路撒冷6約西亞還在瑪拿西以法蓮西緬,遠至拿弗他利的各城邑及其周圍的荒廢之地做了同樣的事情。 7他拆毀祭壇和亞舍拉神像,把偶像磨成粉末,砍掉以色列境內所有的香壇,然後回到耶路撒冷

發現律法書

8約西亞執政第十八年,潔淨國土和聖殿以後,就差遣亞薩利雅的兒子沙番耶路撒冷的總督瑪西雅約哈斯的兒子約亞史官負責整修他的上帝耶和華的殿。 9他們到希勒迦大祭司那裡,把獻給上帝殿的銀子交給他。這銀子是守殿門的利未人從瑪拿西人和以法蓮人,所有剩下的以色列人,所有的猶大人和便雅憫人,以及耶路撒冷的居民那裡收來的。 10他們把銀子交給負責管理耶和華殿的督工,由他們轉交給整修耶和華殿的工人, 11也就是木匠和石匠,讓他們用來購買鑿好的石頭、木架和棟樑,整修猶大諸王毀壞的殿。 12工人都忠誠地工作。他們的督工是利未米拉利的子孫雅哈俄巴底哥轄的子孫撒迦利亞米書蘭。其他精通樂器的利未13負責監督搬運工人,還有一些做書記、官員和殿門守衛。

14他們把奉獻到耶和華殿裡的銀子拿出來的時候,希勒迦祭司發現了摩西所傳的耶和華的律法書。 15希勒迦就對沙番書記說:「我在耶和華的殿裡發現了律法書。」希勒迦就把書卷交給沙番16沙番把書卷帶到王那裡,向王稟告說:「凡交給僕人們辦的事,都已辦妥。 17耶和華殿裡的銀子已被取出來交給督工和工人。」 18沙番書記又對王說:「希勒迦祭司交給我一卷書。」沙番就在王面前誦讀這書。 19王聽了律法書上的話,就撕裂衣服, 20吩咐希勒迦沙番的兒子亞希甘米迦的兒子亞比頓沙番書記和王的臣僕亞撒雅21「你們去為我、為以色列猶大的餘民求問耶和華有關這書卷上的話。耶和華的烈怒已經臨到我們身上,因為我們的祖先沒有遵守耶和華的話,沒有遵行這書卷上的話。」

22於是,王派去的人跟著希勒迦去求問女先知戶勒妲,她是負責管理禮服的沙龍之妻。沙龍哈斯拉的孫子、特瓦的兒子。戶勒妲住在耶路撒冷第二區。他們向她說明來意, 23她對他們說:「以色列的上帝耶和華要你們回去告訴差你們來見我的人, 24耶和華說,『我要照在猶大王面前所讀的那書上的一切咒詛,降災難給這地方及這裡的居民。 25因為他們背棄我,給別的神明燒香,製造偶像惹我發怒,所以我的怒火要在這地方燃燒,絕不止息。』 26你們告訴差你們來求問耶和華的猶大王,『至於你所聽見的那些話,以色列的上帝耶和華說, 27因為你聽到我對這地方及這裡居民的警告,便悔改,在我面前謙卑、撕裂衣服,向我哭泣,我垂聽了你的禱告。這是我耶和華說的。 28我會讓你平安入土,你不會看到我要降給這地方及這裡居民的一切災難。』」他們便回去稟告王。

約西亞立約順服上帝

29於是,王召集猶大耶路撒冷的所有長老, 30猶大人和耶路撒冷的居民、祭司和利未人等全體民眾,不論貴賤,一同上到耶和華的殿。王把在耶和華殿中發現的約書念給他們聽。 31王站在自己的位置上,在耶和華面前立約,要全心全意地跟隨耶和華,遵從祂的一切誡命、法度和律例,履行約書上的規定。 32他使耶路撒冷便雅憫的人都遵行這約。於是,耶路撒冷的居民都遵行他們祖先的上帝的約。 33約西亞除去以色列境內所有的可憎之物,又吩咐所有住在以色列的人都事奉他們的上帝耶和華。約西亞在世時,他們都沒有偏離他們祖先的上帝耶和華。