2 ዜና መዋዕል 32 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 32:1-33

ሰናክሬም በኢየሩሳሌም ላይ ዛተ

32፥9-19 ተጓ ምብ – 2ነገ 18፥17-35ኢሳ 36፥2-20

32፥20-21 ተጓ ምብ – 2ነገ 19፥35ኢሳ 37፥36-38

1ሕዝቅያስ እንዲህ ባለ ታማኝነት ነገሮችን ሁሉ ካከናወነ በኋላ፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ይሁዳን ወረረ። ድል አድርጎ የራሱ ሊያደርጋቸው በማሰብም የተመሸጉትን ከተሞች ከበበ።

2ሕዝቅያስም ሰናክሬም መምጣቱንና ኢየሩሳሌምንም ለመውጋት ማሰቡን ባወቀ ጊዜ፣ 3ከከተማዪቱ ውጭ ያሉት የውሃ ምንጮች እንዲዘጉ ከሹማምቱና ከጦር አለቆቹ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት። 4ብዙ ሰዎችም ተሰብስበው “የአሦር ነገሥታት32፥4 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል የሰብዓ ሊቃናትና የሱርስቱ ትርጕም ግን፣ ንጉሥ ይላል። መጥተው ስለ ምን ብዙ ውሃ ያገኛሉ?” በማለት ምንጮቹን ሁሉና በምድር ውስጥ ለውስጥ ይተላለፍ የነበረውን ውሃ ዘጉ። 5ከዚህ በኋላም ንጉሡ ጠንክሮ በመሥራት፣ ከቅጥሩ የፈራረሱትን ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ማማ ሠራበት፤ በውጭ በኩልም ሌላ ቅጥር በመገንባት የዳዊትን ከተማ ድጋፍ እርከን አጠናከረ፤ እንደዚሁም ብዙ የጦር መሣሪያዎችንና ጋሻዎችን ሠራ።

6የጦር መኮንኖችንም በሕዝቡ ላይ ሾሞ በከተማዪቱ በር አደባባይ ላይ በፊቱ ከሰበሰበ በኋላ፣ እንዲህ ሲል አበረታታቸው፤ 7“በርቱ፤ ጠንክሩ፤ ከእኛ ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ስለሚበልጥ፣ የአሦርን ንጉሥና አብሮት ያለውን ብዙ ሰራዊት አትፍሩ፤ አትደንግጡም። 8ከእነርሱ ጋር ያለው የሥጋ ክንድ ሲሆን፣ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና ጠላታችንን የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው።” ሕዝቡም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ በተናገረው ቃል ተበረታታ።

9ከዚህ በኋላ ሰናክሬም ከሰራዊቱ ሁሉ ጋር ለኪሶን ከብቦ ሳለ፣ የሚከተለውን መልእክት በጦር መኰንኖቹ አማካይነት፣ ለሕዝቅያስና ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ለነበሩት ለይሁዳ ሕዝብ ላከ፤

10“የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም የሚለው ይህ ነው፤ በተከበበችው በኢየሩሳሌም እስከዚህ የቈያችሁት በማን ተማምናችሁ ነው? 11ሕዝቅያስ፣ ‘አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል’ ማለቱስ በራብና በጥማት እንድትሞቱ ሊያስታችሁ አይደለምን? 12ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም፣ ‘በአንድ መሠዊያ ፊት ስገዱ፤ በላዩም መሥዋዕት አቃጥሉ’ በማለት የራሱን አምላክ የኰረብታ መስገጃ ስፍራዎችንና መሠዊያዎችን ያስወገደስ ሕዝቅያስ አይደለምን?

13“እኔና አባቶቼ በሌሎች አገሮች ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደረግነውን አታውቁምን? ታዲያ የእነዚያ መንግሥታት አማልክት ምድራቸውን ከእጄ ለማዳን ችለዋልን? 14አባቶቼ ካጠፏቸው ከእነዚህ የመንግሥታት አማልክት ሁሉ፣ ሕዝቡን ከእጄ ሊያድን የቻለ አምላክ የትኛው ነው? ታዲያ አምላካችሁ እንዴት ከእጄ ሊያድናችሁ ይችላል? 15አሁንም ሕዝቅያስ በዚህ ዐይነት አያታልላችሁ፤ አያስታችሁም። የየትኛውም አገር ሕዝብ ወይም መንግሥት አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ወይም ከአባቶቼ እጅ መታደግ የቻለ ስለሌለ አትመኑት። የእናንተ አምላክማ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ ምንኛ ያንስ!”

16የሰናክሬም ሹማምትም በእግዚአብሔር አምላክና በባሪያው በሕዝቅያስ ላይ ከዚህ የከፋ ብዙ ነገር ተናገሩ። 17ንጉሡም እንደዚሁ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በመሳደብ፣ “የሌሎቹ አገሮች ሕዝቦች አማልክት፣ ከእጄ እንዳልታደጉ ሁሉ፣ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ሊታደግ አይችልም” ሲል በእርሱ ላይ ደብዳቤ ጻፈ። 18ከዚያም በማስደንገጥና በማስፈራራት ከተማዪቱን ለመያዝ ሲሉ በቅጥሩ ላይ ወደ ተቀመጠው ወደ ኢየሩሳሌም ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በዕብራይስጥ ቋንቋ ጮኹ፤ 19የሰው እጅ በሠራቸው በሌሎች የምድር አሕዛብ አማልክት ላይ እንደ ተናገሩት ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም አምላክ ላይም ተናገሩ።

20ንጉሥ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ስለዚህ ጕዳይ በጸሎት ወደ ሰማይ ጮኹ። 21እግዚአብሔርም መልአክ ልኮ በአሦር ንጉሥ ሰፈር ተዋጊዎችን፣ መሪዎችንና የጦር መኰንኖችን እንዲያጠፋቸው አደረገ። ስለዚህ ንጉሡ በውርደት ወደ ገዛ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩ ቤተ ጣዖት እንደ ገባም፣ የገዛ ወንዶች ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት።

22እግዚአብሔርም ሕዝቅያስንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬምና ከሌሎችም እጅ ሁሉ አዳናቸው፤ በዙሪያቸው ካሉትም ሁሉ ጠበቃቸው32፥22 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል የሰብዓ ሊቃናት የቩልጌት ቅጆች ግን አሳረፋቸው ይላል።23ብዙዎችም ለእግዚአብሔር መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስም ውድ የሆኑ ገጸ በረከቶችን አመጡለት፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።

የሕዝቅያስ ዕብሪት፣ ያከናወናቸው ተግባሮችና ሞቱ

32፥24-33 ተጓ ምብ – 2ነገ 20፥1-21ኢሳ 37፥21-3838፥1-8

24በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ ታሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ እርሱም መለሰለት፤ ምልክትም ሰጠው። 25የሕዝቅያስ ልብ ግን ታበየ እንጂ ስለ ተደረገለት በጎ ነገር ተገቢ ምላሽ አልሰጠም፤ በዚህ ምክንያት የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ። 26ይሁን እንጂ ሕዝቅያስና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ስለ ልባቸው ትዕቢት ራሳቸውን አዋረዱ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በዘመነ መንግሥቱ አልመጣባቸውም።

27ሕዝቅያስ እጅግ ብዙ ሀብትና ክብር ነበረው፤ ከዚህ የተነሣም ለብሩ፣ ለወርቁ፣ ለከበሩት ዕንቍዎቹ፣ ለቅመማ ቅመሞቹ፣ ለጋሻዎቹና ለተለያዩ ውድ ዕቃዎቹ ሁሉ ግምጃ ቤቶችን ሠራ። 28እንደዚሁም ለእህሉ፣ ለወይን ጠጁና ለዘይቱ ማከማቻ የሚሆኑ ግምጃ ቤቶች ለተለያዩ እንስሳት በረት ለበግና ለፍየል መንጋም በረት ሠራ። 29እግዚአብሔር ታላቅ ብልጽግና ስለ ሰጠው፤ ብዙ የበግና የፍየል፣ የእንስሳትም መንጋ ሰበሰበ፤ መንደሮችንም ሠራ።

30የላይኛውን የግዮንን ምንጭ መውጫ ገድቦ፣ ውሃውን በቦይ ቍልቍል ወደ ምዕራቡ የዳዊት ከተማ እንዲወርድ ያደረገም ይኸው ሕዝቅያስ ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ተከናወነለት። 31ነገር ግን በምድሪቱ ላይ ስለ ተፈጸመው ታምራዊ ምልክት እንዲጠይቁት፣ የባቢሎን ገዦች መልእክተኞችን በላኩ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሊፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ሊያውቅ ስለ ፈለገ ተወው።

32በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራና ቸርነቱ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራእይ፣ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። 33ሕዝቅያስም እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ፤ የዳዊት ዘሮች መካነ መቃብር በሆነው ኰረብታም ተቀበረ። በሞተም ጊዜ ይሁዳ ሁሉና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በሙሉ አከበሩት። ልጁ ምናሴም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

歷代志下 32:1-33

希西迦加強防禦

1希西迦忠心地辦好這些事以後,亞述西拿基立起兵入侵猶大,圍攻各堅城,企圖攻佔這些城。 2希西迦西拿基立定意要攻打耶路撒冷3就與眾官員和將領商議,決定截斷城外的水源,眾人也都贊成。 4於是,他們召集大批民眾,截斷所有的水源和過境的溪流,不讓亞述王得到充足的水。 5希西迦發憤圖強,修築所有被毀壞的城牆,在上面建造城樓,在城外加建一道牆,並在大衛城的米羅加強防禦,製造許多兵器和盾牌。 6他委任將領管理民眾,將他們全部召集在城門的廣場上,訓勉他們說: 7「你們要剛強勇敢,不要在亞述王和他的大軍面前恐懼驚慌,因為與我們同在的比與他同在的更有能力。 8那與他同在的只是血肉之軀,與我們同在的卻是我們的上帝耶和華,祂必幫助我們,為我們作戰。」眾人因猶大希西迦的這番話而得到鼓舞。

亞述恐嚇耶路撒冷

9之後,亞述西拿基立率領全軍圍攻拉吉,同時派遣使者到耶路撒冷城,對猶大希西迦和城中所有的猶大人說: 10亞述西拿基立這樣說,『你們仍然留在被困的耶路撒冷,究竟倚仗什麼呢? 11希西迦說你們的上帝耶和華會從亞述王手中拯救你們,難道你們不知道這是哄騙你們的話,是要叫你們留在這裡饑渴至死嗎? 12希西迦不是曾經廢掉耶和華的邱壇和祭壇,吩咐猶大人和耶路撒冷人只在一個祭壇前敬拜,在祭壇上燒香嗎? 13難道你們不知道我和我的祖先怎樣對付列國嗎?列國的神明哪個能從我手中救自己的國家呢? 14我祖先所滅的列國中,有哪國的神明能從我手中救自己的國民呢?難道你們的上帝能從我手中救你們嗎? 15所以,不要讓希西迦欺騙、迷惑你們,也不要相信他!任何民族或國家的神明都不能從我和我祖先手中救他的人民,何況你們的上帝呢?』」

16亞述王的使者還用別的話譭謗耶和華上帝和祂的僕人希西迦17西拿基立還寫信侮辱以色列的上帝耶和華說:「既然列邦的神明都不能從我手中救自己的人民,希西迦的上帝也不例外。」 18亞述王的使者用希伯來語大聲向城牆上的耶路撒冷人喊話,威嚇他們,使他們懼怕,以便攻取城。 19他把耶路撒冷的上帝與世間人手所造的神像相提並論。

耶和華拯救耶路撒冷

20於是,希西迦王和亞摩斯的兒子以賽亞先知向天上的上帝呼求禱告。 21耶和華就差遣一個天使進入亞述王營中,毀滅了所有的勇士、官長和將領。西拿基立只好滿臉羞愧地返回自己的國家。趁他去他神明的廟裡時,他的幾個親生兒子用刀殺了他。 22這樣,耶和華從亞述西拿基立及一切仇敵手中拯救了希西迦耶路撒冷的居民,使他們四境平安。 23許多人帶著祭物到耶路撒冷獻給耶和華,也帶許多名貴的禮物送給猶大希西迦。此後,希西迦受到各國的敬重。

希西迦的疾病和驕傲

24那時,希西迦病危,他向耶和華祈求。耶和華應允了他,賜給他一個徵兆。 25希西迦卻沒有為他所蒙的恩典而感謝上帝,因為他心中驕傲。因此,上帝的烈怒臨到他、猶大耶路撒冷26後來希西迦耶路撒冷的居民發覺自己心裡驕傲,就謙卑下來。因此,在希西迦有生之年,耶和華的烈怒沒有臨到他們。

希西迦的財富和尊榮

27希西迦極有財富和尊榮。他建造庫房來存放他的金、銀、寶石、香料、盾牌和各種珍寶, 28又建造倉庫來貯藏穀物、新酒和新油,並為各類牲畜蓋棚立圏。 29他為自己建造城邑,並且擁有大批的牛羊,因為上帝賜他極多的財富。 30他截斷基訓的上泉,將水引到大衛城的西邊。希西迦凡事亨通。 31然而,當巴比倫的使者來見他,詢問他有關這地方發生的奇蹟時,上帝就讓希西迦自行處理,為要試驗他,好知道他內心如何。

希西迦逝世

32希西迦其他的事蹟和他對耶和華的忠誠都記在亞摩斯的兒子以賽亞先知的《啟示書》上,以及《猶大和以色列的列王史》上。 33希西迦與祖先同眠後,葬在大衛子孫墓地的高處。所有猶大人和耶路撒冷的居民都向他致哀。他兒子瑪拿西繼位。