2 ዜና መዋዕል 28 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 28:1-27

የይሁዳ ንጉሥ አካዝ

28፥1-27 ተጓ ምብ – 2ነገ 16፥1-20

1አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር እንዳደረገው እንደ አባቱ እንደ ዳዊት አላደረገም። 2በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በኣሊምን ለማምለክም የተቀረጹ ጣዖታትን ሠራ። 3እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ያስወገዳቸውን አሕዛብ ልማድ በመከተል፣ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ዐጠነ፤ ወንዶች ልጆቹንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። 4በኰረብታ መስገጃዎችና በተራሮች ዐናት ላይ፣ በየዛፉም ጥላ ሥር መሥዋዕት አቀረበ፤ ዕጣንም ዐጠነ።

5ስለዚህ አምላኩ እግዚአብሔር ለሶርያ ንጉሥ አሳልፎ ሰጠው፤ ሶርያውያንም ድል አደረጉት፤ ከሕዝቡም ብዙዎቹን ምርኮኞች አድርገው ወደ ደማስቆ ወሰዷቸው። ደግሞም ለእስራኤል ንጉሥ ዐልፎ ተሰጠ፤ እርሱም ከባድ ጕዳት አደረሰበት። 6ይሁዳ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለ ተወ፣ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ መቶ ሃያ ሺሕ ወታደሮች ገደለ። 7ጦረኛው ኤፍሬማዊ ዝክሪም የንጉሡን ልጅ መዕሤያን፣ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን ዓዝሪቃምንና ለንጉሡ በማዕረግ ሁለተኛ ሰው የሆነውን ሕልቃናን ገደለ። 8እስራኤላውያንም ከገዛ ወገኖቻቸው ሁለት መቶ ሺሕ ባለ ትዳር ሴቶችን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ማረኩ፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ ምርኮ ይዘው ወደ ሰማርያ ተመለሱ።

9ዖዴድ የተባለ የእግዚአብሔር ነቢይ በዚያ ስለ ነበር፣ ሰራዊቱ ወደ ሰማርያ በተመለሰ ጊዜ ለመቀበል ወጣ፤ እንዲህም አላቸው፤ “የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ይሁዳን ስለ ተቈጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣችሁ፤ እናንተ ግን እስከ ሰማይ በሚደርስ ቍጣ ፈጃችኋቸው። 10አሁንም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ወንዶችና ሴቶች፣ ባሪያዎቻችሁ ልታደርጓቸው ትፈልጋላችሁ፤ እናንተስ ብትሆኑ ኀጢአት ሠርታችሁ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አልበደላችሁምን? 11እንግዲህ ስሙኝ፤ የእግዚአብሔር አስፈሪ ቍጣ በእናንተ ላይ ነድዷልና፣ በምርኮ ያመጣችኋቸውን ወገኖቻችሁን መልሷቸው።”

12ከዚያም ከኤፍሬም መሪዎች ጥቂቶቹ የዮሐናን ልጅ ዓዛርያስ፣ የምሺሌሞት ልጅ በራክያ፣ የሰሎም ልጅ ይሒዝቅያ፣ የሐድላይ ልጅ ዓሜሳይ ከጦርነቱ የተመለሱትን በመቃወም፣ 13“እነዚህን ምርኮኞች እዚህ ማምጣት አልነበረባችሁም፤ አለዚያ እኛ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች እንሆናለን፤ በኀጢአታችንና በበደላችን ላይ ሌላ ልትጨምሩ ታስባላችሁን? በደላችንማ ቀድሞውኑ በዝቷል፤ ቍጣውም በእስራኤል ላይ ነውና” አሉ።

14ስለዚህ ወታደሮቹ በሹማምቱና በጉባኤው ሁሉ ፊት ምርኮኞቹን ለቀቁ፤ የተማረከውንም ዕቃ መለሱ። 15በስም የተጠቀሱ ሰዎችም ምርኮኞቹን ተረክበው ዕራቍታቸውን ለቀሩት ሁሉ ከምርኮው አለበሷቸው፤ ልብስና ጫማ፣ ምግብና መጠጥ ሰጧቸው፣ በቅባትም ቀቧቸው፤ የደከሙትንም ሁሉ በአህያ ላይ አስቀመጧቸው። ከዚያም ወገኖቻቸው ወደሚገኙባት የዘንባባ ከተማ ተብላ ወደምትጠራው ወደ ኢያሪኮ ወስደዋቸው፣ ወደ ሰማርያ ተመለሱ።

16በዚያን ጊዜ ንጉሡ አካዝ ወደ አሦር ንጉሥ ልኮ ርዳታ ጠየቀ፤28፥16 አንድ የዕብራይስጥ ቅጅ፣ የሰብዓ ሊቃናትና የሱርስቱ ቅጅ እንዲሁም (2ነገ 16፥7) ከዚህ ጋር ይስማማል፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ትርጕሞች ግን ነገሥታት ይላሉ። 17ኤዶማውያን እንደ ገና መጥተው በይሁዳ ላይ አደጋ በመጣል ምርኮኞችን ወስደው ነበርና። 18ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በየኰረብታው ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ያሉትን ከተሞች በመውረር ቤትሳሚስን፣ ኤሎንን፣ ግዴሮትን፣ ሦኮን፣ ተምናን፣ ጊምዞንና በአካባቢአቸው የሚገኙትን መንደሮች ሁሉ ያዙ፤ ተቀመጡባቸውም። 19የእስራኤል28፥19 በዜና መዋዕል ካልዕ መጽሐፍ ተደጋግሞ እንደ ተጠቀሰው ይህ ይሁዳ ነው። ንጉሥ አካዝ ክፋትን በይሁዳ ምድር ስላስፋፋና ለእግዚአብሔርም የነበረውን ታማኝነት በከፍተኛ ደረጃ ስላጓደለ፣ እግዚአብሔር ይሁዳን አዋረደ። 20የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር ወደ እርሱ መጥቶ ነበር፤ ሆኖም ችግር ፈጠረበት እንጂ አልረዳውም። 21አካዝ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ከቤተ መንግሥቱና ከመሳፍንቱ ጥቂት ዕቃዎች ወስዶ ለአሦር ንጉሥ ሰጥቶ ነበር፤ ይህም አልረዳውም።

22ንጉሥ አካዝ በተጨነቀ ጊዜም፣ ለእግዚአብሔር የነበረውን ታማኝነቱን ከምን ጊዜውም ይበልጥ አጓደለ፤ 23እርሱም “የሶርያ ነገሥታት አማልክት እነርሱን ስለ ረዷቸው፣ እኔንም ይረዱኝ ዘንድ እሠዋላቸዋለሁ” ሲል እርሱን ላሸነፉት የደማስቆ አማልክት መሥዋዕት አቀረበ።

24አካዝ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃዎች ሁሉ አንድ ላይ ሰብስቦ ወሰደ28፥24 ወይም ሰበረ ተብሎ መተርጐም ይችላል።የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በሮች ዘጋ፤ በኢየሩሳሌምም በየአውራ ጎዳናው ማእዘን ላይ መሠዊያ አቆመ። 25በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚያቃጥልባቸውን የኰረብታ መስገጃዎች ሠራ፤ በዚህም የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለቍጣ አነሣሣው።

26በአካዝ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባርና አካሄዱ ሁሉ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። 27አካዝ እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ፤ በኢየሩሳሌምም ከተማ ተቀበረ፤ የተቀበረው ግን በእስራኤል ነገሥታት መካነ መቃብር አልነበረም። ልጁ ሕዝቅያስም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።

New International Version – UK

2 Chronicles 28:1-27

Ahaz king of Judah

1Ahaz was twenty years old when he became king, and he reigned in Jerusalem for sixteen years. Unlike David his father, he did not do what was right in the eyes of the Lord. 2He followed the ways of the kings of Israel and also made idols for worshipping the Baals. 3He burned sacrifices in the Valley of Ben Hinnom and sacrificed his children in the fire, engaging in the detestable practices of the nations that the Lord had driven out before the Israelites. 4He offered sacrifices and burned incense at the high places, on the hilltops and under every spreading tree.

5Therefore the Lord his God delivered him into the hands of the king of Aram. The Arameans defeated him and took many of his people as prisoners and brought them to Damascus.

He was also given into the hands of the king of Israel, who inflicted heavy casualties on him. 6In one day Pekah son of Remaliah killed a hundred and twenty thousand soldiers in Judah – because Judah had forsaken the Lord, the God of their ancestors. 7Zikri, an Ephraimite warrior, killed Maaseiah the king’s son, Azrikam the officer in charge of the palace, and Elkanah, second to the king. 8The men of Israel took captive from their fellow Israelites who were from Judah two hundred thousand wives, sons and daughters. They also took a great deal of plunder, which they carried back to Samaria.

9But a prophet of the Lord named Oded was there, and he went out to meet the army when it returned to Samaria. He said to them, ‘Because the Lord, the God of your ancestors, was angry with Judah, he gave them into your hand. But you have slaughtered them in a rage that reaches to heaven. 10And now you intend to make the men and women of Judah and Jerusalem your slaves. But aren’t you also guilty of sins against the Lord your God? 11Now listen to me! Send back your fellow Israelites that you have taken as prisoners, for the Lord’s fierce anger rests on you.’

12Then some of the leaders in Ephraim – Azariah son of Jehohanan, Berekiah son of Meshillemoth, Jehizkiah son of Shallum, and Amasa son of Hadlai – confronted those who were arriving from the war. 13‘You must not bring those prisoners here,’ they said, ‘or we will be guilty before the Lord. Do you intend to add to our sin and guilt? For our guilt is already great, and his fierce anger rests on Israel.’

14So the soldiers gave up the prisoners and plunder in the presence of the officials and all the assembly. 15The men designated by name took the prisoners, and from the plunder they clothed all who were naked. They provided them with clothes and sandals, food and drink, and healing balm. All those who were weak they put on donkeys. So they took them back to their fellow Israelites at Jericho, the City of Palms, and returned to Samaria.

16At that time King Ahaz sent to the kings28:16 Most Hebrew manuscripts; one Hebrew manuscript, Septuagint and Vulgate (see also 2 Kings 16:7) king of Assyria for help. 17The Edomites had again come and attacked Judah and carried away prisoners, 18while the Philistines had raided towns in the foothills and in the Negev of Judah. They captured and occupied Beth Shemesh, Aijalon and Gederoth, as well as Soko, Timnah and Gimzo, with their surrounding villages. 19The Lord had humbled Judah because of Ahaz king of Israel,28:19 That is, Judah, as frequently in 2 Chronicles for he had promoted wickedness in Judah and had been most unfaithful to the Lord. 20Tiglath-Pileser28:20 Hebrew Tilgath-Pilneser, a variant of Tiglath-Pileser king of Assyria came to him, but gave him trouble instead of help. 21Ahaz took some of the things from the temple of the Lord and from the royal palace and from the officials and presented them to the king of Assyria, but that did not help him.

22In his time of trouble King Ahaz became even more unfaithful to the Lord. 23He offered sacrifices to the gods of Damascus, who had defeated him; for he thought, ‘Since the gods of the kings of Aram have helped them, I will sacrifice to them so that they will help me.’ But they were his downfall and the downfall of all Israel.

24Ahaz gathered together the furnishings from the temple of God and cut them in pieces. He shut the doors of the Lord’s temple and set up altars at every street corner in Jerusalem. 25In every town in Judah he built high places to burn sacrifices to other gods and aroused the anger of the Lord, the God of his ancestors.

26The other events of his reign and all his ways, from beginning to end, are written in the book of the kings of Judah and Israel. 27Ahaz rested with his ancestors and was buried in the city of Jerusalem, but he was not placed in the tombs of the kings of Israel. And Hezekiah his son succeeded him as king.